የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • gf ትምህርት 12 ገጽ 20
  • ሰው ሲሞት ምን ይሆናል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ሰው ሲሞት ምን ይሆናል?
  • የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ!
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የሞቱ ሰዎች በምን ዓይነት ሁኔታ ላይ ይገኛሉ?
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2016
  • የሞቱ አያት፣ ቅድመ አያቶቻችን ያሉት የት ነው?
    ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን መንገድ አግኝተኸዋል?
  • ሙታንን ልትፈራ ይገባሃል?
    ንቁ!—2009
ለተጨማሪ መረጃ
የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ!
gf ትምህርት 12 ገጽ 20

ትምህርት 12

ሰው ሲሞት ምን ይሆናል?

ሞት የሕይወት ተቃራኒ ነው። ሞት ከከባድ እንቅልፍ ጋር ይመሳሰላል። (ዮሐንስ 11:11-14) ሙታን መስማት፣ ማየት፣ መናገር ወይም ምንም ነገር ማሰብ አይችሉም። (መክብብ 9:5, 10) የሐሰት ሃይማኖት ሙታን ከቀድሞ አባቶቻቸው ጋር ለመኖር ወደ መንፈሳዊ ዓለም ይሄዳሉ በማለት ያስተምራል። መጽሐፍ ቅዱስ ግን እንዲህ ብሎ አያስተምርም።

ኢየሱስ የኢያኢሮስን ልጅ ከሞት ሲያስነሳት

የሞቱ ሰዎች ሊረዱንም ሆነ ሊጎዱን አይችሉም። አንዳንዶች የሞቱ ሰዎችን ያስደስታቸዋል ብለው በማሰብ አምልኮታዊ ድርጊቶችንና መሥዋዕቶችን ያቀርባሉ። ይህ ድርጊት ሰይጣን ከተናገራቸው ውሸቶች መካከል በአንዱ ላይ የተመሠረተ በመሆኑ አምላክን አያስደስትም። ሙታን በድን በመሆናቸው የሞቱትንም አያስደስትም። ሙታንን መፍራትም ሆነ ማምለክ አይኖርብንም። ማምለክ ያለብን አምላክን ብቻ ነው።—ማቴዎስ 4:10

ሙታን ዳግመኛ በሕይወት ይኖራሉ። ይሖዋ በገነቲቱ ምድር ውስጥ በሕይወት እንዲኖር ሙታንን ያስነሳቸዋል። ይህ የሚሆነው ወደፊት ነው። (ዮሐንስ 5:28, 29፤ ሥራ 24:15) አንድን የተኛ ሰው ከእንቅልፉ ቀስቅሰህ ማስነሳት እንደምትችል ሁሉ አምላክም የሞቱ ሰዎችን ሊያስነሳ ይችላል።—ማርቆስ 5:22, 23, 41, 42

አንሞትም የሚለው ሐሳብ ሰይጣን ዲያብሎስ የሚያስፋፋው ውሸት ነው። ሰይጣንና አጋንንቱ የሙታን መናፍስት ሕያው ሆነው ይቀጥላሉ፤ ህመምንና ሌሎች ችግሮችንም ያስከትላሉ ብለው ሰዎች እንዲያስቡ ያደርጋሉ። ሰይጣን አልፎ አልፎ በሕልምና በራእይ ሰዎችን ያታልላል። ይሖዋ ከሙታን ጋር ለመነጋገር የሚሞክሩ ሰዎችን ያወግዛል።—ዘዳግም 18:10-12

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ