የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g16 ቁጥር 5 ገጽ 7
  • የዜናው ትኩረት—የአሜሪካ አህጉራት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የዜናው ትኩረት—የአሜሪካ አህጉራት
  • ንቁ!—2016
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ከመጠን በላይ ዓሣ ማጥመድ ካስከተለው ጉዳት ማገገም
  • ኢ-ሜይል ቶሎ ቶሎ አለማየት ውጥረት ይቀንሳል?
  • ዓመፅ በብራዚል
  • ውጥረትን መቆጣጠር የምንችልበት መንገድ
    ንቁ!—2010
  • ውጥረትን መቋቋም የሚቻለው እንዴት ነው?
    ንቁ!—2020
  • ጥሩና መጥፎ ውጥረት
    ንቁ!—1998
  • በትምህርት ቤት የሚያጋጥመኝን ውጥረት እንዴት ልቋቋመው?
    ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች፣ ጥራዝ 1
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2016
g16 ቁጥር 5 ገጽ 7
ውቅያኖስ ውስጥ ያለ ዓሣ

ከዓለም አካባቢ

የዜናው ትኩረት—የአሜሪካ አህጉራት

ከምዕራቡ ንፍቀ ክበብ የሚሰሙ ዜናዎች፣ ጊዜ የማይሽረውን የመጽሐፍ ቅዱስን ምክር መከተል ያለውን ጥቅም ያሳያሉ።

ከመጠን በላይ ዓሣ ማጥመድ ካስከተለው ጉዳት ማገገም

በቤሊዝ እንዲሁም በሌሎች የካሪቢያን አካባቢዎች “ዓሣ ማጥመድ በተከለከለባቸው ቦታዎች የኮንች፣ የሎብስተር እንዲሁም የሌሎች የዓሣ ዝርያዎች ብዛት እንደጨመረ አንዳንድ ዘገባዎች ያሳያሉ” በማለት ለዱር እንስሳት ጥበቃ ማኅበር የቀረበ አንድ ሪፖርት ዘግቧል። ሪፖርቱ አክሎም እንዲህ ይላል፦ “ብዙ በመጠመዳቸው ምክንያት ቁጥራቸው ቀንሶ የነበሩ ዝርያዎች፣ . . . ማጥመድ በተከለከለባቸው ቦታዎች ላይ ቁጥራቸው መልሶ ለመጨመር የሚፈጅበት ጊዜ ከ1-6 ዓመት ያህል ብቻ ነው፤ ሆኖም እነዚህ ዝርያዎች ሙሉ በሙሉ ለማገገም . . . አሥርተ ዓመታት ሊፈጅባቸው ይችላል።” የዱር እንስሳት ጥበቃ ማኅበር ፕሮግራም ዳይሬክተር የሆነችው ጃኔት ጊብሰን ስለ ቤሊዝ ስትናገር እንዲህ ብላለች፦ “ዓሣ ማጥመድ የተከለከለባቸው ቦታዎች መኖራቸው፣ የአገሪቱን የዓሣ ሀብት እና ብዝሃ ሕይወት ለማሳደግ እንደሚረዳ በግልጽ ማየት ይቻላል።”

ሊታሰብበት የሚገባ ነጥብ፦ ፍጥረታት ወደ ቀድሞ ሁኔታቸው የመመለስ ችሎታ ያላቸው መሆኑ ጥበበኛ የሆነ ፈጣሪ እንዳለ የሚያሳይ አይመስልህም?—መዝሙር 104:24, 25

ኢ-ሜይል ቶሎ ቶሎ አለማየት ውጥረት ይቀንሳል?

የኢ-ሜይል መልእክቶቹን በቀን ሦስት ጊዜ የሚከፍት አንድ ሰው የተረጋጋ ይመስላል፤ የኢ-ሜይል መልእክቶቹን ብዙ ጊዜ የሚከፍት ሌላ ሰው ደግሞ በውጥረት የተሞላ ይመስላል

በቫንኩቨር፣ ካናዳ የተደረገ አንድ ጥናት እንዳሳየው ሰዎች አጋጣሚውን ባገኙ ቁጥር የኢ-ሜይል መልእክቶቻቸውን ከመክፈት ይልቅ በቀን ሦስት ጊዜ ብቻ የሚከፍቱ ከሆነ፣ የሚሰማቸው ውጥረት ሊቀንስ ይችላል። ጥናቱን የመሩት ኮስታዲን ኩሽሌቭ ውጤቱን በተመለከተ እንዲህ ብለዋል፦ “ሰዎች የኢ-ሜይል መልእክታቸውን ቶሎ ቶሎ ለማየት ይፈተናሉ፤ ሆኖም ይህን ፈተና መቋቋም ከቻሉ፣ የሚሰማቸው ውጥረት ይቀንሳል።”

ሊታሰብበት የሚገባ ነጥብ፦ የምንኖረው ‘ለመቋቋም በሚያስቸግር በዓይነቱ ልዩ የሆነ ዘመን’ ውስጥ ነው፤ ታዲያ ውጥረት ለመቀነስ የሚያስችሉንን መንገዶች መፈለጋችን ጠቃሚ አይሆንም?—2 ጢሞቴዎስ 3:1

ዓመፅ በብራዚል

አሼንስያ ብራዚል የተባለው የዜና አገልግሎት፣ በብራዚል የሚፈጸሙ የዓመፅ ድርጊቶች እየጨመሩ እንደሆነ ዘግቧል። በ2012 ከ56,000 በላይ የነፍስ ግድያ ወንጀሎች ተፈጽመዋል፤ ይህ ቁጥር በጤና ሚኒስቴር ከተመዘገቡ በአንድ ዓመት ውስጥ የተፈጸሙ የነፍስ ግድያ ወንጀሎች ሁሉ ከፍተኛው ነው። የሕዝብ ደህንነት ባለሙያ የሆኑት ሉዊስ ሳፖሪ፣ ይህ የሆነው በማኅበረሰቡ ውስጥ የሥነ ምግባር ውድቀት ስለሚታይ እንደሆነ ይሰማቸዋል። ሰዎች በአንድ የሠለጠነ ማኅበረሰብ ውስጥ ላሉት ሕጎች አክብሮት ሲያጡ “ፍላጎታቸውን ለማስፈጸም በጉልበት መጠቀም ይጀምራሉ” በማለት ተናግረዋል።

ይህን ያውቁ ኖሯል? መጽሐፍ ቅዱስ ‘ፍቅር የሚቀዘቅዝበትና’ ክፋት የሚበዛበት ጊዜ እንደሚመጣ አስቀድሞ ተናግሯል።—ማቴዎስ 24:3, 12

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ