የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w92 7/1 ገጽ 24-25
  • የአይሁዶችና የግሪካውያን መገናኛ ጌርጌሴኖን

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአይሁዶችና የግሪካውያን መገናኛ ጌርጌሴኖን
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የገሊላን ባሕር መጥታችሁ ጎብኙ!
    መጠበቂያ ግንብ—1993
  • ለ10 እስራኤል በኢየሱስ ዘመን
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • ገለዓድ የደፋር ሰዎች ምድር
    መጠበቂያ ግንብ—1993
  • ግሪክኛ በሚነገርባቸው አገሮች የነበሩት የጥንቶቹ ክርስቲያኖች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
w92 7/1 ገጽ 24-25

የተስፋይቱ ምድር ገጽታዎች

የአይሁዶችና የግሪካውያን መገናኛ ጌርጌሴኖን

ሐዋርያው ጳውሎስ በእውነተኛው የአብርሃም ዘሮች መካከል “አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም” ሲል ጽፏል። (ገላትያ 3:26-29) አዎን፣ በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት በማግኘት ረገድ ብሔር ወይም ባህል ምንም ዓይነት ልዩነት አያመጣም።

እነዚህ ቃላት አይሁዶች፣ ግሪካውያን፣ ሮማውያንና የሀገሬው ተወላጆች ተደባልቀው በሚገኙባቸው እንደ ገላትያ ክፍለ ሀገር ባሉት የሮማ ጠቅላይ ግዛቶች ተበታትነው ለሚኖሩት ክርስቲያኖች የሚስማሙ ናቸው። ይሁን እንጂ የእስራኤል ምድር ክፍል በሆኑት እንደ ገልዓድ ያሉ አካባቢዎች ለሚኖሩትስ?

ይህ አካባቢ የሚገኘው ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምስራቅ በጨው (በሙት) ባህርና በገሊላ ባህር መካከል ነው። የያቦቅ ወንዝ በዚህ ለም በሆነ ፕላቶ መሐል ለመሐል አልፎ ወደ ዮርዳኖስ ይገባል። ከላይ ያለው ፎቶግራፍ የሚያመለክተው በያቦቅ ወንዝ ላይኛ ክፍል የሚገኘውንና በአሁኑ ጊዜ ጄራሽ የሚባለውን የጀራሳ ወይም የጌርጌሴኖን ፍርስራሽ ነው።

ከሰሜን ወደ ደቡብ የሚያሳልፍ “የንጉሡ ጐዳና” የሚባል አንድ የነጋዴዎች መተላለፊያ መንገድ ገለዓድን ያቋርጣል። ያዕቆብና ቤተሰቡ ካራንን ለቀው ወደ ያቦቅ ሲሄዱ የተጓዙት በዚህ ጎዳና ነበር። በዚህም ሥፍራ ያዕቆብ ከመልአክ ጋር ታግሎአል። እንዲሁም ከዔሣው ጋር የተገናኘው ጌርጌሴኖን በተገነባበት አቅራቢያ ነው። (ዘፍጥረት 31:17-25, 45-47፤ 32:22-30፤ 33:1-17) ቆይቶም እስራኤላውያን ወደ ተስፋይቱ ምድር ሲያመሩ ከደቡብ ተነስተው የተጓዙት በንጉሡ ጐዳና ነበር። ሁለት ከግማሽ የሚሆኑት ነገዶችም የሠፈሩት ከያቦቅ በስተ ሰሜንና በስተ ደቡብ በጎዳናው ዳርና ዳር ነው።​—ዘኁልቁ 20:17፤ ዘዳግም 2:26, 27

ግሪካውያን ወደዚህ አካባቢ መጥተው ነበርን? ከመጡስ እንዴት ሊመጡ ቻሉ? አዎን፣ የመጡት ታላቁ እስክንድር ይህንን አካባቢ ወርሮ በያዘበት ጊዜ ነበር። የግሪኮች አፈ ታሪክ እንደሚለው ታላቁ እስክንድር ጌርጌሴኖንን የቆረቆረው ከጦር ሠራዊቱ የተገለሉትን የቀድሞ ወታደሮች ለማስፈር ነበር። ቀስ በቀስም የግሪካውያን ተጽዕኖ ተስፋፋ። ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ያሉት አሥሩ የቅኝ ግዛት ከተሞችም አንድ ኅብረት መስርተው ዲካፖሊስ (አሥር ከተማ) ተባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ “ከገሊላም ከአሥሩ ከተማም ከኢየሩሳሌምም ከይሁዳም ከዮርዳኖስም ማዶ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት” ብሎ በሚያቀርበው ዘገባ ላይ ይህንን ስም ሳታስተውል አትቀርም።​—ማቴዎስ 4:25

‘በግዛቶቹ ውስጥ ሁሉ ግሪካውያንን ማስገባት ከእስክንድር ዕቅዶች ውስጥ አንዱ ክፍል ነበር። በተለይ ታችኛው ሶርያ [ዲካፖሊስን ጨምሮ] ከስትራቴጂያዊ ማዕከሎች አንዱ እንደመሆኑ መጠን በዛ ያሉ ግሪካውያንን ተቀብሎአል። እስከ ዛሬ ድረስ ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ የሚገኘውን የሚያህል ብዙና አስደናቂ የግሪካውያን ፍርስራሽ የተገኘበት የምሥራቁ ዓለም ክፍል አይገኝም። በነዚህ የግሪክ ከተሞች የግሪካውያን ልማዶችና ባህሎች ሙሉ በሙሉ ተቋቁመውባቸው እንደነበሩ በቀላሉ የሚያሳዩ ለግሪካውያን ወንድና ሴት አማልክት የተሠሩ ዕፁብ ድንቅ ቤተ መቅደሶች፣ የስፖርት አዳራሾች፣ የሕዝብ መታጠቢያዎች፣ የጨዋታዎችና የዓመታዊ ክብረ በዓላት ማሳያዎች፣ እንዲሁም ብዙ የፍልስፍናና የቀለም ትምህርት ቤቶች ይገኛሉ።’​—ሔለኒዝም፣ በኖርማን ቤንትዊች

የጌርጌሴኖንን ፍርስራሽ ብትጎበኝ ለዚህ በቂ ማረጋገጫ ለማግኘት ትችላለህ። በሥዕሉ ላይ እንደሚታየው በደቡባዊው መግቢያ በኩል ክብ የሆነ አደባባይ ወይም ገበያ ይገኛል። የመታጠቢያ ገንዳዎቹን፣ ቤተ መቅደሶቹን፣ የቲያትር ቤቶቹን እንዲሁም አብዛኞቹ በተነጠፉና በዓምዶች በተከበቡ መንገዶች የተያያዙ የሕዝብ ሕንፃዎች ስትመለከት ልትደነቅ ትችላለህ። ከከተማው ውጭ ጌርጌሴኖንን ከሌሎች የአሥር ከተማ (ዲካፖሊስ) ከተሞችና በሜዲትራንያን ከሚገኙ ወደቦች ጋር በሚያገናኘው የጥንት መንገድ ዳርና ዳር የድንጋይ ምልክቶች ይገኛሉ።

በ63 ከዘአበ ሮም ጌርጌሴኖን ከተቆጣጠረች በኋላም እንኳን ቢሆን የግሪካውያን ባሕልና ልማድ ፈጽሞ አልጠፋም። ይህ የሔለናውያን ወይም የግሪካውያን ባሕልና ልማድ በጌርጌሴኖንና በአካባቢው በሚኖሩት አይሁዳውያን ላይ ምን ዓይነት ተጽእኖ እንዳሳደረ ልትገምት ትችላለህ። ሔለኒዝም የተባለው መጽሐፍ እንዲህ ሲል አትቷል፦ “አይሁዳውያን ቀስ በቀስ በዙሪያቸው የሚኖሩትን ሕዝቦች ሃይማኖታዊ አስተሳሰብ መቅዳትና ቅዱሳን ጽሑፎችን በእነዚህ አስተሳሰቦች አንጻር መመልከት ጀመሩ።”

ኢየሱስ በከተማው ውስጥ አልሰበከ ይሆናል፤ ቢሆንም እስከ ገሊላ ባህር ድረስ ሊደርስ ወደሚችለው ወደ ጌርጌሴኖን አውራጃ ደርሶ ነበር። በዚያም አውራጃ ከአንድ ሰው አጋንንትን አውጥቶ ወደ እሪያዎች እንዲገቡ አድርጎአል። (ማርቆስ 5:1-17) የመጀመሪያዎቹ ደቀ መዛሙርቱም በአሥሩ ከተሞች ይኖሩ ለነበሩት አይሁዶች፣ ከ36 እዘአ በኋላ ደግሞ በጌርጌሴኖን ይኖሩ ለነበሩት ግሪካውያን ምሥራቹን ሳይሰብኩ አልቀሩም። ክርስትናን የተቀበለው ሰው ይሁዲነትን አጥብቆ የሚከተል የነበረም ይሁን ወደ ሔለናዊነት የተለወጠ አይሁድ ወይም ግሪካዊ በእውነተኛው አምላክ ዘንድ ተቀባይነት ሊያገኝና የአብርሃም መንፈሳዊ ዘር ክፍል ሊሆን ይችላል።

[በገጽ 24 ላይ የሚገኝ ካርታ]

(መልክ ባለው መንገድ የተቀናበረውን ለማየት ጽሑፉን ተመልከት)

ዲኦን

ጌርጌሴኖን (ጀራሽ)

ፊልድልፍያ (ረባት)

የንጉሡ ጐዳና

ጨው ባህር

ኢየሩሳሌም

ዮርዳኖስ

ያቦቅ

ፔላ

ሲቶፖሊስ (ቤትሳን)

ጋዳራ

የገሊላ ባህር

[ምንጭ]

Based on a map copyrighted by Pictorial Archive (Near Eastern History) Est. and Survey of Israel.

[በገጽ 24 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ይህ ፎቶግራፍ በ1992 የይሖዋ ምሥክሮች ቀን መቁጠሪያ ላይ ጉልህ ሆኖ ይታያል

[በገጽ 25 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

Pictorial Archive (Near Eastern History) Est.

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ