-
ኤርምያስ 31:31-34አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
31 “እነሆ፣ ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር አዲስ ቃል ኪዳን የምገባበት ጊዜ ይመጣል” ይላል ይሖዋ።+ 32 “ይህም ቃል ኪዳን አባቶቻቸውን እጃቸውን ይዤ ከግብፅ ምድር እየመራሁ ባወጣኋቸው ቀን ከእነሱ ጋር እንደገባሁት ዓይነት ቃል ኪዳን አይሆንም፤+ ‘እኔ እውነተኛ ጌታቸው* ብሆንም እንኳ እነሱ ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋል’ ይላል ይሖዋ።”+
33 “ከዚያ ጊዜ በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና” ይላል ይሖዋ። “ሕጌን በውስጣቸው አኖራለሁ፤+ በልባቸውም እጽፈዋለሁ።+ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ፤ እነሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።”+
34 “እነሱም እያንዳንዳቸው ባልንጀራቸውን፣ እያንዳንዳቸውም ወንድማቸውን ‘ይሖዋን እወቅ!’ ብለው ከእንግዲህ አያስተምሩም፤+ ከትንሹ አንስቶ እስከ ትልቁ ድረስ ሁሉም ያውቁኛልና”+ ይላል ይሖዋ። “በደላቸውን ይቅር እላለሁና፤ ኃጢአታቸውንም ከእንግዲህ አላስታውስም።”+
-