የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 6/15 ገጽ 16
  • የዜናው ትኩረት—አካባቢ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የዜናው ትኩረት—አካባቢ
  • ንቁ!—2015
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አውስትራሊያ
  • ሰሃራ በረሃ
  • ዓለም
  • እየተመናመነ የሚገኘው የምድር የተፈጥሮ ሀብት
    ንቁ!—2005
  • የርዕስ ማውጫ
    ንቁ!—2023
  • ችግሩ ይበልጥ አሳሳቢ የሆነባቸው ቦታዎች
    ንቁ!—1998
  • አየር
    ንቁ!—2023
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2015
g 6/15 ገጽ 16
ሰሃራ በረሃ

ከዓለም አካባቢ

የዜናው ትኩረት—አካባቢ

ምድር ንፁሕ አየር፣ ገንቢ ምግብ፣ ንፁሕ ውኃ ብታቀርብም የሰው ልጆች እነዚህን የተፈጥሮ ሂደቶች በማቃወስ ላይ ናቸው። የሳይንስ ሊቃውንት ይህን ሁኔታ የሚያስተካክል መፍትሔ ለማግኘት የሞት ሽረት ትግል በማድረግ ላይ ናቸው።

አውስትራሊያ

በዓለም ዙሪያ ከሚገኙት ውቅያኖሶች በታች 500,000 ኪሎ ሜትር ኩብ የሚያህል ጨዋማ ያልሆነ ውኃ እንደሚገኝ ይገመታል። በአድሌድ የሚገኘው የፍላይንደርስ ዩኒቨርሲቲ ባልደረባ የሆኑ ቪንሰንት ፖስት “የባሕር ጠለል አሁን ከሚገኝበት በጣም ዝቅ ያለ ነበር” ብለዋል፤ በመሆኑም የባሕር ዳርቻዎች አሁን ከሚገኙበት በጣም የራቁ ነበሩ። በዚያን ጊዜ “ዛሬ በባሕር ከተሸፈኑ ቦታዎች በታች ያለው የከርሰ ምድር ውኃ በዝናብ ይሞላ ነበር።” ከባሕር በታች ያለ ይህ የውኃ ክምችት ንፁሕ ውኃ ማግኘት ላልቻሉ ከ700 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሕዝቦች ሊጠቅም እንደሚችል ተስፋ ያደርጋሉ።

ሰሃራ በረሃ

በአንድ ወቅት በሰሃራ በረሃ ይገኙ ከነበሩት የትላልቅ እንስሳት ዝርያዎች ውስጥ ግማሽ የሚሆኑት ጠፍተዋል፤ አሊያም ከዚህ ቀደም ይኖሩበት የነበረውን አካባቢ አንድ መቶኛ በሚያህል ወይም ከዚያ በሚያንስ ቦታ ተወስነው ለመኖር ተገደዋል። ለዚህ ምክንያቱ የአካባቢ አለመረጋጋት ወይም የአደን መስፋፋት ብቻ አይደለም። በበረሃማ አካባቢዎች የሚገኘው ብዝሃ ሕይወት በደን ከተሸፈኑ አካባቢዎች የማይተናነስ ቢሆንም “በበረሃ አካባቢ ላለው ብዝሃ ሕይወት የሚሰጠው ሳይንሳዊ ትኩረትና የገንዘብ ድጋፍ” አነስተኛ እንደሆነ ተመራማሪዎች ይናገራሉ። በመሆኑም የዱር አራዊት ጥበቃ ሠራተኞች በበረሃማ አካባቢዎች ያለውን የመጥፋት አደጋ ያጠላበት ሥነ ምህዳር መቆጣጠር አስቸጋሪ ሆኖባቸዋል።

ዓለም

በ2012 ከሞቱት ሰዎች መካከል ከስምንት አንዱ የሞተው በአየር ብክለት ምክንያት እንደሆነ ይገመታል። የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚለው “በአሁኑ ጊዜ ትልቁ የጤና ጠንቅ የአየር ብክለት ነው።”

ሊታሰብባቸው የሚገቡ ነጥቦች፦ ታላቅ ዓላማ ይዘው ብርቱ ጥረት የሚያደርጉ ሰዎች በአካባቢያችን ላይ የሚደርሰውን ውድመት ማስቆም ያልቻሉት ለምንድን ነው?—ኤርምያስ 10:23

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ