የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘፍጥረት 35
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘፍጥረት የመጽሐፉ ይዘት

      • ያዕቆብ ባዕዳን አማልክትን አስወገደ (1-4)

      • ያዕቆብ ወደ ቤቴል ተመለሰ (5-15)

      • ቢንያም ተወለደ፤ ራሔል ሞተች (16-20)

      • የእስራኤል 12 ወንዶች ልጆች (21-26)

      • ይስሐቅ ሞተ (27-29)

ዘፍጥረት 35:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 28:19፤ 31:13
  • +ዘፍ 27:42-44

ዘፍጥረት 35:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 31:19፤ ዘዳ 5:7፤ ኢያሱ 23:7፤ 1ቆሮ 10:14

ዘፍጥረት 35:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በሄድኩበት መንገድ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 28:13, 15፤ 31:42

ዘፍጥረት 35:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ደበቃቸው።”

ዘፍጥረት 35:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 28:19

ዘፍጥረት 35:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “የቤቴል አምላክ” የሚል ትርጉም አለው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 28:20-22

ዘፍጥረት 35:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “የለቅሶ የባሉጥ ዛፍ” የሚል ትርጉም አለው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 24:59

ዘፍጥረት 35:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 25:26፤ 27:36
  • +ዘፍ 32:28

ዘፍጥረት 35:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ከወገብህ ይወጣሉ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 17:1፤ ዘፀ 6:3፤ ራእይ 15:3
  • +ዘፍ 48:3, 4
  • +ዘፍ 17:5, 6፤ ዮሐ 12:13

ዘፍጥረት 35:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 15:18፤ ዘዳ 34:4

ዘፍጥረት 35:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 28:18

ዘፍጥረት 35:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 28:19

ዘፍጥረት 35:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 30:22-24

ዘፍጥረት 35:18

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሷ በምትወጣበት ጊዜ።”

  • *

    “የሐዘኔ ልጅ” የሚል ትርጉም አለው።

  • *

    “የቀኝ እጅ ልጅ” የሚል ትርጉም አለው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 46:21፤ 49:27፤ ዘዳ 33:12

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው፣ ርዕስ 71

    መጠበቂያ ግንብ፣

    2/1/2009፣ ገጽ 14

    7/15/2007፣ ገጽ 4-5

    4/1/1999፣ ገጽ 16

    ስንሞት ምን እንሆናለን?፣ ገጽ 22-23

ዘፍጥረት 35:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 48:7፤ ሚክ 5:2፤ ማቴ 2:6

ዘፍጥረት 35:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 49:3, 4፤ 1ዜና 5:1

ዘፍጥረት 35:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 49:3

ዘፍጥረት 35:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 15:13፤ ዕብ 11:9
  • +ዘፍ 31:17, 18

ዘፍጥረት 35:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 25:20, 26

ዘፍጥረት 35:29

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ይህ ሞትን የሚያመለክት ቅኔያዊ አነጋገር ነው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 49:30, 31

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘፍ. 35:1ዘፍ 28:19፤ 31:13
ዘፍ. 35:1ዘፍ 27:42-44
ዘፍ. 35:2ዘፍ 31:19፤ ዘዳ 5:7፤ ኢያሱ 23:7፤ 1ቆሮ 10:14
ዘፍ. 35:3ዘፍ 28:13, 15፤ 31:42
ዘፍ. 35:6ዘፍ 28:19
ዘፍ. 35:7ዘፍ 28:20-22
ዘፍ. 35:8ዘፍ 24:59
ዘፍ. 35:10ዘፍ 25:26፤ 27:36
ዘፍ. 35:10ዘፍ 32:28
ዘፍ. 35:11ዘፍ 17:1፤ ዘፀ 6:3፤ ራእይ 15:3
ዘፍ. 35:11ዘፍ 48:3, 4
ዘፍ. 35:11ዘፍ 17:5, 6፤ ዮሐ 12:13
ዘፍ. 35:12ዘፍ 15:18፤ ዘዳ 34:4
ዘፍ. 35:14ዘፍ 28:18
ዘፍ. 35:15ዘፍ 28:19
ዘፍ. 35:17ዘፍ 30:22-24
ዘፍ. 35:18ዘፍ 46:21፤ 49:27፤ ዘዳ 33:12
ዘፍ. 35:19ዘፍ 48:7፤ ሚክ 5:2፤ ማቴ 2:6
ዘፍ. 35:22ዘፍ 49:3, 4፤ 1ዜና 5:1
ዘፍ. 35:23ዘፍ 49:3
ዘፍ. 35:27ዘፍ 15:13፤ ዕብ 11:9
ዘፍ. 35:27ዘፍ 31:17, 18
ዘፍ. 35:28ዘፍ 25:20, 26
ዘፍ. 35:29ዘፍ 49:30, 31
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘፍጥረት 35:1-29

ዘፍጥረት

35 ከዚያ በኋላ አምላክ ያዕቆብን እንዲህ አለው፦ “ተነስተህ ወደ ቤቴል+ ውጣ፤ በዚያም ኑር፤ ከወንድምህ ከኤሳው እየሸሸህ+ ሳለህ ለተገለጠልህ ለእውነተኛው አምላክ በዚያ መሠዊያ ሥራ።”

2 ከዚያም ያዕቆብ ቤተሰቡንና አብረውት የነበሩትን ሰዎች ሁሉ እንዲህ አላቸው፦ “በመካከላችሁ ያሉትን ባዕዳን አማልክት አስወግዱ፤+ ራሳችሁን አንጹ፤ ልብሳችሁንም ቀይሩ፤ 3 ተነስተንም ወደ ቤቴል እንውጣ። በዚያም በጭንቀቴ ጊዜ ለሰማኝና በሄድኩበት ሁሉ* ከእኔ ላልተለየው+ ለእውነተኛው አምላክ መሠዊያ እሠራለሁ።” 4 በመሆኑም ባዕዳን አማልክታቸውን በሙሉ እንዲሁም በጆሯቸው ላይ ያደረጓቸውን ጉትቻዎች ለያዕቆብ ሰጡት፤ ያዕቆብም በሴኬም አቅራቢያ ባለው ትልቅ ዛፍ ሥር ቀበራቸው።*

5 በሚጓዙበት ጊዜም አምላክ በዙሪያቸው ባሉት ከተሞች ላይ ሽብር ይለቅባቸው ስለነበር የያዕቆብን ልጆች አላሳደዷቸውም። 6 በመጨረሻም ያዕቆብና አብረውት ያሉት ሰዎች በሙሉ በከነአን ምድር ወደምትገኘው ወደ ሎዛ+ ማለትም ወደ ቤቴል መጡ። 7 እሱም በዚያ መሠዊያ ሠራ፤ የቦታውንም ስም ኤልቤቴል* አለው፤ ምክንያቱም ከወንድሙ በሸሸበት ጊዜ እውነተኛው አምላክ በዚያ ራሱን ገልጦለት ነበር።+ 8 በኋላም የርብቃ ሞግዚት ዲቦራ+ ሞተች፤ በቤቴል አቅራቢያ በሚገኝ የባሉጥ ዛፍ ሥርም ተቀበረች። በመሆኑም ስሙን አሎንባኩት* አለው።

9 ያዕቆብ ከጳዳንአራም እየተመለሰ ሳለ አምላክ ዳግመኛ ተገለጠለትና ባረከው። 10 አምላክም “ስምህ ያዕቆብ ነው።+ ከእንግዲህ ያዕቆብ ተብለህ አትጠራም፤ ከዚህ ይልቅ ስምህ እስራኤል ይባላል” አለው። ስለዚህ እስራኤል ብሎ ጠራው።+ 11 በተጨማሪም አምላክ እንዲህ አለው፦ “እኔ ሁሉን ቻይ አምላክ ነኝ።+ ብዛ፣ ተባዛ። ብሔራትና ብዙ ብሔራትን ያቀፈ ጉባኤ ከአንተ ይገኛሉ፤+ ነገሥታትም ከአንተ ይወጣሉ።*+ 12 ለአብርሃምና ለይስሐቅ የሰጠኋትን ምድር ለአንተ እሰጥሃለሁ፤ ከአንተ በኋላ ለሚመጡት ዘሮችህም ይህችን ምድር እሰጣለሁ።”+ 13 ከዚያም አምላክ ከእሱ ጋር ሲነጋገርበት ከነበረው ስፍራ ወደ ላይ ወጣ።

14 ስለዚህ ያዕቆብ ከአምላክ ጋር ሲነጋገር በነበረበት ስፍራ ላይ የድንጋይ ዓምድ አቆመ፤ ባቆመውም ዓምድ ላይ የመጠጥ መባና ዘይት አፈሰሰበት።+ 15 ያዕቆብም ከአምላክ ጋር የተነጋገረበትን ስፍራ ቤቴል+ በሚለው በዚያው ስም ጠራው።

16 ከዚያም ከቤቴል ተነስተው ሄዱ። ኤፍራታ ለመድረስ የተወሰነ ርቀት ሲቀራቸው ራሔል ምጥ ያዛት፤ ምጡም እጅግ ጠናባት። 17 ምጡ እጅግ አስጨንቋት ሳለም አዋላጇ “አይዞሽ አትፍሪ፤ ሌላ ወንድ ልጅ ልትገላገዪ ነው” አለቻት።+ 18 እሷ ግን ሕይወቷ ሊያልፍ በማጣጣር ላይ ሳለች* (ሞት አፋፍ ላይ ስለነበረች) የልጁን ስም ቤንኦኒ* አለችው፤ አባቱ ግን ስሙን ቢንያም*+ አለው። 19 ራሔልም ሞተች፤ ወደ ኤፍራታ ይኸውም ወደ ቤተልሔም+ በሚወስደው መንገድ ላይ ተቀበረች። 20 ያዕቆብም በመቃብሯ ላይ ዓምድ አቆመ፤ ይህ የራሔል መቃብር ዓምድ እስከ ዛሬ ድረስ አለ።

21 ከዚያ በኋላ እስራኤል ከዚያ ተነስቶ በመሄድ ከኤዴር ማማ አለፍ ብሎ ድንኳኑን ተከለ። 22 አንድ ቀን፣ እስራኤል በዚያ ምድር ሰፍሮ ሳለ ሮቤል ከአባቱ ቁባት ከባላ ጋር ተኛ፤ እስራኤልም ይህን ሰማ።+

ያዕቆብ 12 ወንዶች ልጆች ነበሩት። 23 ከሊያ የወለዳቸው ወንዶች ልጆቹ የበኩር ልጁ ሮቤል+ ከዚያም ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣ ይሳኮር እና ዛብሎን ነበሩ። 24 ከራሔል የወለዳቸው ወንዶች ልጆቹ ዮሴፍና ቢንያም ነበሩ። 25 ከራሔል አገልጋይ ከባላ የወለዳቸው ወንዶች ልጆቹ ዳንና ንፍታሌም ነበሩ። 26 ከሊያ አገልጋይ ከዚልጳ የወለዳቸው ወንዶች ልጆቹ ደግሞ ጋድና አሴር ነበሩ። እነዚህ ያዕቆብ በጳዳንአራም ሳለ የወለዳቸው ወንዶች ልጆቹ ናቸው።

27 ከጊዜ በኋላ ያዕቆብ አባቱ ይስሐቅ ወደነበረበት፣ አብርሃምና ይስሐቅ የባዕድ አገር ሰው ሆነው ወደኖሩበት+ በቂርያትአርባ ይኸውም በኬብሮን አካባቢ ወደሚገኘው ወደ ማምሬ መጣ።+ 28 ይስሐቅ 180 ዓመት ኖረ።+ 29 ከዚያም ይስሐቅ የመጨረሻ እስትንፋሱን ተነፈሰ፤ ዕድሜ ጠግቦና በሕይወቱ ረክቶ ሞተ፤ ወደ ወገኖቹም ተሰበሰበ፤* ልጆቹ ኤሳውና ያዕቆብም ቀበሩት።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ