የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g20 ቁጥር 2 ገጽ 12-13
  • 4. የተፈጠርነው በመከራ የተሞላ ሕይወት እንድንኖር ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • 4. የተፈጠርነው በመከራ የተሞላ ሕይወት እንድንኖር ነው?
  • ንቁ!—2020
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ይህን ማወቅ ለምን አስፈለገ?
  • ሊታሰብባቸው የሚገቡ ነጥቦች
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
  • መከራ
    ንቁ!—2015
  • የርዕስ ማውጫ
    ንቁ!—2020
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምራል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2017
  • ጥያቄ 3፦ አምላክ መከራ እንዲደርስብኝ የሚፈቅደው ለምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2020
g20 ቁጥር 2 ገጽ 12-13
አንድ ቤተሰብ ተራራ ላይ ሲዝናና። የቤተሰቡ አባላት ፎቶ እየተነሱ ነው።

4. የተፈጠርነው በመከራ የተሞላ ሕይወት እንድንኖር ነው?

ይህን ማወቅ ለምን አስፈለገ?

የዚህ ጥያቄ መልስ ለሕይወት ባለን አመለካከት ላይ ለውጥ ያመጣል።

ሊታሰብባቸው የሚገቡ ነጥቦች

ዓለማችንን ውብ አድርጎ የፈጠረው አምላክ በመከራ የተሞላ ሕይወት እንድንመራ ይፈልጋል ብሎ ማሰብ ምክንያታዊ ነው?

ሃይማኖተኛ ያልሆኑ ሰዎች በዓለም ላይ ያለውን መከራ ሲያዩ በአምላክ ባሕርይ ላይ ጥያቄ ያነሳሉ፤ አልፎ ተርፎም እሱ መኖሩን ይጠራጠራሉ። በእነዚህ ሰዎች አመለካከት መሠረት መከራ የሚደርስብን (1) አምላክ መከራን ለማስቆም ኃይል ስለሌለው፣ (2) አምላክ መከራን ማስቆም ስለማይፈልግ ወይም (3) አምላክ ስለሌለ ነው።

ሆኖም ያሉት አማራጮች እነዚህ ብቻ ናቸው?

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት

jw.org ላይ የሚገኘውን መጽሐፍ ቅዱስ ከአምላክ የመጣ መሆኑን እንዴት እርግጠኞች መሆን እንችላለን? የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት።

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

አምላክ የፈጠረን በመከራ የተሞላ ሕይወት እንድንኖር አይደለም።

አምላክ ደስተኛ ሆነን እንድንኖር ይፈልጋል።

“ለሰው በሕይወት ዘመኑ ከመደሰትና መልካም ከማድረግ የተሻለ ነገር የለም . . . ደግሞም ለሰው ከመብላትና ከመጠጣት እንዲሁም ተግቶ በሚሠራው ሥራ ሁሉ ደስታ ከማግኘት የተሻለ ነገር የለም። ይህ የአምላክ ስጦታ ነው።”—መክብብ 3:12, 13

አምላክ አዳምንና ሔዋንን የፈጠራቸው ደስተኛ ሆነው እንዲኖሩ ነበር።

የአምላክ ዓላማ እነሱም ሆኑ ዘሮቻቸው መከራ እንዲደርስባቸው አልነበረም።

“አምላክ ባረካቸው፤ እንዲህም አላቸው፦ ‘ብዙ ተባዙ፤ ምድርንም ሙሏት፤ ግዟትም።’”—ዘፍጥረት 1:28

አዳምና ሔዋን አምላክን ላለመታዘዝ መረጡ።

በመሆኑም በራሳቸውም ሆነ በዘሮቻቸው ላይ ብዙ መከራ አመጡ።

“በአንድ ሰው አማካኝነት ኃጢአት ወደ ዓለም ገባ፤ በኃጢአትም ምክንያት ሞት መጣ፤ ሁሉም ኃጢአት ስለሠሩም ሞት ለሰው ሁሉ ተዳረሰ።”—ሮም 5:12a

አምላክ ለሰው ልጆች ከእሱ አገዛዝ ውጭ ሆነው ራሳቸውን የመምራት ችሎታ አልሰጣቸውም።

ውኃ ውስጥ መኖር እንድንችል ተደርገን እንዳልተፈጠርን ሁሉ ራሳችንን መምራት እንድንችል ተደርገንም አልተፈጠርንም።

“[ሰው] አካሄዱን እንኳ በራሱ አቃንቶ መምራት አይችልም።”—ኤርምያስ 10:23

አምላክ መከራ እንዲደርስብን አይፈልግም።

አምላክ መከራ ከሚያስከትሉብን ነገሮች በተቻለ መጠን እንድንርቅ ይፈልጋል።

“ትእዛዛቴን ብትሰማ ምንኛ መልካም ነው! እንዲህ ብታደርግ ሰላምህ እንደ ወንዝ . . . ይሆናል።”—ኢሳይያስ 48:18

a በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ኃጢአት” የሚለው ቃል ሰዎች የሚፈጽሙትን መጥፎ ድርጊት ብቻ ሳይሆን ሁሉም ሰዎች ያሉበትን ሁኔታ ማለትም በዘር የወረሱትን ኃጢአትም ያመለክታል።

የተፈጠርነው በመከራ የተሞላ ሕይወት እንድንኖር ነው?

በጭራሽ። አምላክ የሰው ልጆች መከራ እንዲደርስባቸው ዓላማው አልነበረም። መከራ የጀመረው አዳምና ሔዋን አምላክን ላለመታዘዝ በመምረጣቸው ነው። ይህ ሲባል ግን የሰው ልጆች ለዘላለም መከራ እየደረሰባቸው ይኖራሉ ማለት አይደለም።

ታዲያ መከራችን የሚያበቃበት ጊዜ ይመጣ ይሆን?

ጥያቄ 5⁠ን ተመልከት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ