ገጽ ሁለት
አኗኗርህ ወደ ሞት አፋፍ እየመራህ ነውን? 3-11
በመልካም ሁኔታ ላይ የሚገኝ አካላዊ፣ አእምሯዊና መንፈሳዊ ጤና አስደሳችና ረጅም ለሆነ ሕይወት መሠረት ሊሆን ይችላል። አኗኗርህ ምን ዓይነት ተጽዕኖ እያሳደረብህ ነው?
ፀሐይ አፍቃሪዎች—ለቆዳችሁ ጥንቃቄ አድርጉ! 18
ቆዳ ሰውነትን ከጉዳት የሚጠብቅ ጥንቃቄ ሊደረግለት የሚገባ እጅግ አስፈላጊ የሆነ አባላካል ነው። ይህ የሆነበትን ምክንያትና በፀሐይ ረገድ ሊወሰድ የሚገባውን ጥንቃቄ ተመልከት።
ከሳንባ ነቀርሳ ጋር ለሚደረገው ፍልሚያ የተቀየሰ አዲስ ስልት 23
በዓለም ዙሪያ ሳንባ ነቀርሳ ሕይወታቸውን የሚቀጥፈው ሰዎች ቁጥር ኤድስ፣ ወባ እና የቆላ በሽታዎች በአንድ ላይ ተዳምረው ከሚፈጁዋቸው ሰዎች ቁጥር ይበልጣል። ይሁን እንጂ ተመራማሪዎች የተስፋ ጭላንጭል እየታያቸው ነው። ለምን?
[በገጽ 2 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]
Photo: WHO/Thierry Falise