የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ነገሥት 12
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

1 ነገሥት የመጽሐፉ ይዘት

      • ሮብዓም ለሕዝቡ የሰጠው መጥፎ ምላሽ (1-15)

      • አሥሩ ነገዶች ዓመፁ (16-19)

      • ኢዮርብዓም የእስራኤል ንጉሥ ሆነ (20)

      • ሮብዓም ከእስራኤላውያን ጋር እንዳይዋጋ ተነገረው (21-24)

      • ኢዮርብዓም ያቋቋመው የጥጃ አምልኮ (25-33)

1 ነገሥት 12:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 10:1-4
  • +ዘፍ 12:6፤ ኢያሱ 20:7, 9፤ መሳ 9:1, 2፤ ሥራ 7:15, 16

1 ነገሥት 12:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 11:26, 40

1 ነገሥት 12:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ጨቋኝ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 8:11-18፤ 1ነገ 4:7

1 ነገሥት 12:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 10:5-7

1 ነገሥት 12:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 10:8-11

1 ነገሥት 12:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 10:12-15

1 ነገሥት 12:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 11:31
  • +ዘዳ 2:30፤ 2ዜና 22:7፤ ሮም 9:18

1 ነገሥት 12:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ወደየድንኳናቸው።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 10:16, 17

1 ነገሥት 12:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 11:12, 13፤ 2ዜና 11:13, 16

1 ነገሥት 12:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 20:24፤ 1ነገ 4:6፤ 5:13, 14
  • +2ዜና 10:18, 19

1 ነገሥት 12:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 17:21

1 ነገሥት 12:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 11:30, 31
  • +1ነገ 11:12, 13፤ ሆሴዕ 11:12

1 ነገሥት 12:21

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የተመረጡ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 11:1-4፤ 25:5

1 ነገሥት 12:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 12:5

1 ነገሥት 12:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 11:30, 31

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    6/2018፣ ገጽ 13-14

1 ነገሥት 12:25

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ምሽግ አድርጎ በመሥራት።”

  • *

    ወይም “ምሽግ አድርጎ ሠራ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 12:1
  • +ዘፍ 32:30፤ መሳ 8:13, 17

1 ነገሥት 12:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 11:38

1 ነገሥት 12:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 12:5, 6

1 ነገሥት 12:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 20:4፤ 2ነገ 10:29
  • +ዘፀ 32:4, 8፤ 2ዜና 11:15, 16

1 ነገሥት 12:29

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 12:8, 9፤ 28:19
  • +ዘፍ 14:14፤ ዘዳ 34:1፤ መሳ 18:29፤ 20:1

1 ነገሥት 12:30

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 10:31፤ 17:21-23

1 ነገሥት 12:31

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 3:10፤ 1ነገ 13:33፤ 2ዜና 11:14፤ 13:9

1 ነገሥት 12:32

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 23:34
  • +አሞጽ 7:13

ተዛማጅ ሐሳብ

1 ነገ. 12:12ዜና 10:1-4
1 ነገ. 12:1ዘፍ 12:6፤ ኢያሱ 20:7, 9፤ መሳ 9:1, 2፤ ሥራ 7:15, 16
1 ነገ. 12:21ነገ 11:26, 40
1 ነገ. 12:41ሳሙ 8:11-18፤ 1ነገ 4:7
1 ነገ. 12:52ዜና 10:5-7
1 ነገ. 12:82ዜና 10:8-11
1 ነገ. 12:122ዜና 10:12-15
1 ነገ. 12:151ነገ 11:31
1 ነገ. 12:15ዘዳ 2:30፤ 2ዜና 22:7፤ ሮም 9:18
1 ነገ. 12:162ዜና 10:16, 17
1 ነገ. 12:171ነገ 11:12, 13፤ 2ዜና 11:13, 16
1 ነገ. 12:182ሳሙ 20:24፤ 1ነገ 4:6፤ 5:13, 14
1 ነገ. 12:182ዜና 10:18, 19
1 ነገ. 12:192ነገ 17:21
1 ነገ. 12:201ነገ 11:30, 31
1 ነገ. 12:201ነገ 11:12, 13፤ ሆሴዕ 11:12
1 ነገ. 12:212ዜና 11:1-4፤ 25:5
1 ነገ. 12:222ዜና 12:5
1 ነገ. 12:241ነገ 11:30, 31
1 ነገ. 12:251ነገ 12:1
1 ነገ. 12:25ዘፍ 32:30፤ መሳ 8:13, 17
1 ነገ. 12:261ነገ 11:38
1 ነገ. 12:27ዘዳ 12:5, 6
1 ነገ. 12:28ዘፀ 20:4፤ 2ነገ 10:29
1 ነገ. 12:28ዘፀ 32:4, 8፤ 2ዜና 11:15, 16
1 ነገ. 12:29ዘፍ 12:8, 9፤ 28:19
1 ነገ. 12:29ዘፍ 14:14፤ ዘዳ 34:1፤ መሳ 18:29፤ 20:1
1 ነገ. 12:302ነገ 10:31፤ 17:21-23
1 ነገ. 12:31ዘኁ 3:10፤ 1ነገ 13:33፤ 2ዜና 11:14፤ 13:9
1 ነገ. 12:32ዘሌ 23:34
1 ነገ. 12:32አሞጽ 7:13
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
  • 32
  • 33
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
1 ነገሥት 12:1-33

አንደኛ ነገሥት

12 ሮብዓም እስራኤላውያን በሙሉ ሊያነግሡት+ ወደ ሴኬም+ መጥተው ስለነበር እሱም ወደ ሴኬም ሄደ። 2 የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም ይህን እንደሰማ (ምክንያቱም ኢዮርብዓም ከንጉሥ ሰለሞን ሸሽቶ በግብፅ ይኖር ስለነበር በወቅቱ በዚያ ይገኝ ነበር)፣+ 3 ልከው አስጠሩት። ከዚያም ኢዮርብዓምና መላው የእስራኤል ጉባኤ መጥተው ሮብዓምን እንዲህ አሉት፦ 4 “አባትህ ቀንበራችንን አክብዶብን ነበር።+ አንተ ግን አባትህ የሰጠንን አስቸጋሪ ሥራና በላያችን የጫነብንን ከባድ* ቀንበር የምታቀልልን ከሆነ እናገለግልሃለን።”

5 በዚህ ጊዜ “እንግዲያው ሂዱና ከሦስት ቀን በኋላ ተመልሳችሁ ኑ” አላቸው። በመሆኑም ሕዝቡ ሄደ።+ 6 ከዚያም ንጉሥ ሮብዓም አባቱ ሰለሞን በሕይወት በነበረበት ጊዜ ሲያገለግሉት የነበሩትን ሽማግሌዎች “ለዚህ ሕዝብ ምን ምላሽ እንድሰጥ ትመክሩኛላችሁ?” በማለት ምክር ጠየቀ። 7 እነሱም “ዛሬ አንተ የዚህ ሕዝብ አገልጋይ ብትሆንና የጠየቁህን ብትፈጽምላቸው እንዲሁም መልካም ምላሽ ብትሰጣቸው ምንጊዜም አገልጋዮችህ ይሆናሉ” በማለት መለሱለት።

8 ሆኖም ሮብዓም ሽማግሌዎቹ የሰጡትን ምክር ትቶ አብሮ አደጎቹ ከነበሩትና አሁን የእሱ አገልጋዮች ከሆኑት ወጣቶች ጋር ተማከረ።+ 9 እሱም እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፦ “‘አባትህ የጫነብንን ቀንበር አቅልልልን’ ለሚለኝ ለዚህ ሕዝብ ምን ምላሽ እንድንሰጥ ትመክሩኛላችሁ?” 10 አብሮ አደጎቹ የሆኑት ወጣቶችም እንዲህ አሉት፦ “‘አባትህ ቀንበራችንን አክብዶብን ነበር፤ አንተ ግን ቀንበራችንን አቅልልልን’ ለሚልህ ለዚህ ሕዝብ እንዲህ በለው፦ ‘ትንሿ ጣቴ ከአባቴ ወገብ ትወፍራለች። 11 አባቴ ከባድ ቀንበር ጭኖባችሁ ነበር፤ እኔ ግን ቀንበራችሁን የባሰ አከብደዋለሁ። አባቴ በአለንጋ ገርፏችሁ ነበር፤ እኔ ግን በእሾህ አለንጋ እገርፋችኋለሁ።’”

12 ኢዮርብዓምና መላው ሕዝብ ንጉሡ “በሦስተኛው ቀን ተመልሳችሁ ኑ” ባላቸው መሠረት በሦስተኛው ቀን ወደ ሮብዓም መጡ።+ 13 ንጉሡ ግን ሽማግሌዎቹ የሰጡትን ምክር ትቶ ለሕዝቡ መጥፎ ምላሽ ሰጠ። 14 ወጣቶቹም በሰጡት ምክር መሠረት “አባቴ ቀንበራችሁን አክብዶባችሁ ነበር፤ እኔ ግን ቀንበራችሁን የባሰ አከብደዋለሁ። አባቴ በአለንጋ ገርፏችሁ ነበር፤ እኔ ግን በእሾህ አለንጋ እገርፋችኋለሁ” አላቸው። 15 በመሆኑም ንጉሡ ሕዝቡን ሳይሰማ ቀረ፤ ይህም የሆነው ይሖዋ በሴሎናዊው በአኪያህ+ አማካኝነት ለናባጥ ልጅ ለኢዮርብዓም የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ ይሖዋ እነዚህ ነገሮች በዚህ መንገድ እንዲከናወኑ ስላደረገ ነው።+

16 እስራኤላውያን ሁሉ ንጉሡ ሊሰማቸው ፈቃደኛ አለመሆኑን ሲያዩ ንጉሡን እንዲህ አሉት፦ “ከዳዊት ምን ድርሻ አለን? ከእሴይ ልጅ ምንም ርስት የለንም። እስራኤል ሆይ፣ ወደ አማልክትህ ተመለስ። ዳዊት ሆይ፣ እንግዲህ የገዛ ቤትህን ጠብቅ!” ከዚያም እስራኤላውያን ወደየቤታቸው* ተመለሱ።+ 17 ይሁንና ሮብዓም በይሁዳ ከተሞች በሚኖሩት እስራኤላውያን ላይ መግዛቱን ቀጠለ።+

18 ከዚያም ንጉሥ ሮብዓም የግዳጅ ሥራ እንዲሠሩ የተመለመሉት ሰዎች አለቃ የነበረውን አዶራምን+ ላከው፤ ሆኖም እስራኤላውያን በሙሉ በድንጋይ ወግረው ገደሉት። ንጉሥ ሮብዓም ግን እንደ ምንም ብሎ ሠረገላው ላይ በመውጣት ወደ ኢየሩሳሌም ሸሸ።+ 19 እስራኤላውያንም እስከዚህ ቀን ድረስ በዳዊት ቤት ላይ እንዳመፁ+ ናቸው።

20 እስራኤላውያን በሙሉ ኢዮርብዓም መመለሱን እንደሰሙ ወደ ማኅበረሰቡ ካስጠሩት በኋላ በመላው እስራኤል ላይ አነገሡት።+ ከይሁዳ ነገድ በስተቀር ከሕዝቡ መሃል የዳዊትን ቤት የተከተለ ማንም አልነበረም።+

21 ሮብዓም ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ከእስራኤል ቤት ጋር ተዋግተው ንግሥናውን ለሰለሞን ልጅ ለሮብዓም እንዲያስመልሱ ከመላው የይሁዳ ቤትና ከቢንያም ነገድ የተውጣጡ 180,000 የሠለጠኑ* ተዋጊዎች ወዲያውኑ ሰበሰበ።+ 22 ከዚያም የእውነተኛው አምላክ ቃል የእውነተኛው አምላክ ሰው ወደሆነው ወደ ሸማያህ+ እንዲህ ሲል መጣ፦ 23 “ለይሁዳ ንጉሥ ለሰለሞን ልጅ ለሮብዓም፣ ለይሁዳ ቤት ሁሉ፣ ለቢንያምና ለቀረው ሕዝብ እንዲህ ብለህ ተናገር፦ 24 ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ከወንድሞቻችሁ ከእስራኤላውያን ጋር ለመዋጋት አትውጡ። ይህ እንዲሆን ያደረግኩት እኔ ስለሆንኩ እያንዳንዳችሁ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ።”’”+ ስለዚህ የይሖዋን ቃል ሰሙ፤ ይሖዋ እንደነገራቸውም ወደየቤታቸው ተመለሱ።

25 ከዚያም ኢዮርብዓም በኤፍሬም ተራራማ አካባቢ ሴኬምን+ ገንብቶ* በዚያ መኖር ጀመረ። ከዚያ ወጥቶ በመሄድ ጰኑኤልን+ ገነባ።* 26 ኢዮርብዓም በልቡ እንዲህ ሲል አሰበ፦ “እንግዲህ አሁን መንግሥቱ ወደ ዳዊት ቤት ይመለሳል።+ 27 ይህ ሕዝብ በኢየሩሳሌም በሚገኘው የይሖዋ ቤት+ መሥዋዕት ለማቅረብ ወደዚያ መውጣቱን ከቀጠለ የዚህ ሕዝብ ልብ ጌታው ወደሆነው ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሮብዓም ይመለሳል። እኔንም ይገድለኛል፤ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሮብዓምም ይመለሳል።” 28 በመሆኑም ንጉሡ ከተማከረ በኋላ ሁለት የወርቅ ጥጃዎችን+ ሠርቶ ሕዝቡን “ወደ ኢየሩሳሌም መውጣት መንገላታት ይሆንባችኋል። እስራኤል ሆይ፣ ከግብፅ ምድር ያወጣህ አምላክህ ይኸውልህ” አለ።+ 29 ከዚያም አንደኛውን በቤቴል+ ሌላኛውን ደግሞ በዳን+ አቆመው። 30 ይህም ለኃጢአት ዳረጋቸው፤+ ሕዝቡም በዳን የሚገኘውን ጥጃ ለማምለክ እስከዚያ ድረስ ይሄድ ነበር።

31 እሱም በኮረብቶቹ ላይ የአምልኮ ቤቶችን ሠራ፤ ከሕዝቡም መካከል ሌዋውያን ያልሆኑ ሰዎችን ካህናት አድርጎ ሾመ።+ 32 በተጨማሪም ኢዮርብዓም በስምንተኛው ወር ከወሩም በ15ኛው ቀን በይሁዳ ይከበር የነበረው ዓይነት በዓል እንዲቋቋም አደረገ።+ ለሠራቸውም ጥጆች በቤቴል+ በሠራው መሠዊያ ላይ መሥዋዕት አቀረበ፤ በቤቴል ለሠራቸው ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎችም ካህናት መደበ። 33 በቤቴል በሠራው መሠዊያም ላይ ራሱ በመረጠው ወር ይኸውም በስምንተኛው ወር በ15ኛው ቀን መባዎችን ማቅረብ ጀመረ፤ ለእስራኤል ሰዎችም በዓል አቋቋመ፤ እንዲሁም መባዎችንና የሚጨሱ መሥዋዕቶችን ለማቅረብ ወደ መሠዊያው ወጣ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ