መዝሙር 2:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 የይሖዋን ድንጋጌ ልናገር፤እንዲህ ብሎኛል፦ “አንተ ልጄ ነህ፤+እኔ ዛሬ ወለድኩህ።+ ማቴዎስ 17:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 ኢየሱስ ከስድስት ቀን በኋላ ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ወንድሙን ዮሐንስን ብቻ ይዞ ወደ አንድ ረጅም ተራራ ወጣ።+ ማቴዎስ 17:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ገና እየተናገረ ሳለም ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፤ ከደመናውም “በጣም የምደሰትበት፣ የምወደው ልጄ ይህ ነው።+ እሱን ስሙት”+ የሚል ድምፅ ተሰማ። ማርቆስ 9:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ከዚያም ደመና መጥቶ ጋረዳቸው፤ ከደመናውም “የምወደው ልጄ ይህ ነው።+ እሱን ስሙት”+ የሚል ድምፅ መጣ።+ ሉቃስ 9:35 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 35 ከዚያም ከደመናው “የመረጥኩት ልጄ ይህ ነው።+ እሱን ስሙት”+ የሚል ድምፅ መጣ።+