ዘፀአት 20:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 “አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝም+ አባትህንና እናትህን አክብር።+ ዘዳግም 5:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 “‘አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝምና መልካም እንዲሆንልህ+ አምላክህ ይሖዋ ባዘዘህ መሠረት አባትህንና እናትህን አክብር።+ ኤፌሶን 6:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ልጆች ሆይ፣ ከጌታ ፈቃድ ጋር በሚስማማ መንገድ ለወላጆቻችሁ ታዘዙ፤+ ይህ የጽድቅ ተግባር ነውና። ቆላስይስ 3:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 ልጆች ሆይ፣ በሁሉም ነገር ለወላጆቻችሁ ታዘዙ፤+ እንዲህ ማድረጋችሁ ጌታን ያስደስተዋልና።