የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w92 4/1 ገጽ 31
  • የአንባብያን ጥያቄዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአንባብያን ጥያቄዎች
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ኤልሳቤጥ ልጅ ወለደች
    ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ያለ ነቀፋ በመመላለሳቸው ተክሰዋል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • መንገድ የሚያዘጋጅ ሰው ተወለደ
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • ከአምላክ የተላኩ ሁለት መልእክቶች
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
w92 4/1 ገጽ 31

የአንባብያን ጥያቄዎች

ሉቃስ 1:62 የሚጠቁም እንደሚመስለው የዮሐንስ መጥምቁ አባት ዘካርያስ ደንቆሮም ድዳም እንዲሆን ተደርጎ ነበርን?

አንዳንዶች ዘካርያስ ደንቆሮም ሆኖ ነበር ብለው ደምድመዋል። በመጽሐፍ ቅዱስ ትረካ ላይ “በአባቱ ስም ዘካርያስ ሊሉት ወደዱ። እናቱ ግን መልሳ ‘አይሆንም፣ ዮሐንስ ይባል እንጂ’ አለች። እነሱም ‘ከወገንሽ ማንም በዚህ ስም የተጠራ የለም’ አሏት። አባቱንም ማን ሊባል እንዲወድ ጠቀሱት። ብራናም ለምኖ፦ ‘ስሙ ዮሐንስ ነው’ ብሎ ጻፈ” የሚል እናነባለን።—ሉቃስ 1:59-63

በዚህ ትረካ ላይ ዘካርያስ ለተወሰነ ጊዜ መስማት እንደተሳነው የሚያመለክት ምንም ፍንጭ የለም።

ቀደም ሲል መልአኩ ገብርኤል ለዘካርያስ ዮሐንስ የሚባል ወንድ ልጅ እንደሚወልድ አብስሮት ነበር። በዕድሜ የሸመገለው ዘካርያስ ይህን ለማመን አዳጋች ሆነበት። መልአኩም “እነሆም በጊዜው የሚፈጸመውን ቃሌን ስላላመንህ ይህ ነገር እስከሚሆን ቀን ድረስ ድዳ ትሆናለህ፣ መናገርም አትችልም” በማለት ነግሮታል። (ሉቃስ 1:13, 18-20) መልአኩ የተናገረው የዘካርያስ የመናገር ችሎታ እክል እንደሚደርስበት እንጂ የመስማት ችሎታው እንደሚታወክ አይደለም።

በተጨማሪም ታሪኩ “[ከመቅደስ] በወጣም ጊዜ [ይጠብቁት ለነበሩት ሕዝብ] ሊነግራቸው አልቻለም። በቤተ መቅደስም ራዕይ እንዳየ አስተዋሉ። እርሱም ይጠቅሳቸው ነበር፤ ድዳም ሆኖ ኖረ” ይለናል። (ሉቃስ 1:22) እዚህ ላይ “ድዳ” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክኛ ቃል በንግግር፣ በመስማት ወይም በሁለቱም የመደነዝን ሐሳብ ያስተላልፋል። (ሉቃስ 7:22) ታዲያ ስለ ዘካርያስ ምን ሊባል ይቻላል? በዳነ ጊዜ የሆነውን አስተውሉ፦ “ያን ጊዜ አፉ ተከፈተ፣ መላሱም ተፈታ፣ እግዚአብሔርንም እየባረከ ተናገረ”። (ሉቃስ 1:64) ይህም ጉዳት የደረሰበት የዘካርያስ የመናገር ችሎታ ብቻ ነበር ወደሚለው ምክንያታዊ አመለካከት ያደርሰናል።

ታዲያ ሰዎች ዘካርያስን “[ልጁ] ማን ሊባል እንደሚወድ የጠቀሱት ለምንድነው? አንዳንድ ተርጓሚዎች ይህን “ጠቀሱት” የሚለውን ቃል “በምልክት ቋንቋ” ወይም “በምልክት ቋንቋ ተጠቅመው” ብለው ተርጉመውታል።

መልአኩ ካበሠረው ጊዜ ጀምሮ ድዳ ሆኖ የኖረው ዘካርያስ ሐሳቡን ለመግለጽ የምልክት ቋንቋ የሚመስል የሰውነት እንቅስቃሴ ለመጠቀም ተገዶ ነበር። ለምሳሌ ያህል ዘካርያስ በቤተ መቅደስ ደጅ ይጠብቁት ለነበሩት ሰዎች “ይጠቅሳቸው ነበር።” (ሉቃስ 1:21, 22) ቆይቶም ብራና እንዲሰጡት ሲለምናቸው ምልክቶችን ወይም የሰውነት እንቅስቃሴዎችን ተጠቅሞ መሆን አለበት። (ሉቃስ 1:63) ስለዚህ ድዳ በነበረበት ጊዜ በአጠገቡ የነበሩ ሰዎችም በሰውነት እንቅስቃሴ ወደ መጠቀም አዘንብለው ሊሆን ይችላል።

ይሁን እንጂ በሉቃስ 1:62 ላይ ለተጠቀሰው ጥቅሻ የበለጠ ማብራሪያ አለ። ኤልሳቤጥ የልጅዋ ስም ማን መሆን እንዳለበት ቀደም ሲል ገልጻለች። ስለዚህ እሷን ሳይቃወሙ የባሏን ውሳኔ ለማግኘት የሚያስችላቸውን ተገቢ እርምጃ መውሰዳቸው ነበር። ይህንንም ለመጠየቅ ራሳቸውን መነቅነቅ ብቻ ወይም በሰውነት እንቅስቃሴ ምልክት ማሳየት ብቻ ይበቃቸው ነበር። ዘካርያስ ጥያቄያቸውን እንዲያነበው በጽሑፍ አለማቅረባቸው ራሱ የሚስቱን ቃል እንደሰማ ማስረጃ ሊሆን ይችላል። በመሆኑም ራስ በመነቅነቅም ሆነ በሌላ ተመሳሳይ ምልክት ለዘካርያስ ያሳዩት ጥቅሻ ‘እንግዲህ ሁላችንም [ዘካርያስም ጭምር] የሷን አስተያየት ሰምተናል፤ ስለ ልጁ ስም የአንተ ውሳኔስ ምንድነው?’ የማለት ያህል ነበር።

ወዲያውኑም ሁኔታውን የሚለውጥ ሌላ ተአምር ተፈጸመ። “ያን ጊዜም አፉ ተከፈተለት፣ መላሱም ተፈታ፣ እግዚአብሔርንም እየባረከ ተናገረ።” (ሉቃስ 1:64) የመስማት ችሎታው ታውኮ ስላልነበረ መስማት ስለመቻሉ መናገር አላስፈለገም።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ