የሕፃን ልጅ ሞት የሚያስከትለውን ሐዘን መቋቋም
በብሪታንያ የምትኖር አንዲት እናት የምትወዱት ሰው ሲሞት ለተባለው ብሮሹር ያላትን አድናቆት ለመግለጽ ደብዳቤ ጽፋለች። “ብሮሹሩ ለቤተሰባችን በተገቢው ሰዓት የቀረበ ምግብ ነው።” ከዚያም እንዲህ ስትል ገልጻለች:-
“ብሮሹሩ ላይ የቀረቡት ተሞክሮዎች እኛ ከደረሰብን ሁኔታ ጋር ሊመሳሰሉ የሚችሉ ናቸው። ሌሎች እኛ የተሰማን ዓይነት ስሜት ተሰምቷቸው እንደነበረና እንደሚሰማቸውም ማወቅ በጣም የሚያጽናና ነው።
“በተለይ ደግሞ ውርጃ ከሞት ተለይቶ እንደማይታይና ሐዘን እንደሚያስከትል የሚገልጸውን ክፍል ጠቃሚ ሆኖ አግኝቸዋለሁ። ሕፃኑ ከማኅፀን ውጪ በሕይወት ስላልኖረና ስብዕና ያለው ልጅ ሆኖ ስላላዩት ብዙዎች ውርጃ የሚያስከትለውን ሐዘን አይረዱም።
“በእኔ ላይ የደረሱት የተለመዱ ዓይነት ውርጃዎች አይደሉም ... በሁለቱም ጊዜያት ምጥ ይዞኝ የነበረ ሲሆን የተገላገልኩት ግን የሞቱ ሕፃናትን ነበር። ቬሮኒካ (በብሮሹሩ 10ኛ ገጽ ላይ) ‘ለአንዲት እናት የሞተ ሕፃን መውለድ በጣም የሚያሳዝን ነገር ነው’ በማለት የተናገረቻቸውን ቃላት እኔም ደግሜ መናገር እፈልጋለሁ።”
ምናልባትም እርስዎም ሆኑ አንድ የሚያውቁት ሰው ይህን ከፍተኛ አድናቆት የተቸረው ባለ 32 ገጽ ብሮሹር በማንበብ ማጽናኛ ማግኘት ይችሉ ይሆናል። ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ አለዚያም ደግሞ በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው በመላክ የምትወዱት ሰው ሲሞት የተባለውን ብሮሹር ማግኘት ይችላሉ።
□ የምትወዱት ሰው ሲሞት የተባለውን ብሮሹር ማግኘት እፈልጋለሁ።
□ መጽሐፍ ቅዱስ መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።