መዝሙር
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በባለ አውታር መሣሪያዎች የሚታጀብ። የአሳፍ+ ማህሌት። መዝሙር።
3 በዚያም የሚንበለበሉትን ፍላጻዎች፣
ጋሻን፣ ሰይፍንና የጦር መሣሪያዎችን ሰባበረ።+ (ሴላ)
5 ልበ ሙሉ የሆኑት ሰዎች ተዘርፈዋል።+
እንቅልፍ ጥሏቸዋል፤
ተዋጊዎቹ በሙሉ መከላከል የሚችሉበት ኃይል አልነበራቸውም።+
6 የያዕቆብ አምላክ ሆይ፣ ከተግሣጽህ የተነሳ
ባለ ሠረገላውም ሆነ ፈረሱ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወስዷቸዋል።+
7 አንተ ብቻ እጅግ የምትፈራ ነህ።+
ኃይለኛ ቁጣህን ማን ሊቋቋም ይችላል?+
8 አንተ ከሰማይ ፍርድ ተናገርክ፤+
ምድር ፈርታ ዝም አለች፤+
9 ይህም የሆነው አምላክ በምድር ላይ የሚኖሩትን የዋሆች ሁሉ ለማዳን+
ፍርድ ሊያስፈጽም በተነሳበት ጊዜ ነው። (ሴላ)
12 እሱ የመሪዎችን ኩራት* ያስወግዳል፤
በምድር ነገሥታት ላይ ፍርሃት ያሳድራል።