የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w92 7/1 ገጽ 20
  • ከምሥራቅ አውሮፓ የተገኘ መልካም ዜና

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከምሥራቅ አውሮፓ የተገኘ መልካም ዜና
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ‘ከሕፃናት አፍ’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • ሴቶች የማይወዱኝ ለምንድን ነው?
    ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች፣ ጥራዝ 1
  • ሴቶች የማይወዱኝ ለምንድን ነው?
    ንቁ!—2009
  • አምላክ ‘ለስሙ ያሳያችሁትን ፍቅር አይረሳም’
    መጠበቂያ ግንብ—1993
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
w92 7/1 ገጽ 20

የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች ሪፖርት

ከምሥራቅ አውሮፓ የተገኘ መልካም ዜና

በምሥራቅ አውሮፓ በሚገኘው ቲኦክራቲካዊ መስክ ብዙ አስደሳች ነገሮች እየተፈጸሙ ናቸው። በ1991 ከነሐሴ 16-18 በዛግሬብ የተደረገው ብሔራት አቀፍ ስብሰባ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ነው። 7,300 የሚሆኑት ምስክሮች ከ15 አገሮች ለመጡት ወንድሞቻቸው ልባዊ አቀባበል አድርገውላቸው ነበር። በጠቅላላው በስብሰባው ላይ የተገኙት 14,684 ሰዎች ነበሩ። እረፍት አጥታ በምትናወጠው በዚህች አገር ይህን የመሰለ ፍቅርና አንድነት መታየቱ በጣም የሚያስደንቅ ነበር።

በምሥራቅ አውሮፓ የሚኖሩ ምስክሮች እውነተኛ ሰላም የምታስገኝ ብቸኛዋ የሰው ልጆች ተስፋ ስለሆነችው የይሖዋ መንግሥት በትጋት ለሰዎች በመናገር ላይ ናቸው። በአንዳንድ አካባቢዎች በገለልተኝነት አቋማቸው መጽናት አስቸጋሪ ሆኖባቸዋል። ቢሆንም ብዙ ሰዎች መልእክታቸውን ያዳምጣሉ። ጥሩ ተሞክሮዎች እንዳገኙም ሪፖርት ያደርጋሉ።

አንዲት የይሖዋ ምሥክር ብቻ በምትኖርበት በአንድ ከተማ አንዲት የ16 ዓመት ልጃገረድ ከዚህች እህት እውነትን ሰማች። የዘወትር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ተጀመረላትና ለእውነት የነበራት አድናቆት እያደገ መጣ። የተማረቻቸውን አስደናቂ ነገሮች ለሌሎች ለማካፈል ትልቅ ፍላጎት ስለነበራት ለትምህርት ቤት ጓደኞቿ ልትነግራቸው ሞከረች። ይሁን እንጂ እያሾፉ ተቃወሙአት። በተለይ አንደኛዋ ተማሪ በጣም ትቃወማት ነበር። ይሁን እንጂ ወጣቷ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪ ይህ ሁሉ ስድብ ሲደርስባት ከመቆጣት ይልቅ ባሳየችው ትዕግሥት በጣም ልትገረምና ልትነካ ቻለች። ቆይቶም ለዚህች ልጅ ሰፋ ያለ ተጨማሪ ምስክርነት ተሰጣትና አመለካከቷ ትክክል እንዳልነበረ ተገነዘበች። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ተጀመረላት። የመጀመሪያዋ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪና ይህች ጓደኛዋ ከወላጆቻቸው፣ ከአስተማሪዎቻቸውና ከትምህርት ቤት ጓደኞቻቸው ተቃውሞ ቢደርስባቸውም ይህን ደስታቸውን ለሌሎች ለማካፈል ሞከሩ።

በሰጡት ምስክርነት ምክንያት ሌላዋ የትምህርት ቤት ጓደኛቸው እውነትን ተቀበለች። አሁን ክፍላቸው ውስጥ ሦስት ሆኑ። ሦስቱም በፈቃደኝነት ሌሎችን በመርዳትና እርስ በርስ በመዋደድ ረገድ ጥሩ ምሳሌ ሆኑ። ከዚያም ሌላዋ ልጅ ከነሱ ጋር ተባበረች።

አሁን በትምህርት ቤታቸው ግቢ ውስጥ ሆነው ስለ መጽሐፍ ቅዱስ በሚወያዩበት አግዳሚ ወንበር ላይ አራት ሆነው መቀመጥ ጀመሩ። ሌሎችን በሚያስገርም ሁኔታ ቁጥራቸው እየጨመረ መጣ። ሌላም የክፍላቸው ልጅ በመልካም ጠባያቸው ደስ በመሰኘቷ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቱ ለመካፈል ወሰነች። አምስቱም ሌሎች ተማሪዎችና አስተማሪዎች በውይይታቸው እንዲካፈሉ መጋበዛቸውን ቀጠሉ። ይህም ሆኖ ልጃገረዶቹ ከወላጆቻቸው ከባድ ተፅዕኖ ይደርስባቸው ነበር። ወላጆቻቸው ጽሑፎቻቸውን በማጥፋትና እነሱንም በማሠቃየት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታቸውን እንዲያቆሙ ለማስገደድ ከባድ ጥረት አድርገው ነበር።

በአንዲት ፍላጎት ባሳየች ወጣት የተጀመረው ይህ ምስክርነት ምን ውጤት አስገኘ? ከመካከላቸው አንዷ በ1990 በተደረገው የወረዳ ስብሰባ ላይ ስትጠመቅ አራቱ ደግሞ በ1991 የጸደይ ወራት በተደረገው የክልል ስብሰባ ላይ ተጠመቁ። በዚህም ምክንያት ከፍተኛ ደስታ ተገኝቶአል። ዛሬ አምስቱም ወጣት ልጃገረዶች በዘወትር አቅኚነት እያገለገሉ ናቸው! ይህ በተፈጸመበት ከተማ አሁን 11 አስፋፊዎች ሲኖሩ 8ቱ አቅኚዎች ናቸው።

ይሖዋ በምሥራቅ አውሮፓ የሚገኙትን ምስክሮቹን እየደገፈና እየባረካቸው ነው። በዚህ የዓለም ክፍል በሚገኙ በነዚህ ቅን ልብ ባላቸው ሰዎች መካከል ብዙ ጭማሪ ለማስገኘት የሚያስችል አጋጣሚ መኖሩ ግልጽ ነው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ