የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መዝሙር 94
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

መዝሙር የመጽሐፉ ይዘት

      • አምላክ የበቀል እርምጃ እንዲወስድ የቀረበ ጸሎት

        • “ክፉዎች እስከ መቼ ድረስ ይፈነጥዛሉ?” (3)

        • ያህ የሚሰጠው እርማት ደስታ ያስገኛል (12)

        • ‘አምላክ ሕዝቡን አይጥልም’ (14)

        • ‘በሕግ ስም ችግር መፍጠር’ (20)

መዝሙር 94:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 32:35፤ ናሆም 1:2፤ ሮም 12:19

መዝሙር 94:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 18:25፤ ሥራ 17:31
  • +መዝ 31:23

መዝሙር 94:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 73:3፤ 74:10

መዝሙር 94:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 14:4

መዝሙር 94:6

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    1/1/1995፣ ገጽ 30

መዝሙር 94:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 59:2, 7፤ ሕዝ 8:12
  • +መዝ 10:4, 11፤ 73:3, 11፤ ኢሳ 29:15

መዝሙር 94:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 1:22

መዝሙር 94:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የተከለው።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 34:15

መዝሙር 94:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 9:5፤ ኢሳ 10:12
  • +መዝ 25:8፤ ኢሳ 28:26፤ ዮሐ 6:45

መዝሙር 94:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 3:20

መዝሙር 94:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 119:71፤ ምሳሌ 3:11፤ 1ቆሮ 11:32፤ ዕብ 12:5, 6
  • +መዝ 19:8

መዝሙር 94:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 55:23፤ 2ጴጥ 2:9

መዝሙር 94:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 12:22፤ መዝ 37:28፤ ዕብ 13:5
  • +ዘዳ 32:9

መዝሙር 94:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ነፍሴ በዝምታ በኖረች ነበር።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 124:2, 3፤ 2ቆሮ 1:10

መዝሙር 94:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 2:9፤ መዝ 37:24፤ 121:3፤ ሰቆ 3:22

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 8

መዝሙር 94:19

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “እረፍት የሚነሱ ሐሳቦች በውስጤ በበዙ ጊዜ።”

  • *

    ወይም “ማጽናኛዎችህ ነፍሴን አረጋጓት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 86:17፤ ፊልጵ 4:6, 7

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    1/2024፣ ገጽ 25

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው፣ ርዕስ 189

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 8

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/15/2006፣ ገጽ 13

    3/15/2003፣ ገጽ 9

    9/1/2001፣ ገጽ 16-17

መዝሙር 94:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ፈራጆች።” ቃል በቃል “ዙፋን።”

  • *

    ወይም “በአዋጅ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 10:1፤ ዳን 6:7፤ ሥራ 5:27, 28

መዝሙር 94:21

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በጻድቁ ነፍስ ላይ።”

  • *

    ቃል በቃል “የንጹሑንም ሰው ደም በደለኛ (ክፉ) ያደርጉታል።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 59:3
  • +1ነገ 21:13

መዝሙር 94:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 18:2

መዝሙር 94:23

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ጸጥ ያሰኛቸዋል።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 5:22፤ 2ተሰ 1:6
  • +1ሳሙ 26:9, 10

ተዛማጅ ሐሳብ

መዝ. 94:1ዘዳ 32:35፤ ናሆም 1:2፤ ሮም 12:19
መዝ. 94:2ዘፍ 18:25፤ ሥራ 17:31
መዝ. 94:2መዝ 31:23
መዝ. 94:3መዝ 73:3፤ 74:10
መዝ. 94:5መዝ 14:4
መዝ. 94:7መዝ 59:2, 7፤ ሕዝ 8:12
መዝ. 94:7መዝ 10:4, 11፤ 73:3, 11፤ ኢሳ 29:15
መዝ. 94:8ምሳሌ 1:22
መዝ. 94:9መዝ 34:15
መዝ. 94:10መዝ 9:5፤ ኢሳ 10:12
መዝ. 94:10መዝ 25:8፤ ኢሳ 28:26፤ ዮሐ 6:45
መዝ. 94:111ቆሮ 3:20
መዝ. 94:12መዝ 119:71፤ ምሳሌ 3:11፤ 1ቆሮ 11:32፤ ዕብ 12:5, 6
መዝ. 94:12መዝ 19:8
መዝ. 94:13መዝ 55:23፤ 2ጴጥ 2:9
መዝ. 94:141ሳሙ 12:22፤ መዝ 37:28፤ ዕብ 13:5
መዝ. 94:14ዘዳ 32:9
መዝ. 94:17መዝ 124:2, 3፤ 2ቆሮ 1:10
መዝ. 94:181ሳሙ 2:9፤ መዝ 37:24፤ 121:3፤ ሰቆ 3:22
መዝ. 94:19መዝ 86:17፤ ፊልጵ 4:6, 7
መዝ. 94:20ኢሳ 10:1፤ ዳን 6:7፤ ሥራ 5:27, 28
መዝ. 94:21መዝ 59:3
መዝ. 94:211ነገ 21:13
መዝ. 94:22መዝ 18:2
መዝ. 94:23ምሳሌ 5:22፤ 2ተሰ 1:6
መዝ. 94:231ሳሙ 26:9, 10
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
መዝሙር 94:1-23

መዝሙር

94 የበቀል አምላክ፣ ይሖዋ ሆይ፣+

የበቀል አምላክ ሆይ፣ ብርሃንህን አብራ!

 2 የምድር ፈራጅ ሆይ፣ ተነስ።+

ለትዕቢተኞች የሚገባቸውን ብድራት ክፈላቸው።+

 3 ክፉዎች እስከ መቼ፣ ይሖዋ ሆይ፣

ክፉዎች እስከ መቼ ድረስ ይፈነጥዛሉ?+

 4 ይለፈልፋሉ፤ በእብሪት ይናገራሉ፤

ክፉ አድራጊዎች ሁሉ ስለ ራሳቸው ጉራ ይነዛሉ።

 5 ይሖዋ ሆይ፣ ሕዝብህን ያደቃሉ፤+

ርስትህንም ይጨቁናሉ።

 6 መበለቲቱንና ባዕዱን ሰው ይገድላሉ፤

አባት የሌላቸውንም ልጆች ሕይወት ያጠፋሉ።

 7 “ያህ አያይም፤+

የያዕቆብ አምላክ አያስተውለውም” ይላሉ።+

 8 እናንተ ማመዛዘን የጎደላችሁ ሰዎች፣ ይህን ልብ በሉ፤

እናንተ ሞኞች፣ አስተዋዮች የምትሆኑት መቼ ነው?+

 9 ጆሮን ያበጀው* እሱ መስማት አይችልም?

ወይስ ዓይንን የሠራው እሱ ማየት አይችልም?+

10 ብሔራትን የሚያርመው እሱ መውቀስ አይችልም?+

ለሰዎች እውቀት የሚሰጠው እሱ ነው!+

11 ይሖዋ የሰዎችን ሐሳብ ያውቃል፤

ከንቱ እንደሆነም ይረዳል።+

12 ያህ ሆይ፣ አንተ የምታርመው፣+

ከሕግህ ላይ የምታስተምረው ሰው ደስተኛ ነው፤+

13 ይህም ለክፉዎች ጉድጓድ እስኪቆፈር ድረስ፣+

በመከራ ወቅት ለእሱ ሰላም ትሰጠው ዘንድ ነው።

14 ይሖዋ ሕዝቡን አይጥልምና፤+

ርስቱንም አይተውም።+

15 ፍርድ፣ ዳግመኛ ጽድቅ የሚንጸባረቅበት ይሆናልና፤

ልበ ቅን የሆኑ ሰዎችም ሁሉ ይከተሉታል።

16 ከክፉዎች ጋር የሚሟገትልኝ ማን ነው?

ክፉ አድራጊዎችን በመቃወም ከጎኔ የሚቆም ማን ነው?

17 ይሖዋ ረዳቴ ባይሆን ኖሮ፣

በአጭር ጊዜ ውስጥ በጠፋሁ ነበር።*+

18 “እግሬ አዳለጠኝ” ባልኩ ጊዜ፣

ይሖዋ ሆይ፣ ታማኝ ፍቅርህ ደገፈኝ።+

19 በጭንቀት በተዋጥኩ ጊዜ፣*

አጽናናኸኝ፤ ደግሞም አረጋጋኸኝ።*+

20 ምግባረ ብልሹ ገዢዎች* በሕግ ስም* ችግር ለመፍጠር እያሴሩ፣+

የአንተ ተባባሪ ሊሆኑ ይችላሉ?

21 በጻድቁ ላይ* ጭካኔ የተሞላበት ጥቃት ይሰነዝራሉ፤+

በንጹሕ ሰው ላይ ሞት ይፈርዳሉ።*+

22 ለእኔ ግን ይሖዋ አስተማማኝ መጠጊያ ይሆንልኛል፤

አምላኬ መጠጊያ ዓለቴ ነው።+

23 ክፉ ሥራቸውን በላያቸው ይመልሳል፤+

በገዛ ክፋታቸው ያጠፋቸዋል።*

ይሖዋ አምላካችን ያጠፋቸዋል።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ