የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 1/15 ገጽ 16
  • የዜናው ትኩረት—ሃይማኖት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የዜናው ትኩረት—ሃይማኖት
  • ንቁ!—2015
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ዓለም
  • እንግሊዝ
  • አውስትራሊያ
  • እውነተኛውን ሃይማኖት ማግኘት የምችለው እንዴት ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ማንኛውም ሃይማኖት ጥሩ ነውን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • ሃይማኖቶች ተከታይ እያጡ ነው?
    ንቁ!—2015
  • ለደህንነት በሚያበቃ ንጹሕ ሃይማኖት መመላለስ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2015
g 1/15 ገጽ 16
የአንድ ቤተ ክርስቲያን አናት

ከዓለም አካባቢ

የዜናው ትኩረት—ሃይማኖት

ሃይማኖት አንድነትን ማምጣት ነበረበት። ብዙውን ጊዜ ግን ግጭት እንዲቀሰቀስና መተማመን እንዲጠፋ መንስኤ ሲሆን ይታያል።

ዓለም

የምድርን ሦስት አራተኛ ክፍል ደመቅ አድርጎ የሚያሳይ ምስል

ከሦስት አራተኛ በላይ የሚሆነው የዓለም ሕዝብ የሚኖረው በመንግሥት ፖሊሲ ወይም በሕዝብ ጥላቻ ምክንያት በሃይማኖት ላይ ከፍተኛ ገደብ በተደረገባቸው አገሮች ውስጥ ነው። አናሳ በሆኑ ሃይማኖታዊ ቡድኖች ላይ ጥቃት የሚፈጸምባቸው አገሮች ቁጥር በቅርቡ ባሳለፍናቸው አምስት ዓመታት ውስጥ በእጥፍ ገደማ ጨምሯል።

እስቲ አስበው፦ አንዳንድ ሰዎች ለሃይማኖት ጥላቻ የሚኖራቸው በየትኞቹ ተቃራኒ ምክንያቶች ሊሆን ይችላል?—ማቴዎስ 23:27, 28፤ ዮሐንስ 15:19

እንግሊዝ

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ቶኒ ብሌር ኦብዘርቨር በተሰኘ ጋዜጣ ላይ እንደጻፉት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለሚታዩት የሽብር ጥቃቶች ዋነኛው መንስኤ ሃይማኖታዊ ጽንፈኝነት ነው። እንዲህ ብለዋል፦ “በ20ኛው ክፍለ ዘመን እንደነበረው ሁሉ በዚህ ክፍለ ዘመን ለሚደረጉት ጦርነቶችም መንስኤው ፖለቲካዊ ጽንፈኝነት ነው ብሎ ማሰብ የማይመስል ነገር ነው፤ ከዚህ ይልቅ ጦርነቶቹ በባሕል ወይም በሃይማኖታዊ ልዩነቶች ምክንያት በቀላሉ በሚቀሰቀሱ ውዝግቦች ሳቢያ የተነሱ ናቸው።”

እስቲ አስበው፦ ሃይማኖት ብዙውን ጊዜ ለግጭት መንስኤ የሆነው ለምንድን ነው?—ማርቆስ 7:6-8

አውስትራሊያ

የአውስትራሊያ ስታቲስቲክስ ቢሮ ባወጣው ሪፖርት መሠረት ከ5 የአውስትራሊያ ዜጎች 1ዱ የየትኛውም የሃይማኖት ድርጅት አባል እንዳልሆነ ይናገራል። በዚያ ላይ ደግሞ ሪፖርቱ እንደገለጸው ከሆነ “አንድ ሰው የአንድ ሃይማኖት ድርጅት አባል እንደሆነ መናገሩ በሃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ንቁ ተሳትፎ እንደሚያደርግ አያሳይም።” ሃይማኖት እንዳላቸው ከተናገሩት ሰዎች መካከል በሃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ አዘውትረው እንደሚሳተፉ የገለጹት 15 በመቶ የሚሆኑት ወንዶችና እና 22 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ብቻ ናቸው።

አንደኛው ሰው የሰረዝ ምልክት ተደርጎበታል፤ አራቱ ሰዎች እጃቸውን ወደ ላይ አንስተዋል

እስቲ አስበው፦ በዛሬው ጊዜ ባሉት አብዛኞቹ የሃይማኖት ድርጅቶች ውስጥ ምን ዓይነት መጥፎ ባሕርያት ይታያሉ?—ማቴዎስ 7:15-20

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ