የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘሌዋውያን 24
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘሌዋውያን የመጽሐፉ ይዘት

      • ለማደሪያው ድንኳን መብራቶች የሚሆን ዘይት (1-4)

      • ገጸ ኅብስት (5-9)

      • የአምላክን ስም የሰደበው በድንጋይ ተወገረ (10-23)

ዘሌዋውያን 24:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 27:20, 21፤ ዘኁ 8:2

ዘሌዋውያን 24:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 25:31፤ 39:33, 37፤ ዕብ 9:2

ዘሌዋውያን 24:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ሁለት አሥረኛ ኢፍ 4.4 ሊትር ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።

ዘሌዋውያን 24:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 25:23, 24፤ 1ነገ 7:48
  • +ዘፀ 40:22, 23፤ 1ሳሙ 21:4፤ ማር 2:25, 26

ዘሌዋውያን 24:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 2:2፤ 6:15

ዘሌዋውያን 24:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 4:7፤ 1ዜና 9:32፤ 2ዜና 2:4

ዘሌዋውያን 24:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 21:22፤ 22:10፤ 1ሳሙ 21:4, 6፤ ማቴ 12:3, 4፤ ሉቃስ 6:3, 4
  • +ዘሌ 6:14, 16

ዘሌዋውያን 24:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 12:38፤ ዘኁ 11:4

ዘሌዋውያን 24:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ዘሌ 24:15 እና 16 እንደሚጠቁሙት ይሖዋ የሚለውን ስም ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 20:7፤ 22:28፤ ዘሌ 19:12
  • +ዘፀ 18:22

ዘሌዋውያን 24:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 18:15, 16፤ ዘኁ 15:32, 34

ዘሌዋውያን 24:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 15:32, 35፤ ዘዳ 17:7

ዘሌዋውያን 24:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 5:11

ዘሌዋውያን 24:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የማንኛውንም ሰው ነፍስ መትቶ ከገደለ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 9:6፤ ዘፀ 21:12፤ ዘኁ 35:31፤ ዘዳ 19:11-13

ዘሌዋውያን 24:18

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የቤት እንስሳን ነፍስ መትቶ የገደለ።”

  • *

    ወይም “ነፍስ ስለ ነፍስ።”

ዘሌዋውያን 24:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 21:23, 24

ዘሌዋውያን 24:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 19:21፤ ማቴ 5:38

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ንቁ!፣

    9/2010፣ ገጽ 10-11

    መጠበቂያ ግንብ፣

    9/1/2009፣ ገጽ 22

ዘሌዋውያን 24:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 22:1
  • +ዘፍ 9:6፤ ዘፀ 21:12

ዘሌዋውያን 24:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 12:49፤ ዘሌ 17:10፤ 19:34፤ ዘኁ 9:14፤ 15:16

ዘሌዋውያን 24:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 15:33, 36፤ ዘዳ 17:7

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘሌ. 24:2ዘፀ 27:20, 21፤ ዘኁ 8:2
ዘሌ. 24:4ዘፀ 25:31፤ 39:33, 37፤ ዕብ 9:2
ዘሌ. 24:6ዘፀ 25:23, 24፤ 1ነገ 7:48
ዘሌ. 24:6ዘፀ 40:22, 23፤ 1ሳሙ 21:4፤ ማር 2:25, 26
ዘሌ. 24:7ዘሌ 2:2፤ 6:15
ዘሌ. 24:8ዘኁ 4:7፤ 1ዜና 9:32፤ 2ዜና 2:4
ዘሌ. 24:9ዘሌ 21:22፤ 22:10፤ 1ሳሙ 21:4, 6፤ ማቴ 12:3, 4፤ ሉቃስ 6:3, 4
ዘሌ. 24:9ዘሌ 6:14, 16
ዘሌ. 24:10ዘፀ 12:38፤ ዘኁ 11:4
ዘሌ. 24:11ዘፀ 20:7፤ 22:28፤ ዘሌ 19:12
ዘሌ. 24:11ዘፀ 18:22
ዘሌ. 24:12ዘፀ 18:15, 16፤ ዘኁ 15:32, 34
ዘሌ. 24:14ዘኁ 15:32, 35፤ ዘዳ 17:7
ዘሌ. 24:16ዘዳ 5:11
ዘሌ. 24:17ዘፍ 9:6፤ ዘፀ 21:12፤ ዘኁ 35:31፤ ዘዳ 19:11-13
ዘሌ. 24:19ዘፀ 21:23, 24
ዘሌ. 24:20ዘዳ 19:21፤ ማቴ 5:38
ዘሌ. 24:21ዘፀ 22:1
ዘሌ. 24:21ዘፍ 9:6፤ ዘፀ 21:12
ዘሌ. 24:22ዘፀ 12:49፤ ዘሌ 17:10፤ 19:34፤ ዘኁ 9:14፤ 15:16
ዘሌ. 24:23ዘኁ 15:33, 36፤ ዘዳ 17:7
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘሌዋውያን 24:1-23

ዘሌዋውያን

24 ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 2 “መብራቱ ያለማቋረጥ እንዲበራ ለማድረግ ለመብራቱ የሚሆን ተጨቅጭቆ የተጠለለ ንጹሕ የወይራ ዘይት እንዲያመጡልህ እስራኤላውያንን እዘዛቸው።+ 3 ከምሽት አንስቶ እስከ ጠዋት ድረስ መብራቱ በይሖዋ ፊት ያለማቋረጥ እንዲበራ አሮን በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ ካለው ከምሥክሩ መጋረጃ ውጭ ያስቀምጠው። በትውልዶቻችሁ ሁሉ ይህ ዘላለማዊ ደንብ ነው። 4 ዘወትር በይሖዋ ፊት እንዲሆኑ መብራቶቹን ከንጹሕ ወርቅ በተሠራው መቅረዝ+ ላይ በቦታ በቦታቸው ያስቀምጣቸው።

5 “አንተም የላመ ዱቄት ወስደህ የቀለበት ቅርጽ ያላቸው 12 ዳቦዎችን ጋግር። እያንዳንዱ ዳቦ ከሁለት አሥረኛ ኢፍ* ዱቄት የተዘጋጀ መሆን ይኖርበታል። 6 እነዚህንም በይሖዋ ፊት ባለው ከንጹሕ ወርቅ በተሠራው ጠረጴዛ+ ላይ ስድስት ስድስት አድርገህ በማነባበር በሁለት ረድፍ ታስቀምጣቸዋለህ።+ 7 ተነባብሮ በተቀመጠው በእያንዳንዱ ረድፍ ላይም ንጹሕ ነጭ ዕጣን አድርግ፤ ይህም ለምግቡ መታሰቢያ እንዲሆን+ ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ ይሆናል። 8 እሱም በየሰንበቱ ዘወትር በይሖዋ ፊት ይደርድረው።+ ይህ በእኔና በእስራኤላውያን መካከል ያለ ዘላቂ ቃል ኪዳን ነው። 9 ይህም የአሮንና የወንዶች ልጆቹ ይሆናል፤+ ለይሖዋ በእሳት ከሚቀርቡት መባዎች መካከል ለእሱ እጅግ ቅዱስ ነገር ስለሆነ ቅዱስ በሆነ ቦታ ይበሉታል፤+ ይህ ዘላቂ ሥርዓት ነው።”

10 በእስራኤላውያን መካከል በእናቱ እስራኤላዊ በአባቱ ግን ግብፃዊ የሆነ አንድ ሰው ነበር፤+ በሰፈሩም ውስጥ በእሱና በአንድ እስራኤላዊ መካከል ጠብ ተነሳ። 11 የእስራኤላዊቷም ልጅ የአምላክን ስም* መሳደብና መራገም ጀመረ።+ በመሆኑም ወደ ሙሴ አመጡት።+ የእናትየውም ስም ሸሎሚት ነበር፤ እሷም ከዳን ነገድ የሆነው የዲብራይ ልጅ ነበረች። 12 እነሱም የይሖዋ ውሳኔ ግልጽ እስኪሆንላቸው ድረስ በጥበቃ ሥር እንዲቆይ አደረጉት።+

13 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 14 “የተራገመውን ሰው ከሰፈሩ ውጭ አውጣው፤ የሰሙትም ሰዎች ሁሉ እጃቸውን በራሱ ላይ ይጫኑበት፤ መላው ጉባኤም በድንጋይ ይውገረው።+ 15 ለእስራኤላውያንም እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘ማንኛውም ሰው አምላኩን ቢራገም ለሠራው ኃጢአት ይጠየቅበታል። 16 ስለሆነም የይሖዋን ስም የተሳደበው ሰው ይገደል።+ መላው ጉባኤም በድንጋይ ይውገረው። የባዕድ አገሩም ሰው የአምላክን ስም ከተሳደበ ልክ እንደ አገሩ ተወላጅ ይገደል።

17 “‘አንድ ሰው የሰው ሕይወት ካጠፋ* ይገደል።+ 18 የቤት እንስሳን የገደለ* ሰው፣ ሕይወት ስለ ሕይወት* ካሳ አድርጎ መክፈል ይኖርበታል። 19 አንድ ሰው በባልንጀራው ላይ ጉዳት ቢያደርስ ልክ እሱ ያደረሰው ዓይነት ጉዳት በራሱ ላይ እንዲደርስ ይደረግ።+ 20 ስብራት ስለ ስብራት፣ ዓይን ስለ ዓይን፣ ጥርስ ስለ ጥርስ ይሁን፤ በሰውየው ላይ ያደረሰው ዓይነት ጉዳት በእሱ ላይ እንዲደርስ ይደረግ።+ 21 እንስሳን መትቶ የገደለ ስለ እንስሳው ካሳ መክፈል ይኖርበታል፤+ ሰውን መትቶ የገደለ ግን መገደል አለበት።+

22 “‘ለባዕድ አገሩም ሰው ሆነ ለአገሬው ተወላጅ፣ ለሁላችሁም የሚሠራው አንድ ዓይነት ድንጋጌ ነው፤+ ምክንያቱም እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ።’”

23 ከዚያም ሙሴ ለእስራኤላውያን ነገራቸው፤ እነሱም የተራገመውን ሰው ከሰፈሩ ውጭ አውጥተው በድንጋይ ወገሩት።+ በዚህ መንገድ እስራኤላውያን ልክ ይሖዋ ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ