የክፍል 2 ማስተዋወቂያ
ይሖዋ በጥንት ዘመን የነበረውን ዓለም በውኃ ያጠፋው ለምንድን ነው? በሰው ልጅ ታሪክ መጀመሪያ ላይ ሰይጣን በይሖዋ ላይ ዓመፀ። እንደ አዳም፣ ሔዋንና ቃየን ያሉ ሰዎች ከሰይጣን ጎን ለመሰለፍ መረጡ። እንደ አቤልና ኖኅ ያሉ ጥቂት ሰዎች ደግሞ ከይሖዋ ጎን ለመሰለፍ መረጡ። አብዛኞቹ ሰዎች በጣም መጥፎ ሆነው ስለነበር ይሖዋ ያንን ክፉ ዓለም አጠፋው። ይህ ክፍል፣ ይሖዋ ከእሱ ጎን አለዚያም ከሰይጣን ጎን ለመሰለፍ የምናደርገውን ምርጫ እንደሚመለከት ይገልጻል። ከዚህም ሌላ ይሖዋ በአሁኑ ጊዜም ቢሆን ክፋት መልካም የሆነውን ነገር እንዲያሸንፍ እንደማይፈቅድ ያብራራል።