እንደጠበቅከው ሳይሆን በመቅረቱ ምክንያት አታዝንም
በፊሊፒንስ የሚኖሩ ባልና ሚስት በቦታው ለመገኘት ሁለት ቀን ፈጅቶባቸዋል። ሁለት ትንንሽ ልጆቻቸውን ይዘው ጎጂ ነፍሳት በበዙበት ጫካ ውስጥ በኃይለኛ ዝናብ የሞሉ ወንዞችን እያቋረጡ 70 ኪ.ሜ. መጓዝ ነበረባቸው። ይሁን እንጂ እንዳያመልጣቸው ቆርጠዋል።
በዛየር የሚኖሩ ሁለት ሴቶችም በቦታው ለመገኘት ከ500 ኪ.ሜ. የሚበልጥ ርቀት ለ14 ቀናት በእግር ተጉዘዋል። በዚሁ በዛየር አንድ የ70 ዓመት አዛውንት 260 ኪ.ሜ. በብስክሌት ተጉዘው ደርሰዋል። የመንገዱ ርዝመትና አስቸጋሪነት እንዲያስቀራቸው አልፈለጉም። ትልቁ አስፈላጊ ጉዳይ አለመቅረታቸው ነበር።
እነዚህ ሁሉ የተጓዙት ወዴት ነበር? በየአገራቸው በተዘጋጀው የይሖዋ ምሥክሮች ትልቅ ስብሰባ ላይ ለመገኘት ያደረጉት ጉዞ ነበር። ጉዞአቸው ምንም ያህል አስቸጋሪ ቢሆን ጥረታቸው አለፍሬ እንዳልቀረ ሁሉም ተሰምቶአቸው ነበር።
እርስዎስ በ1992 በሚደረገው “ብርሃን አብሪዎች” የወረዳ ስብሰባ ላይ ለመገኘት ከአሁኑ እቅድ አውጥተዋልን? በስብሰባው ላይ ለመገኘት እነዚህ ታማኝ ሰዎች ያደረጉትን የመሰለ ከባድ ጥረት ማድረግ ላያስፈልግዎት ይችላል። ቢሆንም ምንም ዓይነት አስቸጋሪ ሁኔታ ቢያጋጥምዎት ስብሰባው እንዳያመልጥዎት እናበረታታዎታለን።
እጅግ ጥሩና በጣም ተግባራዊ የሆኑ ፕሮግራሞች ተዘጋጅተዋል። ከክርስቲያኖች ጋር አብሮ መዋል የሚያስደስትዎት ወይም እውነተኛ ሰላም እንዴት እንደሚገኝ፣ የወደፊቱ ጊዜ ምን ዓይነት ሁኔታዎችን እንደሚያመጣ፣ ወይም የአምላክን ፈቃድ እንዴት እንደሚያደርጉ ለማወቅ የሚፈልጉ ከሆነ የፈለጉትን እንደሚያገኙ ቃል እንገባልዎታለን። በቅርብዎ የሚደረገው ስብሰባ መቼና የት እንደሚደረግ በአካባቢዎ የሚኖር ማንኛውም ምሥክር ሊነግርዎት ይችላል።