መዝሙር
መዝሙር። የቆሬ ልጆች+ ማህሌት። ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በማሃላት ቅኝት፤* በመቀባበል የሚዘመር። የዛራዊው የሄማን+ ማስኪል።*
4 አሁንም እንኳ ወደ ጉድጓድ* ከሚወርዱ ሰዎች ጋር ተቆጥሬአለሁ፤+
5 ተገድለው በመቃብር ውስጥ እንደተጋደሙ፣
ከእንግዲህ ፈጽሞ እንደማታስታውሳቸውና
የአንተ እንክብካቤ* እንደተቋረጠባቸው ሰዎች፣
በሙታን መካከል ተተውኩ።
6 አዘቅት ውስጥ ከተትከኝ፤
በጨለማ በተዋጠ ስፍራ፣ ጥልቅ በሆነ ጉድጓድ ውስጥ አኖርከኝ።
7 በላዬ ላይ ያረፈው ቁጣህ እጅግ ከብዶኛል፤+
በኃይለኛ ማዕበልህም አጥለቀለቅከኝ። (ሴላ)
8 የሚያውቁኝን ሰዎች ከእኔ አራቅክ፤+
በእነሱ ፊት አስጸያፊ ነገር አደረግከኝ።
ወጥመድ ውስጥ ገብቻለሁ፤ ማምለጥም አልቻልኩም።
9 ከደረሰብኝ ጉስቁልና የተነሳ ዓይኔ ፈዘዘ።+
ይሖዋ ሆይ፣ ቀኑን ሙሉ አንተን እጣራለሁ፤+
እጆቼንም ወደ አንተ እዘረጋለሁ።
10 ለሙታን ድንቅ ሥራዎች ታከናውናለህ?
በሞት የተረቱትስ ተነስተው ሊያወድሱህ ይችላሉ?+ (ሴላ)
11 ታማኝ ፍቅርህ በመቃብር፣
ታማኝነትህስ በጥፋት ቦታ* ይታወጃል?
12 ያከናወንከው ድንቅ ሥራ በጨለማ፣
ጽድቅህስ በተረሱ ሰዎች ምድር ይታወቃል?+
14 ይሖዋ ሆይ፣ ፊት የምትነሳኝ ለምንድን ነው?*+
ፊትህንስ ከእኔ የምትሰውረው ለምንድን ነው?+
16 የሚነደው ቁጣህ በላዬ ላይ ወረደ፤+
አንተ ያመጣህብኝ ሽብር አጠፋኝ።
17 ቀኑን ሙሉ እንደ ውኃ ከበበኝ፤
በሁሉም አቅጣጫ* ከቦ መውጫ አሳጣኝ።
18 ወዳጆቼንና ባልንጀሮቼን ከእኔ አራቅክ፤+
ጓደኛዬ ጨለማ ብቻ ሆኖ ቀረ።