የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w91 2/1 ገጽ 31
  • “ዘውዱና ምስክሩ”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “ዘውዱና ምስክሩ”
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
w91 2/1 ገጽ 31

“ዘውዱና ምስክሩ”

“ከዚያም [ካህኑ ዮዳሄ] የንጉሡንም ልጅ አውጣና ዘውዱንና ምስክሩን ጫነበት፤ ይህንንም በማድረግ ቀብተው አነገሱት።” (2 ነገሥት 11:12 አ.ዓ.ት) መጽሐፈ ነገሥት የንጉሥ ኢዮአስን ሥርዓተ ንግሥና የሚገልጸው በዚህ ዓይነት ነው። ዮዳሄ ከዘውዱ በተጨማሪ “ምስክሩን” በወጣቱ ንጉሥ አናት ላይ እንደጫነ አስተውል። ምስክሩ ምን ነበር? የሥርዓተ ንግሥናው ክፍል የሆነውስ ለምንድንነው?

እዚህ ላይ “ምስክሩ” ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቅል አስሩን ትዕዛዛት ወይም የአምላክን ቃል በአጠቃላይ ያመለክታል። (ዘፀአት 31:18፤ መዝሙር 78:5) ከዚህ ጋር በመስማማት በ2 ዜና 23:11 ላይ ያለው ተመሳሳይ ታሪክ በዘ ጀሩሳሌም ባይብል (1966)መሠረት “ከዚያም ዮዳሄ የንጉሱን ልጅ ወደ ውጭ አውጥቶ አነገሰውና ሕጉን ጫነበት” ይላል። ይሁን እንጂ ይኸው ትርጉም በ2 ነገሥት 11:12 ላይ “ምስክሩ” በሚለው ቃል ምትክ “የእጅ አምባር” የሚል ቃል አስገብቶአል። በሁለቱም ቦታዎች ላይ ግን የሰፈረው የዕብራይስጥ ቃል አንድ ነው። ለምን እንዲህ ሆነ?

አንድ እውቅ ኸርደርስ ቢበኮመንታር የተባለ የጀርመንኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ማብራሪያ አንዳንድ ተርጓሚዎች ንጉሱ ሕጉን በራሱ ላይ ወይም በክንዱ ላይ ያደርጋል ብሎ ማሰብ አስቸጋሪ ስለሆነባቸው ነው ሲል ይገልጻል። 2 ሳሙኤል 1:10 ስለ ሳሙኤል ሲናገር ካደረገው ዘውድ ጋራ አምባር ስለሚጠቅስ በ2 ነገሥት 11:12 ላይ ያለው ጥቅስ “ዘውዱና አምባሩ” መባል አለበት ብለው አሰቡ። ይሁን እንጂ ይህ በግምት ላይ ብቻ የተመሰረተ አስተሳሰብ ነው። “ምስክሩ” የሚለውን ቃል “በአምባር” መለወጥ በቀላሉ የሚታይ ለውጥ አይደለም።

በዚህ ምክንያት ዘ ኒው ጀሩሳሌም ባይብል (1985) “የቃል ኪዳኑንም ቅጂ ሰጠው” ብሎ በመተርጎም ሕጉን ወይም የሕጉን ቃል ኪዳን ያመለክታል ወደሚለው አሳብ ተመልሶአል። ይሁን እንጂ ዮዳሄ “ምስክሩን” ለኢዮአስ ሰጥቶት ነበርን? እርግጥ “አስቀመጠ” ተብሎ የሚተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል “ሰጠ” ተብሎም ሊተረጎም ይችላል። ይሁን እንጂ ይህ ቃል በነገስትም ሆነ በዜና መዋዕል መጽሐፍ ውስጥ የተጠቀሰው አንድ ጊዜ ብቻ ሲሆን ያገለገለውም ስለ ዘውዱና ስለ ምስክሩ ለመናገር ነው። ከዚህም በላይ “በላይ” የሚል ትርጉም ያለው የዕብራይስጥ ቃል ተከትሎታል። ስለዚህ ትክክለኛው ትርጉም “ከላዩ አደረገበት” የሚል መሆን አለበት። አዲሲቱ ዓለም ትርጉም እንደሚለው ዘውዱም ሆነ ምስክሩ በወጣቱ ንጉሥ በኢዮአስ ራስ ላይ ተደርጎአል።

ሆኖም ግን ሊቀ ካህናቱ ምሥክሩን በወጣቱ ንጉሥ ራስ ላይ ያደረገው እንዴትና ለምንድንነው? ጀርመናዊው ምሁር ኦቶ ቴኒየስ የሰጡትን ሐሳብ እንመልከት፤ “ሕጉ የሙሴ ድንጋጌዎች የተመዘገቡበት መጽሐፍ ነበር። እርሱም ንጉሱ ዘውድ ከጫነ በኋላ በምሳሌነት በራሱ ላይ ይደረግ ነበር።” (ዲ ቢውሸር ደር ከኒገ የነገሥት መጽሐፍ) በተመሳሳይም ፕሮፌሰር አርነስት በርቶ እንዲህ ብለዋል፤ “ሕጉ በንጉሱ ራስ ላይ መጫኑ ምሳሌነት አለው። ንጉሱ ከዚህ ጋር ተስማምቶ የመግዛት ግዴታ እንዳለበት ያመለክታል።”​—ዲ ቢውሸር ዲ ክሮኒክ (የዜና መዋዕል መጽሐፍ)

አምላክ ንጉሱ በዙፋን ላይ በተቀመጠ ጊዜ ሕጉን እንዲገለብጥና እያነበበና እያጠና በሕይወቱ ሁሉ በሥራ ላይ እንዲያውለው አዝዞ ነበር። (ዘዳግም 17:18-20) “ምስክሩን” አዲስ በነገሰው ንጉስ ላይ መጫን እርሱ ንጉሥ ቢሆንም ከይሖዋ ሕግ በላይ እንዳልሆነ የሚያስገነዝብ ተምሳሊት ያለው ድርጊት ሊሆን ይችላል። የሚያሳዝነው ግን ዮዳሄ ከሞተ በኋላ ንጉስ ኢዮአስ ይህን ትልቅ ትምህርት ዘንግቶ ቀስ በቀስ ከይሖዋ አምልኮ ራቀና በሰው እጅ ተገደለ።​—2 ዜና 24:17-25

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ