የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 2/14 ገጽ 3
  • ከዓለም አካባቢ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከዓለም አካባቢ
  • ንቁ!—2014
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ዩናይትድ ስቴትስ
  • ጣሊያን
  • ማሌዥያ
  • አፍሪካ
  • አውስትራሊያ
  • ተላላፊ በሽታዎች አደገኛ ቢሆኑም መከላከል ይቻላል
    ንቁ!—2001
  • ቁማር መጫወት ምን ስህተት አለው?
    ንቁ!—2002
  • በ20ኛው መቶ ዘመን የተከሰተ ወረርሽኝ
    ንቁ!—1998
  • ትንቢት 3. በሽታ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2014
g 2/14 ገጽ 3

ከዓለም አካባቢ

ዩናይትድ ስቴትስ

“አንድ ሲጋራ አጫሽ ሠራተኛ፣ ከማያጨስ ሠራተኛ ጋር ሲወዳደር አሠሪውን በዓመት 5,816 የአሜሪካ ዶላር ተጨማሪ ወጪ ያስወጣዋል” በማለት ኒው ዮርክ ታይምስ ዘግቧል። በኦሃዮ በሚገኝ አንድ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ጥናቱን ያካሄዱት ተመራማሪዎች እንደገለጹት ይህን ተጨማሪ ወጪ ከሚያስወጡት ነገሮች መካከል ለማጨስ ብሎ ሥራን ማቋረጥ፣ ለሕክምና የሚወጣ ከፍተኛ ወጪ እና ከሥራ ገበታ መቅረት ይገኙበታል። ሌላው ምክንያት ደግሞ የሚያጨሰው ሰው የኒኮቲን ሱሰኛ በመሆኑ ሲጋራ ካላጨሰ ሥራውን በሚገባ መሥራት አለመቻሉ ነው።

ጣሊያን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ

“ቀሳውስትና ምዕመናን በሚናገሩት እና በሚያደርጉት፣ ማለትም በአንደበታቸውና በአኗኗራቸው መካከል ከፍተኛ መጣረስ መኖሩ የቤተ ክርስቲያንን ተአማኒነት በጣም እየሸረሸረው ነው።”—ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ

ማሌዥያ

የማሌዥያ ባለሥልጣናት በሕገ ወጥ መንገድ የገባ የዝሆን ጥርስ ሲይዙ

የማሌዥያ ባለሥልጣኖች በሁለት የጣውላ ጭነቶች ውስጥ 240 ኩንታል የሚመዝኑ ከ1,000 የሚበልጡ የዝሆን ጥርሶች ተደብቀው አግኝተዋል። የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያዎች ይህን ያህል መጠን ያለው የዝሆን ጥርስ ከአሁን በፊት ተይዞ እንደማያውቅ ተናግረዋል። የጭነቱ መነሻ ቦታ ቶጎ ሲሆን መድረሻው ደግሞ ቻይና ነበር።

አፍሪካ

አንድ አፍሪካዊ ሰው

በዓለም የጤና ድርጅት የ2012 ሪፖርት መሠረት ባለፉት ጥቂት ዓመታት ከሞቱት ሰዎች መካከል 63 በመቶ የሚሆኑት የሞቱት በተላላፊ በሽታዎች ምክንያት ነው፤ ከእነዚህ መካከል ኤች አይ ቪ/ኤድስ፣ ተቅማጥ፣ ወባ፣ ሳንባ ነቀርሳ እና የሕፃናት በሽታዎች ይገኙበታል።

አውስትራሊያ

በስማርት ፎን ላይ የተጫነ የቁማር መጫወቻ ፕሮግራም

በስማርት ፎኖች እና በሌሎች መሣሪያዎች ላይ የሚጫኑ የቁማር መጫወቻ ፕሮግራሞች በልጆች ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነት አትርፈዋል። አንዳንዶቹ ጨዋታዎች እውነተኛውን የቁማር ጨዋታ የሚመስሉ ሲሆኑ ለማሸነፍም ቀላል ናቸው። መንግሥት ያወጣው አንድ ዘገባ ላይ የሚገኝ ማሳሰቢያ እንደሚገልጸው እንዲህ ያሉት ጨዋታዎች ልጆች ቁማርን ተቀባይነት እንዳለው ነገር እንዲመለከቱትና “ወደፊት የቁማር ሱሰኞች እንዲሆኑ” ሊያደርግ ይችላል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ