ይህን ቡክሌት መጠቀም የሚቻልበት መንገድ
በሚቀጥሉት ገጾች ላይ ለእያንዳንዱ ቀን የተሰጠውን ጥቅስና ጥቅሱን የሚያብራራ ሐሳብ ታገኛለህ። የዕለቱን ጥቅስም ሆነ ሐሳቡን በቀኑ ውስጥ በማንኛውም ሰዓት ላይ ማንበብ ቢቻልም ብዙዎች የዕለቱን እንቅስቃሴያቸውን ከመጀመራቸው በፊት የዕለቱን ጥቅስ ማንበብ ጠቃሚ ሆኖ አግኝተውታል። እንዲህ ማድረጋቸው ባነበቡት ሐሳብ ላይ ቀኑን ሙሉ ለማሰላሰል አስችሏቸዋል። የዕለቱን ጥቅስ በቤተሰብ ሆኖ መወያየትም በጣም ጠቃሚ ነው። በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የቤቴል ቤተሰቦች በቁርስ ሰዓት እንዲህ የማድረግ ልማድ አላቸው።
ጥቅሱን የሚያብራሩት ሐሳቦች የተወሰዱት ከሚያዝያ 2016 እስከ መጋቢት 2017 ከወጡት የመጠበቂያ ግንብ (w) እትሞች ላይ ነው። መጠበቂያ ግንቡ የመቼ እትም እንደሆነ ከሚገልጸው አኃዝ ቀጥሎ ያለው ቁጥር (1, 2, 3, 4 ወይም 5 ሊሆን ይችላል) ሐሳቡ የተወሰደው ከስንተኛው የጥናት ርዕስ እንደሆነ ያመለክታል። ከዚያ ቀጥሎ ማብራሪያው የሚገኝባቸው አንቀጾች ተጠቅሰዋል። (ከታች ያለውን ምሳሌ ተመልከት።) ስለ ጉዳዩ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት የጥናት ርዕሱን መመልከት ይቻላል። ርዕሶቹ የሚገኙበትን ገጽ ለማወቅ የመጠበቂያ ግንቡን ሁለተኛ ገጽ ተመልከት።