የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g98 8/8 ገጽ 32
  • በአምላክ ያላመነችው ለምን ነበር?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በአምላክ ያላመነችው ለምን ነበር?
  • ንቁ!—1998
ንቁ!—1998
g98 8/8 ገጽ 32

በአምላክ ያላመነችው ለምን ነበር?

የቀድሞዋ ሶቪየት ሕብረት ክፍል በነበረችው በጆርጂያ ሪፓብሊክ፣ በሩስታቪ ከተማ ትኖር የነበረችው ኦሌዚያ የምትባል አንዲት ወጣት እቤቷ መጥተው ለነበሩ ሁለት ሰዎች የወላጆቿን ፎቶ አሳየቻቸውና “አምላክ ቢኖር ኖሮ ወላጆቼ ገና ወጣት ሳሉ እንዲሞቱ አያደርግም ነበር” አለች። የኦሌዚያ ባለቤት ቶማዜ እቤት ሲመጣ ሰዎቹ በምድር ላይ በደስታ ለዘላለም ኑር! እና “እነሆ! ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ” የተባሉትን ብሮሹሮች ሰጥተዋቸው ሄዱ።

ለባልና ሚስቱ ተመላልሶ መጠየቅ በተደረገላቸው ጊዜ ኦሌዚያ “እነሆ!” የተባለውን ብሮሹር አንብባ ጨርሳ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ ለማጥናት ፍላጎት አደረባት። ያነበበችው ነገር አስደስቷት ነበር። መወያየት እንደጀመሩ ብሮሹሩን ገለጠችና ምልክት አድርጋባቸው የነበሩትን ክፍሎች ማንበብ ጀመረች። ልቧ በቀረቡት ምክንያታዊ ማብራሪያዎች በጣም ተነክቶ ነበር።

ለምሳሌ ያህል ብሮሹሩ እንዲህ ይላል:- “አበቦች፣ ወፎች፣ እንስሳት፣ አስገራሚ ፍጥረት የሆነው ሰው፣ የሕይወትና የመወለድ ተአምር በአጠቃላይ በዙሪያችን ያሉት አስደናቂ ነገሮች በሙሉ እነሱን ስለ ፈጠረው በዓይን የማይታይ ታላቅ ጠቢብ የሚመሠክሩ ናቸው። (ሮሜ 1:20) የማሰብ ችሎታ ካለ አእምሮ አለ። አእምሮ ካለ ደግሞ አንድ ሕያው አካል አለ። እንግዲያው የዚህ ታላቅ አእምሮ ባለቤት የሁሉም ነገሮች ፈጣሪና የሕይወት ሁሉ ምንጭና የሁሉ የበላይ የሆነው ሕያው አካል ነው። (መዝሙር 36:9) ፈጣሪ በእርግጥም ሊወደስና ሊመለክ ይገባል።—መዝሙር 104:24፤ ራእይ 4:11”

ኦሌዚያ መጽሐፍ ቅዱስ እንድታጠና ያነሳሳት አምላክ በሞት የተለዩንን የምናፈቅራቸውን ሰዎች ከሞት እንደሚያስነሳ የገባው ቃል እንደሆነ ቆየት ብላ ተናግራለች። እርስዎም በእነዚህ ብሮሹሮች ውስጥ ከሚገኙት እምነት የሚያጠናክሩ መረጃዎች ጥቅም ያገኛሉ ብለን እናምናለን። በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር! እና “እነሆ! ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ” የተሰኙትን ብሮሹሮች ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ ወይም አንድ የይሖዋ ምሥክር መጥቶ እንዲያነጋግርዎትና መጽሐፍ ቅዱስን በነፃ እንዲያስተምርዎ የሚፈልጉ ከሆነ የይሖዋ ምሥክሮች፣ ፖ.ሣ.ቁ. 5522፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ወይም በገጽ 5 ላይ ከተዘረዘሩት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው ይጻፉ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ