“በሰላምና በስምምነት የሚኖር ዓለም”
ይህ ሊሆን ይችላል ብለው ያምናሉ? በዩ ኤስ ኤ ፍሎሪዳ ውስጥ የምትኖር አንዲት ሴት እንዲህ ስትል ጽፋለች:- “ሰዎች ሁሉ እርስ በርሳቸው የሚዋደዱበት ጊዜ ይመጣ ይሆን? የተባለው ትራክታችሁ እስከ ዛሬ ካነበብኳቸው እጅግ ኃይለኛ የሆነ የተስፋ መልእክት ያዘሉ ጽሑፎች ውስጥ አንዱ ነው። ደግሜ ደጋግሜ አንብቤዋለሁ። በሰላምና በስምምነት ስለሚኖር ዓለም የሚናገረውን አስደሳች ሐሳብ ባነበብኩ ቁጥር እፈነድቃለሁ።”
የሰው ዘር ዓለም ሰላምና ስምምነት በሰፈነበት ሁኔታ ሊኖር እንደሚችል ደግሞም እንደሚኖር የሚያሳይ ማስረጃ ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ የይሖዋ ምሥክሮች፣ ፖ. ሣ. ቁ. 5522፣ አዲስ አበባ ብለው ወይም በገጽ 5 ላይ ካሉት አድራሻዎች አመቺ ወደ ሆነው ይጻፉ። አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን? የተባለ ባለ 32 ገጽ ብሮሹር ይላክልዎታል። “አምላክ የሚያመጣው ግሩም የሆነ አዲስ ዓለም” የሚል ርዕስ ያለው 10ኛው ክፍል እንደሚያስደስትዎ እናምናለን።