የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘሌዋውያን 17
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘሌዋውያን የመጽሐፉ ይዘት

      • የማደሪያ ድንኳኑ፣ መሥዋዕቶች የሚቀርቡበት ቦታ (1-9)

      • ደም መብላት የተከለከለ ነው (10-14)

      • ሞተው የተገኙ እንስሳትን በተመለከተ የተሰጠ ሕግ (15, 16)

ዘሌዋውያን 17:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 3:1, 2፤ 7:11

ዘሌዋውያን 17:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የሚያረጋጋ፤ የሚያበርድ።” ቃል በቃል “እረፍት የሚሰጥ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 3:3-5፤ 7:29-31

ዘሌዋውያን 17:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ፍየሎች።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 34:15፤ ዘዳ 31:16
  • +ዘዳ 32:17፤ ኢያሱ 24:14

ዘሌዋውያን 17:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 1:3፤ ዘዳ 12:5, 6, 13, 14

ዘሌዋውያን 17:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍስ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 9:4፤ ዘሌ 3:17፤ 7:26፤ 19:26፤ 1ሳሙ 14:33፤ ሥራ 15:20, 29

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 39

    መጠበቂያ ግንብ፣

    11/15/2014፣ ገጽ 10-11

    6/15/1991፣ ገጽ 9

    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ጥራዝ 6፣ ገጽ 1

ዘሌዋውያን 17:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍስ።”

  • *

    ወይም “ለነፍሳችሁም።”

  • *

    ወይም “ነፍስ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 17:14፤ ዘዳ 12:23
  • +ዘሌ 8:15፤ 16:18
  • +ማቴ 26:28፤ ሮም 3:25፤ 5:9፤ ኤፌ 1:7፤ ዕብ 9:22፤ 13:12፤ 1ጴጥ 1:2፤ 1ዮሐ 1:7፤ ራእይ 1:5

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ከአምላክ ፍቅር፣ ገጽ 75

    መጠበቂያ ግንብ፣

    6/15/2004፣ ገጽ 15

    6/15/1991፣ ገጽ 9

ዘሌዋውያን 17:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ማንኛውም ነፍስ ደም መብላት የለበትም።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 12:49
  • +ዘዳ 12:23

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    6/15/2004፣ ገጽ 15

ዘሌዋውያን 17:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 12:16፤ 15:23

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?፣ ገጽ 139

    የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፣ ገጽ 129

    መጠበቂያ ግንብ፣

    6/15/2004፣ ገጽ 15

    10/15/2000፣ ገጽ 30-31

ዘሌዋውያን 17:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍስ።”

  • *

    ወይም “ነፍስ።”

  • *

    ወይም “ነፍስ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 17:10, 11

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው፣ ርዕስ 41

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 39

ዘሌዋውያን 17:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍስ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 22:31፤ ዘዳ 14:21
  • +ዘሌ 11:40

ዘሌዋውያን 17:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 19:20

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘሌ. 17:5ዘሌ 3:1, 2፤ 7:11
ዘሌ. 17:6ዘሌ 3:3-5፤ 7:29-31
ዘሌ. 17:7ዘፀ 34:15፤ ዘዳ 31:16
ዘሌ. 17:7ዘዳ 32:17፤ ኢያሱ 24:14
ዘሌ. 17:9ዘሌ 1:3፤ ዘዳ 12:5, 6, 13, 14
ዘሌ. 17:10ዘፍ 9:4፤ ዘሌ 3:17፤ 7:26፤ 19:26፤ 1ሳሙ 14:33፤ ሥራ 15:20, 29
ዘሌ. 17:11ዘሌ 17:14፤ ዘዳ 12:23
ዘሌ. 17:11ዘሌ 8:15፤ 16:18
ዘሌ. 17:11ማቴ 26:28፤ ሮም 3:25፤ 5:9፤ ኤፌ 1:7፤ ዕብ 9:22፤ 13:12፤ 1ጴጥ 1:2፤ 1ዮሐ 1:7፤ ራእይ 1:5
ዘሌ. 17:12ዘፀ 12:49
ዘሌ. 17:12ዘዳ 12:23
ዘሌ. 17:13ዘዳ 12:16፤ 15:23
ዘሌ. 17:14ዘሌ 17:10, 11
ዘሌ. 17:15ዘፀ 22:31፤ ዘዳ 14:21
ዘሌ. 17:15ዘሌ 11:40
ዘሌ. 17:16ዘኁ 19:20
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘሌዋውያን 17:1-16

ዘሌዋውያን

17 ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 2 “አሮንንና ወንዶች ልጆቹን እንዲሁም እስራኤላውያንን በሙሉ እንዲህ በላቸው፦ ‘ይሖዋ ያዘዘው ይህ ነው፦

3 “‘“ከእስራኤል ቤት የሆነ ማንኛውም ሰው በሬ ወይም የበግ ጠቦት አሊያም ፍየል በሰፈሩ ውስጥ ወይም ከሰፈሩ ውጭ ቢያርድና 4 በይሖዋ የማደሪያ ድንኳን ፊት ለይሖዋ መባ አድርጎ ለማቅረብ ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ባያመጣ ያ ሰው በደም ዕዳ ይጠየቃል። ሰውየው ደም አፍስሷል፤ በመሆኑም ይህ ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ መደረግ አለበት። 5 ይህም እስራኤላውያን በሜዳ ላይ እየሠዉ ያሉትን መሥዋዕት ወደ ይሖዋ፣ ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግቢያና ወደ ካህኑ እንዲያመጡ ነው። እነዚህንም ለይሖዋ የኅብረት መሥዋዕቶች አድርገው መሠዋት አለባቸው።+ 6 ካህኑም ደሙን በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ ባለው የይሖዋ መሠዊያ ላይ ይረጨዋል፤ ስቡንም ለይሖዋ ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ አድርጎ ያጨሰዋል።+ 7 ከእንግዲህ ወዲህ፣ አብረዋቸው ምንዝር ለሚፈጽሙት+ ፍየል የሚመስሉ አጋንንት*+ አይሠዉም። ይህም በመጪዎቹ ትውልዶቻችሁ ሁሉ ለእናንተ ዘላቂ ደንብ ሆኖ ያገለግላል።”’

8 “እንዲህም በላቸው፦ ‘የሚቃጠል መባ ወይም መሥዋዕት የሚያቀርብ ከእስራኤል ቤት የሆነ ማንኛውም ሰው ወይም በመካከላችሁ የሚኖር ማንኛውም የባዕድ አገር ሰው 9 ይህን ለይሖዋ ለማቅረብ ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ባያመጣ ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ መደረግ አለበት።+

10 “‘ከእስራኤል ቤት የሆነ ማንኛውም ሰው ወይም በመካከላችሁ የሚኖር የትኛውም የባዕድ አገር ሰው ምንም ዓይነት ደም ቢበላ፣+ ደም በሚበላው ሰው* ላይ በእርግጥ ፊቴን አጠቁርበታለሁ፤ ከሕዝቡም መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ። 11 ምክንያቱም የሥጋ ሕይወት* ያለው በደሙ ውስጥ ነው፤+ ለራሳችሁም* ማስተሰረያ እንዲሆን እኔ ራሴ ደሙን ለእናንተ ስል ለመሠዊያው ሰጥቼዋለሁ፤+ ምክንያቱም በውስጡ ባለው ሕይወት* አማካኝነት የሚያስተሰርየው ደሙ ነው።+ 12 እስራኤላውያንን “ማንኛችሁም ደም መብላት የለባችሁም፤* እንዲሁም በመካከላችሁ የሚኖር ማንኛውም የባዕድ አገር ሰው+ ደም አይብላ”+ ያልኳቸው ለዚህ ነው።

13 “‘አንድ እስራኤላዊ ወይም በመካከላችሁ የሚኖር አንድ የባዕድ አገር ሰው ለመብልነት የተፈቀደ እንስሳ ወይም ወፍ አድኖ ቢይዝ ደሙን ያፍሰው፤+ አፈርም ያልብሰው። 14 የሥጋ ሁሉ ሕይወት* ደሙ ነውና፤ ምክንያቱም በውስጡ ሕይወት* አለ። በዚህም የተነሳ እስራኤላውያንን እንዲህ አልኳቸው፦ “የሥጋ ሁሉ ሕይወት* ደሙ ስለሆነ የማንኛውንም ሥጋ ደም አትብሉ። ደም የሚበላ ማንኛውም ሰው ተለይቶ እንዲጠፋ ይደረጋል።”+ 15 የአገሬው ተወላጅም ይሁን የባዕድ አገር ሰው፣ ማንኛውም ሰው* ሞቶ የተገኘን ወይም አውሬ የቦጫጨቀውን እንስሳ+ ሥጋ ቢበላ ልብሶቹን ይጠብ፤ በውኃም ይታጠብ፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሁን፤+ ከዚያም ንጹሕ ይሆናል። 16 ሆኖም ልብሶቹን ካላጠበና ሰውነቱን ካልታጠበ በሠራው ጥፋት ይጠየቅበታል።’”+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ