የቤተሰብዎን ሕይወት ሊያሻሽለው ይችላል
ከ12 እስከ 22 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ አራት ልጆች ያሏት አንዲት እናት እንዲህ ስትል ጽፋለች:- “በዚህ መጽሐፍ በመታገዝ የቤተሰብ ሕይወታቸውን በአዲስ መልክ መጀመር ቢችሉ ደስ የሚላቸው ብዙ ቤተሰቦች እንደሚኖሩ ይሰማኛል።” ሴትዮዋ ይህን ያለችው ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ አስመልክታ ስትናገር ነው።
ይህች በኒው ዚላንድ የምትኖረው 49 ዓመት ዕድሜ ያላት የልጆች እናት ይህን መጽሐፍ በተመለከተ እንዲህ ብላለች:- “በእርግጥም መጽሐፉ ጥልቀት ያለውና ቤተሰብ ነክ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ ማስተዋል የተንጸባረቀበት ነው።”
የቤተሰብ ደስታ የተባለው መጽሐፍ ሁሉንም የቤተሰብ አባላት ማለትም ባሎችን፣ ሚስቶችን፣ ወላጆችን፣ ልጆችንና አያቶችን ሊጠቅም ይችላል። ትምህርት ሰጪ ከሆኑት ምዕራፎቹ መካከል “የተሳካ ትዳር ለመመሥረት መዘጋጀት፣” “ቤተሰባችሁን ማስተዳደር የምትችሉት እንዴት ነው?፣” “ቤተሰብን የሚያናጉ ችግሮችን መቋቋም ትችላላችሁ፣” እና “በእርጅና ዘመንም ተደጋግፎ መኖር” የሚሉት ይገኙበታል።
የግል ቅጂ ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ እባክዎ በዚህ ገጽ ላይ ያለውን ኩፖን ሞልተው ይላኩ። ችግሮችን ለመፍታትና ፈጣሪ ለቤተሰብ በነበረው ዓላማ መሠረት የቤተሰብን ሕይወት አስደሳች ለማድረግ የሚረዱ አንዳንድ ሐሳቦችን ማግኘት ይችላሉ።
□ ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ላኩልኝ።
□ መጽሐፍ ቅዱስ መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።