የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w92 3/15 ገጽ 31
  • የእርዳታ ተልእኮ ለዩክሬይን

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የእርዳታ ተልእኮ ለዩክሬይን
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
w92 3/15 ገጽ 31

የእርዳታ ተልእኮ ለዩክሬይን

አሁንም እንደገና የዜና ማሠራጫዎች በአሳዛኝ ዘገባዎች መሞላት ጀምረዋል የኤኮኖሚ ውድቀት፣ የምግብ እጥረትና ረሀብ ምድርን በሙሉ በአሁን ጊዜ ደግሞ በተለይ የቀድሞዋን የሶቪየት ህብረት ክፍሎችም እያጠቃ ነው። በቅርቡ የይሖዋ ምሥክሮች የአስተዳደር አካል በዴንማርክ የሚገኘውን የመጠበቂያ ግንብ ማህበር ቅርንጫፍ ቢሮ በዩክሬይን ላሉ ችግረኛ ምሥክሮች እርዳታ እንዲያደራጅ ጠይቆት ነበር። የዴንማርክ ወንድሞችስ ምን አደረጉ?

የእርዳታ ዝግጅቱን ሥራ ወዲያውኑ ጀመሩ! የቅርንጫፍ ቢሮው ወዲያውኑ የተሻለ የምግብ ሸቀጥ ግዢ የሚገኝበትን ሥፍራ እንዲያገኙ በገበያው በሙሉ እንዲያስሱ ወንድሞችን ላከ። በዴንማርክ ወዳሉ የይሖዋ ሕዝቦች ጉባኤዎች በሙሉ ስለ ችግሩ የሚገልጽ መልእክት ተላለፈ። ቅርንጫፍ ቢሮው የሚከተለውን ሪፖርት ልኳል፦ “ሁሉም ጉባኤዎች ከሚጠበቀው በላይ እርዳታ ለመስጠት ዝግጁዎች ነበሩ። በመጨረሻም በዩክሬይን በረሀብ በመሰቃየት ላይ ለሚገኙት ወንድሞቻችን የችግራቸው ተካፋዮች መሆናችንን የሚያሳይ ተጨባጭ ማስረጃ ማቅረብ ቻልን።” በመሃሉም በጀርመን ያለው ቅርንጫፍ ቢሮ በእርዳታ የተዋጡ አምስት የጭነት መኪናዎችን ወደ ዴንማርክ ላከ። እነዚህ የጭነት መኪናዎች ከሌሎች ሁለት አነስተኛ አውቶቡሶችና 14 ፈቃደኛ ሾፌሮች ጋር ቅዳሜ ታኅሣሥ 7, 1991 በዴንማርክ ወዳለው ቅርንጫፍ ቢሮ ደረሱ። የቅርንጫፍ ቢሮው ሠራተኞች የጭነት መኪናዎቹን በገዙአቸው የምግብ ሸቀጦች ሞሉአቸው።

ሰኞ ታኅሣሥ 9 እኩለ ቀን ላይ የጭነት መኪናዎቹ አጀብ በአውሮፓ አቋርጦ ወደ ዩክሬይን የሚወስደውን ረዥም ጉዞ ጀመረ። “መላው የቤቴል ቤተሰብ እጁን እያውለበለበ ሲሰናበታቸው ማየት ልብን የሚነካ ትርኢት ነበር” ይላል ቅርንጫፉ ሲጽፍ። “በብዙ የእርዳታ ጭነቶች ላይ ጥቃት እንደሚደርስ ስለምናውቅ ወንድሞቻችንን በመንገዳቸው ሁሉ ከብዙ ጸሎት ጋር ተከተልናቸው።”

ታኅሣሥ 18 ጭንቀታችን አበቃ። ጭነቱ በሰላም ልቮብ ዩክሬይን እንደገባ የሚገልጽ መልእክት ለዴንማርክ ቅርንጫፍ ቢሮ ደረሰው። በዩክሬይን ያሉ ወንድሞች እርዳታውን ተቀበሉ። እያንዳንዱ ጥቅል 16.41 ኪሎ ግራም የሚመዝንና በውስጡ ሥጋ፣ ዱቄት፣ ሩዝ፣ ስኳርና ሌሎችም ዋና ዋና ምግቦች የያዘ ለ1,100 ቤተሰብ የሚበቃ ጓዝ ሲያራግፉ እንዴት እፎይታ ተሰማቸው! ጠቅላላው የእርዳታ ጭነት 220 ኩንታል የሚያክል ነበር። የዴንማርክ ቅርንጫፍ ቢሮ “ይሖዋ የዕርዳታ እጃችንን እንድንዘረጋ ያስቻለንን ይህን አጋጣሚ ስለሰጠንና ጥበቃውም ስላልተለየን ስናመሰግን ደስታችን ከፍተኛ ነው” በማለት ጽፏል።

በተጨማሪም ልብስ ለመላክ ታስቧል። “በዚህ ረገድም ጉባኤዎች የሰጡት ምላሽ ከሚጠበቀው በላይ ነበር” በማለት ቅርንጫፍ ቢሮው ዘግቧል። ይሖዋ በእርግጥ ሕዝቡን ‘ለእግዚአብሔር የምስጋና ምክንያት የሚሆነውን ልግስና ሁሉ እንዲያሳዩ በሁሉ ነገር ባለጠጎች ያደርጋል’ (2 ቆሮንቶስ 9:11) እነሱም በምላሹ ለወንድሞቻቸውና ለእህቶቻቸው በነፃ ከመስጠት የሚመጣውን ጥልቅ ደስታ አግኝተዋል። ያሳዩት ፍቅር የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮች መለያ ምልክት ነው። (ዮሐንስ 13:35) እንዲህ ዓይነቱ ፍቅር በዚህ ችግረኛ ዓለም እጅግ በጣም ብርቅ ሆኗል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ