ገጽ 2
ተላላፊ በሽታ ይወገድ ይሆን? 3-10
በሕክምናም ሆነ በሳይንስ መስክ ብዙ ዕድገቶች የታዩ ቢሆንም ወረርሽኞችና ሌሎች በሽታዎች እየተበራከቱ መጥተዋል። በዚህ በ20ኛው መቶ ዘመን የተከሰቱት ወረርሽኝ በሽታዎች ስለ ጊዜያችን የተነገሩት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትንቢቶች ፍጻሜ ናቸውን? ወደፊት ሕመም የሌለበት ዓለም ማየት እንችል ይሆን?
ጤንነትህን መጠበቅ የምትችልባቸው ስድስት መንገዶች 11
እራስዎንም ሆነ ቤተሰብዎን የጤንነት መታወክ ሊያስከትሉ ከሚችሉ ጀርሞች ለመጠበቅ መውሰድ ስለሚገባዎት ስድስት እርምጃዎች ያንብቡ።
በጎዳና ላይ የሚያጋጥም ግልፍተኝነትን እንዴት መቋቋም ይቻላል? 13
ስሜትን መቆጣጠር አለመቻልና በዚሁ ሳቢያ የሚፈጸመው የኃይል ድርጊት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል። በጎዳና ላይ ከሚያጋጥም ግልፍተኝነት ራስዎን ለመጠበቅ ምን ሊያደርጉ ይችላሉ?