ዮሐንስ 12:36 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 36 የብርሃን ልጆች+ እንድትሆኑ ብርሃኑ እያለላችሁ በብርሃኑ እመኑ።” ኢየሱስ ይህን ተናግሮ እንደጨረሰ ሄደ፤ ከእነሱም ተሰወረ። ሮም 13:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 ሌሊቱ እየተገባደደ ነው፤ ቀኑም ቀርቧል። ስለዚህ ከጨለማ ጋር የተያያዙ ሥራዎችን አውልቀን+ የብርሃንን የጦር ዕቃዎች እንልበስ።+ ኤፌሶን 5:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 እናንተ በአንድ ወቅት ጨለማ ውስጥ ነበራችሁና፤ አሁን ግን የጌታ በመሆናችሁ+ ብርሃን ውስጥ ናችሁ።+ የብርሃን ልጆች ሆናችሁ መመላለሳችሁን ቀጥሉ፤