የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g97 10/8 ገጽ 9
  • ልጆቻችሁ ቢነወሩ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ልጆቻችሁ ቢነወሩ
  • ንቁ!—1997
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ልጆቻችሁን ከጥቃት መጠበቅ የምትችሉት እንዴት ነው?
    ንቁ!—2007
  • ፍቅርና ፍትሕ—ክፋት በሞላበት ዓለም ውስጥ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2019
  • በሕፃናት ላይ የሚፈጸም ወሲባዊ በደል የሚያስከትለው ስውር ቁስል
    ንቁ!—1999
  • በቤት ውስጥ እንዳይከሰት መከላከል
    ንቁ!—1997
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—1997
g97 10/8 ገጽ 9

ልጆቻችሁ ቢነወሩ

በልጆቻችሁ ላይ የሚፈጸመውን የማስነወር ወንጀል መግታት እንድትችሉ ምልክቶቹን ማወቅ ይኖርባችኋል። የሙያው ጠበብት በጉዳዩ ላይ ሰፊ ትንተና በሰጡባቸው በርካታ መጻሕፍት ላይ ወላጆች ልጆቻቸው በጾታ እንደተነወሩ ማወቅ የሚችሉባቸውን ብዙ ምልክቶች ዘርዝረዋል። ከእነዚህም መካከል አንዳንዶቹ የሚከተሉት ናቸው:- በሚሸኑበትና በሚጸዳዱበት ጊዜ የሕመም ስሜት እንደሚሰማቸው የሚናገሩ ከሆነ፣ የአባለዘር ኢንፌክሽን፣ በአባላዘር አካባቢ የቆዳ መፈግፈግ ወይም መቁሰል፣ መኝታ ላይ መሽናት፣ የምግብ ፍላጎት ማጣት ወይም ሌሎች ከአመጋገብ ጋር የተያያዙ ችግሮች፣ ከዕድሜያቸው በላይ የሆነ ከጾታ ስሜት ጋር የተያያዘ ጠባይ ማሳየት፣ እንደ ትምህርት ቤት ባሉ ቦታዎች ወይም ደግሞ እቤታቸው ውስጥ የሆነ ክፍል ውስጥ ሲገቡ ድንገት ፍርሃት የሚያድርባቸው ከሆነ፣ በአንዳንድ ወቅቶች ላይ ከፍተኛ የመሸበር ስሜት መታየት፣ ልብስ ለማውለቅ መፍራት፣ ከሚያውቁት ሰው ጋር ብቻቸውን ሲሆኑ መፍራት እና ሆን ብሎ የራስን አካል መጉዳት።

ሆኖም እነዚህን ምልክቶች ብታዩ እንኳ በጾታ እንደተነወሩ አድርጋችሁ ለመደምደም አትቸኩሉ። አብዛኞቹ ምልክቶች በራሳቸው ብቻ ልጁ ወይም ልጅቷ በጾታ ተነውረዋል ብሎ ለመደምደም የሚያስችሉ አይደሉም። እያንዳንዱ ምልክት ሌላ ችግር የሚያመለክት ሊሆን ይችላል። ሆኖም የሚረብሹ ምልክቶች ከተመለከታችሁ ቀስ ብላችሁ ጉዳዩን አንሱባቸው፤ ምናልባት ውይይቱን እንዲህ ብላችሁ ልትጀምሩ ትችላላችሁ:- “በማትፈልጊው ሁኔታ የሚነካካሽ ሰው ካለ ንገሪኝ እሺ፤ አንቺን ለመጠበቅ የምችለውን ሁሉ አደርጋለሁ። ከዚህ በፊት እንዲህ ዓይነት ነገር አጋጥሞሽ ያውቃል እንዴ?”—ምሳሌ 20:5

ልጃችሁ በጾታ የማስነወር ወንጀል እንደተፈጸመባት ከነገረቻችሁ ቅስማችሁ እንደሚሰበር የታወቀ ነው። ሆኖም ልጃችሁ ማገገም የምትችልበት ሁኔታ በአብዛኛው የተመካው እናንተ በምታሳዩት ምላሽ ላይ እንደሆነ መዘንጋት የለባችሁም። ልጃችሁ ከአቅሟ በላይ የሆነ ሸክም የወደቀባት በመሆኑ አዋቂ እንደመሆናችሁ መጠን ባላችሁ ጉልበት ሁሉ ተጠቅማችሁ ሸክሙን ከጫንቃዋ ላይ እንድታነሡላት ትፈልጋለች። የተፈጸመባትን ሁኔታ ደፍራ በመናገሯ በጣም አመስግኗት። ከለላ ለመሆን የተቻላችሁን ሁሉ እንደምታደርጉ፣ ጥፋቱ የእሷ ሳይሆን ድርጊቱን የፈጸመው ሰው መሆኑን፣ እሷ “መጥፎ” እንዳልሆነችና በጣም እንደምትወዷት ደጋግማችሁ ንገሯት።

አንዳንድ የሕግ ባለሙያዎች የተፈጸመውን የማስነወር ወንጀል በተቻለ መጠን በፍጥነት ለሚመለከተው የሕግ ክፍል ማሳወቅ ጥሩ እንደሆነ ይናገራሉ። በአንዳንድ አገሮች የሕጉ አሠራር ራሱ እንዲህ ለማድረግ የሚያበረታታ ነው። ሆኖም በሌሎች ቦታዎች የሕጉ አሠራር በዚህ በኩል ብዙም የማይረዳ ሊሆን ይችላል።

ይሁን እንጂ ወንጀሉን የፈጸመው በጣም የምትወዱት የራሳችሁ የትዳር ጓደኛ ቢሆንስ? በጣም የሚያሳዝነው፣ ብዙ ሴቶች ቆራጥ አቋም መውሰድ ሲሳናቸው ይታያል። እርግጥ፣ ልጁን ወይም ልጅቷን ያስነወረው የገዛ ራሳችን የትዳር ጓደኛ ነው ብሎ ማመን በጣም የሚከብድ ነገር ነው። ስሜታዊው ትስስር በጣም የጠበቀ ሊሆን ይችላል፤ አልፎ ተርፎም ገንዘብ ነክ በሆኑ ጉዳዮች በጣም የተሳሰራችሁ ልትሆኑ ትችላላችሁ። በተጨማሪም በደሉ የደረሰባት ሚስት እርምጃ መውሰዷ ባሏ፣ ቤተሰቡንና ሥራውን ሊያሳጣውና ስሙን ሊያጎድፍበት እንደሚችል ትገነዘብ ይሆናል።a ሆኖም ግለሰቡ ራሱ የዘራውን መልሶ እያጨደ ሊሆን ይችላል። (ገላትያ 6:7) በሌላ በኩል ግን ምንም የማያውቁት ምስኪኖቹ ልጆች የተናገሩትን የማታምኗቸውና ከለላ የማትሆኗቸው ከሆነ የከፋ ጉዳት ሊደርስባቸው ይችላል። የወደፊት ሕይወታቸው በሙሉ አደጋ ላይ ይወድቃል። ልጆች እንደ አዋቂዎች ችግሮችን በራሳቸው የመፍታት አቅምም ሆነ ችሎታ የላቸውም። የደረሰባቸው የሥነ ልቦና ቀውስ የማይሽር ቁስል ሊተውባቸውና ሕይወታቸውን ሊያበላሸው ይችላል። በርኅራኄ መያዝ የሚያስፈልጋቸውና የሚገባቸው እነሱ ናቸው።—ከዘፍጥረት 33:13, 14 ጋር አወዳድር።

ስለዚህ ወላጆች ልጆቻቸውን ለመጠበቅ አስፈላጊ የሆነውን እርምጃ ሁሉ መውሰድ አለባቸው! ብዙ አስተዋይ የሆኑ ወላጆች በጾታ የተነወሩ ልጆቻቸው ሙያዊ እርዳታ እንዲያገኙ ያደርጋሉ። ሐኪም ፊት በምትቀርቡበት ጊዜ እንደምታደርጉት ሁሉ ለልጃችሁ እንዲህ ዓይነት ሙያዊ እርዳታ የሚሰጠው ባለሙያም ሃይማኖታዊ አመለካከታችሁን እንዲያከብርላችሁ አድርጉ።b ወላጃዊ ፍቅራችሁን ሁልጊዜ በመግለጽ ልጆቻችሁ አጥተውት የነበረውን በራስ የመተማመን መንፈስ መልሰው እንዲያገኙ እርዷቸው።

[የግርጌ ማስታወሻ]

a እንዲያውም ወሲባዊ ጥቃቱን የፈጸመው ሰው ራሱ ቀድሞውኑ ችግር ውስጥ የገባ በመሆኑ በእጅጉ እርዳታ ያስፈልገዋል። ግለሰቡ ይቅርታ ቢጠይቅም እንኳ ተበዳይዋ ሚስት ‘የድርጊቱ ሰለባ የሆነው ልጅ ድርጊቱን ከማጋለጡ በፊት ለምን ይቅርታ አልጠየቀም ነበር?’ ብላ ራሷን ልትጠይቅ ትችላለች።

b ለምሳሌ ያህል የይሖዋ ምሥክሮች ደም በደም ሥር የመውሰድ ጥያቄ በሚነሳበት ጊዜ ዶክተሩ ሃይማኖታዊ እምነታቸውን እንዲያከብርላቸው ያደርጋሉ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ