የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w92 12/15 ገጽ 30
  • ታስታውሳለህን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ታስታውሳለህን?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • “አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • መጽሐፍ ቅዱስ ስለ አሥራት ምን ይላል?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • “መሲሕን አግኝተናል”!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • የይሖዋ በረከት ባለጠጋ ታደርጋለች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
w92 12/15 ገጽ 30

ታስታውሳለህን?

በቅርቡ የወጡትን የመጠበቂያ ግንብ እትሞች በማንበብ ተደስተህባቸዋልን? ከተደሰትክባቸው ቀጥሎ ያሉትን ነጥቦች ማስታወሱን አስደሳች ሆኖ እንደምታገኘው ምንም ጥርጥር የለውም፦

▫ በመጀመሪያው መቶ ዘመን በነበሩት የተለያዩ የመንፈስ ቅዱስ አሠራሮች ምን አሳማኝ ማስረጃዎችን ሰጥተዋል?

እነዚህ አሠራሮች አምላክ የ1,500 ዓመት ዕድሜ የነበረውን የእስራኤልን ጉባኤ ከዚያ ወዲያ እንደ ልዩ ሕዝቡ አድርጎ የሚጠቀምበት አለመሆኑን ሞገሱ ያለው ግን በአንድያ ልጁ አማካኝነት በተቋቋመው አዲሱ የክርስቲያን ጉባኤ ላይ መሆኑን የሚያስረዱ ተጨባጭ ማስረጃዎች ነበሩ። (ከዕብራውያን 2:2-4 ጋር አወዳድሩ።)—8/15፣ ገጽ 5

▫ የይሖዋ ምስክሮች ላገኙት ከፍተኛ ዕድገት ምክንያት የሆነው ምንድን ነው?

በመጀመሪያ ደረጃ ይህ ዕድገት የተገኘው በይሖዋ በረከት ምክንያት ነው። ሥራው የአምላክ ሥራ ነው። የይሖዋ ምስክሮች በወንጌላዊነት ሥራቸው ላይ የሚያስተምሩት ትምህርት በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ ነው። የተሳካ ውጤት የሚያገኙበት ሌላው ምክንያት አምላክ የጉባኤው ራስ አድርጎ ለሾመው ለጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሙሉ ዕውቅና ስለሚሰጡ ነው።—9/1፣ ገጽ 19

▫ ዳዊት ከቤርሳቤህ ጋር ለፈጸመው ከባድ ኃጢአት ይሖዋ ምሕረት ያደረገለት ለምን ነበር?

ዋነኛው ምክንያት የመንግሥት ቃል ኪዳን የተገባለት ሰው በመሆኑ ቢሆንም ዳዊት ራሱ መሐሪ በመሆኑና እውነተኛ ንስሐ በመግባቱም ጭምር ነበር። (1 ሳሙኤል 24:4-7፤ 2 ሳሙኤል 7:12፤ 12:13፤ መዝሙር 51:1, 2, 17)—9/15፣ ገጽ 10, 11

▫ የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን ጽሑፎች የኢየሱስን መሲሕነት በመደገፍ ምን ሦስት ዓይነት ማረጋገጫዎችን ይሰጣሉ?

የኢየሱስ የትውልድ ሐረግ የመጀመሪያው ማረጋገጫ ነው። (ማቴዎስ 1:1-16፤ ሉቃስ 3:23-38) ሌላው ማረጋገጫ የትንቢቶቹ መፈጸም ነው። ዳንኤል 9:25 ላይ እንዳለው ያሉ ኢየሱስን እንደ መሲሕ አድርገው የሚያሳውቁት ቃል በቃል የተነገሩ ትንቢቶች አሉ። ሦስተኛው የማረጋገጫ መስመር አምላክ ራሱ የሰጠው ምስክርነት ነው። ይህንንም በሦስት አጋጣሚዎች በራሱ ድምፅ አረጋግጧል። (ማቴዎስ 17:5፤ ሉቃስ 3:21, 22፤ ዮሐንስ 12:28)—10/1፣ ገጽ 10, 12

▫ ኢየሱስ በማቴዎስ 24:37 ላይ እንደተመዘገበው “የኖኅ ዘመን እንደነበረ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና” ብሎ ሲናገር ምን ማለቱ ነበር?

የጥፋት ውኃ ከመምጣቱና ያንን ብልሹ የዓለም ሥርዓት ጠራርጎ ከማጥፋቱ አስቀድሞ ኖኅ ለብዙ አሥር ዓመታት መርከብ ይሠራና ክፉዎችን ያስጠነቅቅ ነበር። በተመሳሳይም የክርስቶስ የማይታይ መገኘትም በታላቅ ጥፋት ከመደምደሙ በፊት ለጥቂት አሥር ዓመታት ይቆያል። በዚያ ጊዜ ውስጥም ዓለም አቀፍ ምሥክርነት ይሰጣል።—10/1፣ ገጽ 16

▫ ጥሩ የቤተሰብ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዲኖር ከሚያስፈልጉት ነገሮች ውስጥ አንዳንዶቹ ምን ምን ናቸው?

ጊዜያችን በቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ወይም በሌሎች የጊዜ ማሳለፊያዎች እንዲጣበብ ባለመፍቀድ ለጥናቱ ጊዜን መዋጀት አለብን። በተለይ ለቤተሰቡ የሚያስፈልገው ነገር ምን እንደሆነ ሊታሰብበት ይገባል። ልጆቹ የሚማሩትን ነገር በእርግጥ የተረዱት መሆኑን ለማወቅ በአመለካከት ጥያቄዎች ተጠቀሙ። (ማቴዎስ 17:25) የጥናቱን መንፈስ የተዝናና አድርጉት። ሞቅ ባለ ስሜት የምትናገሩ በመሆን ሁሉም በውይይቱ እንዲሳተፉ አድርጉ።—10/15፣ ገጽ 17

▫ የደም ተዋፅዖዎች በምግብ ውጤቶች ውስጥ ተጨምረው ሊሆን ይችላል የሚለው ስጋት ክርስቲያኖችን ምን ያህል ሊያሳስባቸው ይገባል?

ክርስቲያኖች ይሆናል በሚል ጥርጣሬ ወይም በወሬ ከመረበሽ መጠበቅ ይኖርባቸዋል። ሆኖም በአካባቢው በምግብም ይሁን በሕክምና ውስጥ ደምን በስፋት እንደሚጠቀሙበት በእርግጠኝነት ከታወቀ ከደም እንዲርቁ የሚያሳስባቸውን የአምላክን ትዕዛዝ ለመታዘዝ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል። (ሥራ 15:28, 29)—10/15፣ ገጽ 30-31

▫ የምሳሌ መጽሐፍ በእስራኤል ውስጥ የነበሩትን የማስተማሪያ ዘዴዎች መንፈሳዊ ጥልቀት ያጎላው እንዴት ነው?

የምሳሌ መጽሐፍ የትምህርቱ ዓላማ “ተሞክሮ የጎደላቸውን ሰዎች” እንደ ጥበብ፣ ተግሣጽ፣ መረዳት፣ ማስተዋል፣ ፍትህ፣ ብልሃት፣ እውቀትና የማሰብ ችሎታ ያሉትን ከፍ ያሉ ነገሮች ‘ይሖዋን ከመፍራት’ ጋር ለማስተማር ነበር። (ምሳሌ 1:1-7፤ 2:1-14)—11/1፣ ገጽ 12

▫ በዛሬው ጊዜ ያሉ ወጣቶች ትምህርትን በሚመለከት ሊይዙት የሚገባ ሚዛናዊ አመለካከት ምንድን ነው?

ክርስቲያኖች ትምህርትን የሚመለከቱት ተፈላጊውን ግብ ለማሳካት እንደሚረዳ አድርገው መሆን ይኖርበታል። በእነዚህ የመጨረሻ ቀኖች ዓላማቸው የሚቻለውን ያህል ውጤታማ በሆነ መንገድ የሚችሉም ከሆነ በሙሉ ጊዜ አገልጋይነት ይሖዋን ማገልገል ነው።—11/1፣ ገጽ 18

▫ ይሖዋ የእስራኤል ሕዝቦች አሥራትን እንዲያወጡ ይጠይቅባቸው የነበረው ለምን ነበር?

በመጀመሪያ ደረጃ ለይሖዋ ደግነት ያላቸውን አድናቆት ተጨባጭ በሆነ መንገድ ለማሳየት እንዲችሉ ነው። ሁለተኛ ሕጉን ማስተማርን በሚጨምረው ግዴታቸው ላይ ማተኮር ይችሉ ዘንድ ለሌዋውያን ድጋፍ እንዲሰጡ ነበር። (2 ዜና መዋዕል 17:7-9⁠ን ተመልከት።)—12/1፣ ገጽ 9

▫ ክርስቲያኖች እንዲያመጡ የተጋበዙት አሥራት ምንድን ነው? (ሚልክያስ 3:10)

ይህ አሥራት ለይሖዋ የምናመጣለትን ወይም ለአገልግሎቱ የምናውለውን የእኛ የሆነ ነገር ይወክላል። ይህም ለእርሱ ላለን ፍቅርና እኛም የእርሱ መሆናችንን ለመገንዘባችን ምልክት ነው።—12/1፣ ገጽ 15

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ