የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘዳግም 25
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘዳግም የመጽሐፉ ይዘት

      • የግርፋት ሕግ (1-3)

      • የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር (4)

      • የወንድምን ሚስት ማግባት (5-10)

      • በጠብ ጊዜ ተገቢ ያልሆነን የሰውነት ክፍል መያዝ (11, 12)

      • ትክክለኛ ሚዛንና መለኪያ (13-16)

      • አማሌቃውያን መጥፋት አለባቸው (17-19)

ዘዳግም 25:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 16:18፤ 17:8, 9፤ 19:16, 17
  • +ዘፀ 23:6፤ 2ዜና 19:6፤ ምሳሌ 17:15፤ 31:9

ዘዳግም 25:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 10:13፤ 20:30፤ 26:3፤ ሉቃስ 12:48፤ ዕብ 2:2

ዘዳግም 25:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ቆሮ 11:24

ዘዳግም 25:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 12:10፤ 1ቆሮ 9:9፤ 1ጢሞ 5:18

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    5/1/2012፣ ገጽ 30

ዘዳግም 25:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 38:7, 8፤ ሩት 4:5፤ ማር 12:19

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    አዲስ ዓለም ትርጉም፣ ገጽ 1648

ዘዳግም 25:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 38:9፤ ሩት 4:10, 17
  • +ዘኁ 27:1, 4

ዘዳግም 25:7

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 7/2021፣ ገጽ 6

ዘዳግም 25:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሩት 4:7

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    9/15/2004፣ ገጽ 26

ዘዳግም 25:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የዚያ ሰው ስም።”

ዘዳግም 25:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ዓይንህ ሊያዝንላት አይገባም።”

ዘዳግም 25:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 11:1፤ 20:10፤ ሚክ 6:11

ዘዳግም 25:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “በቤትህ ውስጥ አንድ ኢፍና አንድ ኢፍ።” ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 19:36

ዘዳግም 25:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 4:40

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    8/2022፣ ገጽ 27

ዘዳግም 25:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 19:35

ዘዳግም 25:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 17:8፤ ዘኁ 24:20

ዘዳግም 25:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 22:4
  • +ዘፀ 17:14፤ 1ሳሙ 14:47, 48፤ 15:1-3፤ 1ዜና 4:42, 43

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ምሰሏቸው፣ ገጽ 144

    መጠበቂያ ግንብ፣

    1/1/2012፣ ገጽ 29

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘዳ. 25:1ዘዳ 16:18፤ 17:8, 9፤ 19:16, 17
ዘዳ. 25:1ዘፀ 23:6፤ 2ዜና 19:6፤ ምሳሌ 17:15፤ 31:9
ዘዳ. 25:2ምሳሌ 10:13፤ 20:30፤ 26:3፤ ሉቃስ 12:48፤ ዕብ 2:2
ዘዳ. 25:32ቆሮ 11:24
ዘዳ. 25:4ምሳሌ 12:10፤ 1ቆሮ 9:9፤ 1ጢሞ 5:18
ዘዳ. 25:5ዘፍ 38:7, 8፤ ሩት 4:5፤ ማር 12:19
ዘዳ. 25:6ዘፍ 38:9፤ ሩት 4:10, 17
ዘዳ. 25:6ዘኁ 27:1, 4
ዘዳ. 25:9ሩት 4:7
ዘዳ. 25:13ምሳሌ 11:1፤ 20:10፤ ሚክ 6:11
ዘዳ. 25:14ዘሌ 19:36
ዘዳ. 25:15ዘዳ 4:40
ዘዳ. 25:16ዘሌ 19:35
ዘዳ. 25:17ዘፀ 17:8፤ ዘኁ 24:20
ዘዳ. 25:19ኢያሱ 22:4
ዘዳ. 25:19ዘፀ 17:14፤ 1ሳሙ 14:47, 48፤ 15:1-3፤ 1ዜና 4:42, 43
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘዳግም 25:1-19

ዘዳግም

25 “በሰዎች መካከል አለመግባባት ቢፈጠር ሰዎቹ ዳኞች ፊት መቅረብ ይችላሉ፤+ እነሱም ይዳኟቸዋል፤ ጻድቅ የሆነውን ንጹሕ፣ ጥፋተኛ የሆነውን ደግሞ በደለኛ ይሉታል።+ 2 ጥፋተኛው መገረፍ የሚገባው ሆኖ ከተገኘ+ ዳኛው መሬት ላይ እንዲያስተኙትና እሱ ባለበት እንዲገረፍ ያደርጋል። የግርፋቱም ቁጥር ከሠራው ጥፋት ጋር የሚመጣጠን ይሁን። 3 እስከ 40 ግርፋት ሊገርፈው ይችላል፤+ ከዚያ ማስበለጥ ግን የለበትም። ከዚህ የበለጠ ብዙ ግርፋት ከገረፈው ግን ወንድምህ በፊትህ ይዋረዳል።

4 “እህል እያበራየ ያለውን በሬ አፉን አትሰር።+

5 “ወንድማማቾች አንድ ላይ ሲኖሩ ቆይተው ከመካከላቸው አንዱ ወንድ ልጅ ሳይወልድ ቢሞት የሟቹ ሚስት ከቤተሰቡ ውጭ የሆነ ሰው ማግባት የለባትም። የባሏ ወንድም ወደ እሷ በመሄድ ሚስቱ አድርጎ ይውሰዳት፤ የዋርሳነት ግዴታውንም ይፈጽምላት።+ 6 መጀመሪያ የምትወልደው ልጅ በሟች ወንድሙ ስም ይጠራል፤+ ይህ የሚሆነው የሟቹ ስም ከእስራኤል መካከል እንዳይጠፋ ነው።+

7 “ሰውየው የሟች ወንድሙን ሚስት ለማግባት ፈቃደኛ ካልሆነ መበለት የሆነችው ሴት በከተማዋ በር ወደሚገኙት ሽማግሌዎች ሄዳ ‘የባሌ ወንድም የወንድሙ ስም ከእስራኤል መካከል እንዳይጠፋ ለማድረግ ፈቃደኛ አልሆነም። የዋርሳነት ግዴታውን ሊፈጽምልኝ አልተስማማም’ ትበላቸው። 8 የከተማዋ ሽማግሌዎችም ጠርተው ያናግሩት። እሱም ‘እኔ እሷን ማግባት አልፈልግም’ ብሎ በሐሳቡ ከጸና 9 የወንድሙ ሚስት በሽማግሌዎቹ ፊት ወደ እሱ ቀርባ ጫማውን ከእግሩ ላይ ታውልቅ፤+ ከዚያም ፊቱ ላይ ትትፋበትና ‘የወንድሙን ቤት በማይሠራ ሰው ላይ የሚደረግበት እንዲህ ነው’ ትበል። 10 ከዚያ በኋላ የዚያ ሰው ቤተሰብ ስም* በእስራኤል ውስጥ ‘ጫማው የወለቀበት ሰው ቤት’ ይባላል።

11 “ሁለት ሰዎች ቢደባደቡና የአንደኛው ሚስት ባሏን ከደብዳቢው እጅ ለማስጣል ስትል እጇን ዘርግታ ብልቱን ብትይዝ 12 እጇን ቁረጠው። ልታዝንላት አይገባም።*

13 “በከረጢትህ ውስጥ ትልቅና ትንሽ የሆኑ ሁለት ዓይነት የሚዛን ድንጋዮች አይኑሩህ።+ 14 በቤትህም ውስጥ ትልቅና ትንሽ የሆኑ ሁለት ዓይነት መስፈሪያዎች* አይኑሩህ።+ 15 አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝም ትክክለኛና ሐቀኛ ሚዛን እንዲሁም ትክክለኛና ሐቀኛ መስፈሪያ ይኑርህ።+ 16 ምክንያቱም እንዲህ ያሉ ነገሮችን በማድረግ ፍትሕ የጎደለው ድርጊት የሚፈጽም ሰው ሁሉ በአምላክህ በይሖዋ ፊት አስጸያፊ ነው።+

17 “ከግብፅ በወጣችሁ ጊዜ መንገድ ላይ ሳላችሁ አማሌቃውያን ያደረጉባችሁን ነገር አስታውሱ፤+ 18 በጉዞ ላይ ሳለህ ደክመህና ዝለህ በነበረበት ጊዜ አግኝተውህ ከኋላ ከኋላህ እያዘገሙ በነበሩት ሁሉ ላይ እንዴት ጥቃት እንደሰነዘሩ አስታውስ። አምላክንም አልፈሩም። 19 አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርገህ እንድትወርሳት በሚሰጥህ ምድር ላይ አምላክህ ይሖዋ በዙሪያህ ካሉት ጠላቶችህ ሁሉ በሚያሳርፍህ ጊዜ+ አማሌቃውያንን ከሰማይ በታች ጨርሶ እንዳይታወሱ አድርገህ ጠራርገህ አጥፋቸው።+ ይህን አትርሳ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ