በትሕትና ተጋብዘዋል
ከ1,900 ዓመታት በፊት የተፈጸመው የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት በታሪክ ዘመናት ከተፈጸሙት ነገሮች ሁሉ የበለጠ ታላቅ ድርጊት ነው። የእርሱ መሞት ለሁላችንም በገነታዊ ምድር ላይ የዘላለም ሕይወት የማግኘትን ተስፋ ከፍቶልናል። ኢየሱስ ክርስቶስ ባከበረው አንድ ቀላል በዓል ወይንና ያልቦካ ቂጣ ላይ የፍቅራዊ ሰብአዊ መሥዋዕቱ ምሳሌ እንደሆነ አሳይቷል። ከዚያም ለደቀ መዛሙርቱ “ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት” አላቸው። (ሉቃስ 22:19) እርስዎስ ይህን ሞቱን ለማሰብ ይፈልጋሉን?
የይሖዋ ምሥክሮች ይህን የመታሰቢያ በዓል አብረዋቸው እንዲያከብሩ ከልብ ይጋብዙዎታል። የሚከበረውም በመጽሐፍ ቅዱስ የጨረቃ አቆጣጠር መሠረት ኒሳን 14 በሚውልበት ቀን ፀሐይ ከገባች በኋላ ነው። በአቅራቢያዎ ባለው የመንግሥት አዳራሽ ተገኝተው የበዓሉን አከባበር ሊከታተሉ ይችላሉ። ትክክለኛውን ሰዓትና ቦታ በአካባቢው ካሉት የይሖዋ ምሥክሮች ጠይቀው ያረጋግጡ። በ1992 በዓሉ የሚከበረው ዐርብ ሚያዝያ 17 ቀን ይሆናል።