28 እንዲህ በሏቸው፦ ‘“በሕያውነቴ እምላለሁ” ይላል ይሖዋ፤ “እናንተው ራሳችሁ ስትናገሩ የሰማሁትን ነገር አደርግባችኋለሁ!+ 29 ሃያ ዓመትና ከዚያ በላይ ሆኗችሁ የተመዘገባችሁትና የተቆጠራችሁት ሁሉ አዎ፣ በእኔ ላይ ያጉረመረማችሁት+ ሁሉ ሬሳችሁ በዚህ ምድረ በዳ ይወድቃል።+ 30 ከየፎኒ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በስተቀር+ አንዳችሁም ብትሆኑ በዚያ እንደማኖራችሁ ወደማልኩላችሁ ምድር አትገቡም።+