መታወስ የሚገባው ቀን
ኢየሱስ መሞቱ በፊት በነበረው ምሽት አንድ ኅብስትና አንድ ጽዋ ወይን ጠጅ ከሐዋርያቱ ጋር ተካፍሎ ከበላና ከጠጣ በኋላ “ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት” አላቸው።—ሉቃስ 22:19 በዚህ ዓመት ይህ ቀን በኢየሱስ ትዕዛዝ መሠረት የሚታሰበው ሚያዝያ 17 ቀን ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ነው።
በዚህም ምክንያት በዓለም በሙሉ የሚገኙ የይሖዋ ምሥክሮች በዚህ ልዩ ምሽት ተሰብስበው ይህንን መታሰቢያ ኢየሱስ ባዘዘውና ባከበረው መንገድ ያከብሩታል። ከእኛ ጋር ተሰብስባችሁ እንድታከብሩ ከልብ እንጋብዛችኋለን። ስብሰባው የሚደረግበትን ትክክለኛ ጊዜና ቦታ ለማወቅ በአካባቢያችሁ የሚገኙትን የይሖዋ ምሥክሮች ጠይቁ።