የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w93 4/15 ገጽ 32
  • በይሖዋ ቤት የተገኘ የሮማን በትር

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በይሖዋ ቤት የተገኘ የሮማን በትር
  • መጠበቂያ ግንብ—1993
መጠበቂያ ግንብ—1993
w93 4/15 ገጽ 32

በይሖዋ ቤት የተገኘ የሮማን በትር

የመሬት ቁፋሮ ተመራማሪዎች በእስራኤል ምድር ብዙ ዓይነት ባለሥልጣኖች ይይዙአቸው የነበሩ በትሮችን ወይም በትረ መንግሥቶችን አግኝተዋል። (ዘፍጥረት 49:​10፤ አስቴር 8:​4፤ ሕዝቅኤል 19:​14) በለኪሶ የተገኙት አንዳንድ በትረ መንግሥቶች አናታቸው የሮማን ቅርጽ ያለው ነው። የአምላክ ሕዝቦች ይህን ፍሬ በሚገባ ያውቁት ነበር። — ዘዳግም 8:​8፤ መኃልየ መኃልይ 4:​13

በስተግራ የሚታየለው የፈነዳ ሮማን የሚመስለው የዝሆን ጥርስ የተገኘው በቅርብ ጊዜ ነው። የ43 ሚሊ ሜትር ቁመት ያለው ሲሆን ከሥሩ ቀዳዳ ያለው መሆኑ የበትረ መንግሥት አናት እንደነበረ ያመለክታል። በስምንተኛው መቶ ዘመን ከዘአበ በፊት በጥንታዊው የዕብራይስጥ አጻጻፍ የተጻፈውን ፊደል ልብ በሉ።

የዝሆን ጥርሱ በከፊል የተሰበረው በጥንት ዘመን ስለነበረ ጥቂት ፊደላት ጎድለዋል። ቢሆንም የጥንት ጽሑፎች ሊቃውንት ከታች የሚታየውን ይመስል ነበር የሚል ሐሳብ አቅርበዋል። በፊደሎቹ መካከል ያለው ባዶ ቦታ አንድ ዓይነት ባለመሆኑ ምክንያት ሁለት ዓይነት አነባበቦች ቀርበዋል። ኦንድሬ ለሜር የተባሉት ፈረንሣዊ ምሑር “ለካህናት ቅዱስ የሆነ የጌታ [የያህዌህ] ቤተ መቅደስ” የሚል ንባብ እንዳለው ገልጸዋል። ናማን አቪጋድ ደግሞ “ለያህዌህ ቤት ካህናት የተሰጠ ቅዱስ ስጦታ” ተብሎ መነበብ አለበት የሚል ሐሰብ አቅርበዋል።

እነዚህም ሆኑ ሌሎች ምሑራን ጥንት በበትረ መንግሥቱ ላይ ይሖዋ የተባለውን የአምላክ ስም የሚወክሉ አራት የዕብራይስጥ ፊደላት እንደነበሩ ደምድመዋል። ስለዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን የተለመደውን “የይሖዋ ቤት” የሚል ሐረግ መጥቀሱ ተገቢ ነው። — ዘጸአት 23:​19፤ 1 ነገሥት 8:​10, 11

ስለዚህ ይህ የበትረ መንግሥት አናት ሰለሞን በሠራው ቤተ መቅደስ ያገለግል የነበረ ካህን በትር እንደነበረ ወይም ለዚህ ቤተ መቅደስ የተሰጠ ስጦታ እንደሆነ የሚያምኑ ምሑራን ብዙ ናቸው። በአምላክ ቤተ መቅደስ ውስጥ የሮማን ቅርጽ በብዛት መኖሩ ሊስተዋል የሚገባው ነው። — ዘጸአት 28:​31–35፤ 1 ነገሥት 7:​15–20

[ምንጭ]

Israel Museum, Jerusalem

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ