ይህን ቡክሌት መጠቀም የሚቻልበት መንገድ
በሚቀጥሉት ገጾች ላይ ለእያንዳንዱ ቀን የተሰጠውን ጥቅስና ጥቅሱን የሚያብራራ ሐሳብ ታገኛለህ። የዕለቱን ጥቅስም ሆነ ሐሳቡን በቀኑ ውስጥ በማንኛውም ሰዓት ላይ ማንበብ ቢቻልም ብዙዎች የዕለቱን እንቅስቃሴያቸውን ከመጀመራቸው በፊት የዕለቱን ጥቅስ ማንበብ ጠቃሚ ሆኖ አግኝተውታል። እንዲህ ማድረጋቸው ባነበቡት ሐሳብ ላይ ቀኑን ሙሉ ለማሰላሰል አስችሏቸዋል። የዕለቱን ጥቅስ በቤተሰብ ሆኖ መወያየትም በጣም ጠቃሚ ነው። በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የቤቴል ቤተሰቦች በቁርስ ሰዓት እንዲህ የማድረግ ልማድ አላቸው።
ጥቅሱን የሚያብራሩት ሐሳቦች የተወሰዱት ከሚያዝያ 2020 እስከ መጋቢት 2021 ከወጡት የመጠበቂያ ግንብ (w) እትሞች ላይ ነው። መጠበቂያ ግንቡ የመቼ እትም እንደሆነ ከሚገልጸው አኃዝ ቀጥሎ ያለው ቁጥር፣ ሐሳቡ የሚገኝበትን ገጽ ይጠቁማል። ከዚያ ቀጥሎ ያሉት ቁጥሮች ማብራሪያው የሚገኝባቸውን አንቀጾች ያመለክታሉ። (ከታች ያለውን ምሳሌ ተመልከት።) ስለ ጉዳዩ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት የጥናት ርዕሱን መመልከት ይቻላል።