የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w93 5/1 ገጽ 3-4
  • መጽሐፍ ቅዱስ ያስፈልገናልን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መጽሐፍ ቅዱስ ያስፈልገናልን?
  • መጠበቂያ ግንብ—1993
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ተቺዎችና ተጠራጣሪዎች
  • የመመሪያ አስፈላጊነት
  • ብቸኛ አማራጭ
  • እምነት የሚጣልበት አመራር ከየት ልታገኝ ትችላለህ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • በዚህ ንቁ! መጽሔት ውስጥ፦ መጽሐፍ ቅዱስ የተሻለ ሕይወት ለመምራት ይረዳናል?
    ንቁ!—2019
  • መጽሐፍ ቅዱስ ለዘመናዊው ሰው የሚሆን ተግባራዊ መመሪያ
    መጠበቂያ ግንብ—1993
  • መጽሐፍ ቅዱስና አንተ
    መጽሐፍ ቅዱስ—የአምላክ ቃል ነው ወይስ የሰው?
ለተጨማሪ መረጃ
መጠበቂያ ግንብ—1993
w93 5/1 ገጽ 3-4

መጽሐፍ ቅዱስ ያስፈልገናልን?

ኦክሳና የምትባል አንዲት ወጣት ሩሲያዊት ሴት ሞስኮ ውስጥ በመንገድ ዳር መጻሕፍት የሚሸጥ ሰው መጽሐፍ ቅዱስ ደርድሮ በተመለከተች ጊዜ በጣም ተደሰተች። መጽሐፍ ቅዱስ እንደልብ ከሚገኝበት አገር የመጣው አብሯት የነበረው ጆን የኦክሳና ጉጉት አስገረመው። “እኔ አምላክ የለሽ ብሆንም መጽሐፍ ቅዱሱን ልገዛላት ፈለግሁ“ በማለት ተናገረ። ኦክሳና መጀመሪያ ላይ የጆንን ስጦታ አልፈልግም ብትልም በኋላ ግን ተቀብላለች።

እንደ ኦክሳና ያሉ ብዙዎች መጽሐፍ ቅዱስ እንዲኖራቸው በጣም ይመኛሉ። በተለይ መጽሐፍ ቅዱስ እንዳይሰራጭ ለብዙ ዓመታት ታግዶ በኖረባቸው አገሮች እንደዚህ ያለ ሁኔታ አለ። ለምሳሌ ያህል የዚህ መጽሔት አዘጋጆች በቀድሞዋ ሶቪየት ኅብረት ሪፑብሊክ አገሮችና በሌሎችም የዓለም ክፍሎች ያሉ ሰዎች ያላቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ፍላጎት ለሟሟላት ጠንክረው በመሥራት ላይ ናቸው። በእነዚህ አካባቢዎች ያሉ ብዙ ሰዎች ተገቢ የመጽሐፍ ቅዱስ ምርምር ለማድረግ አጋጣሚ ያገኙት ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን ብዛት ያላቸው ሰዎች በኃይለኛ መልእክቶቹ እየተሳቡ ነው።

ተቺዎችና ተጠራጣሪዎች

ከዚህ በተቃራኒ ደግሞ በተለይ በሰሜን አውሮፓ መጽሐፍ ቅዱስ በመጽሐፍ መደርደሪያ ላይ ተቀምጦ አቧራ እንዲለብስ ተትቷል። “ያለፈ ታሪክ ነው!“ ይላሉ። አንዳንዶች አክለውም “ለሌላ [ለቀድሞ] ዘመን የተጻፈ ነው። ለዘመናዊው ሰው ምንም አያደርግለትም“ ይላሉ። እውቅ ካህናትም እንኳን ሳይቀሩ መጽሐፍ ቅዱስና የሚያዋርድ ብዙ ነገር በሕዝብ ፊት ተናግረዋል። የአንግሊካን ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ዴዝሞንድ ቱቱ ዘ ስታር በተባለ የደቡብ አፍሪካ ጋዜጣ ላይ “ዘላቂ ጥቅም የሌላቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች አሉ“ ብለው እንደተናገሩ ተዘግቧል። እንደዚህ ያሉ አባባሎችን የሰሙ ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ የቱን ያህል እምነት ሊጥሉበት እንደሚገባ የሚያሳስብ ጉዳይ ሆኖባቸዋል።

የመመሪያ አስፈላጊነት

የመጽሐፍ ቅዱስ ተቺዎችም ሆኑ አማኞች ዓለም ከምን ጊዜውም የበለጠ አሁን ሊሠሩ የሚችሉ መፍትሔዎች እንደሚያስፈልጓት መቀበል ይኖርባቸዋል። “ሰው በግል ጉዳዮቹና እንዲሁም በአጠቃላይ በኅብረተሰቡ ውስጥ ለውጦች የሚደረጉበትን ፍጥነት መቆጣጠር ካልተማረ በቀር“ ይላሉ አልቨን ቶፍለር ፊውቸር ሾክ በተሰኘው መጽሐፋቸው ውስጥ “ከፍተኛ . . . መፈራረስ ተደቅኖብናል።“ ያ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው ከ20 ዓመታት በፊት ነበር። ቶፍለር የተናገሩለት መፈራረስ አሁን እየታየ ነው።

ይህ መቶ ዘመን ወደ መጨረሻው እየተቃረበ ሲሄድ ቴክኖሎጂያዊ እድገቶችና ሰብአዊ ፍልስፍናዎች ለዓለም መረጋጋትና ለማስገኘት ሳይችሉ ቀርቷል። የብዙ ሰዎች ሕይወትም በማሽቆልቆል የዕለት ጉርስ ለማግኘትና በሕይወት ለመኖር ከፍተኛ ትግል የሚያስፈልገው ሆኗል።

በሀብታሞችና በድሆች መካከል ያለው የኢኮኖሚ ልዩነት የገደል ያህል የሰፋ ሆኗል። በቅርብ ጊዜ የተደረገ ጥናት 827 በመቶ የሚሆነው የዓለም ሀብት 20 በመቶ በሚያህሉት የዓለም ሕዝቦች እጅ ብቻ እንደተከማቸ ያመለክታል። ታዲያ በብዙ አገሮች ጦርነት፣ ረሀብ፣ በሽታ፣ ረብሻና ሥርዓተ አልበኝነት መብዛቱ ያስደንቃልን? የኑሮ ደረጃ እየተበላሸ መሄዱ የሚያመጣው ተጽእኖ በብዙ ሰዎች ስሜት ላይ ትልቅ ጭንቀት አስከትሏል። በውጤቱም በጣም መሠረታዊ የኅብረተሰብ ክፍል የሆነው ቤተሰብም እንኳን እየተዳከመ ሄዷል።

ምንም እንኳን እንደ ቶፍለር ያሉ ብዙ ሰዎች “ራስን ለማረጋጋትና ዋስትና ለማግኘት የሚያስችሉ ፈጽሞ አዲስ የሆኑ መንገዶችን መፈለግ“ የሰው የራሱ ኃላፊነት እንደሆነ ሐሳብ ቢያቀርቡም ማስረጃው ግን የሚረጋገጠው ሰዎች ለራሳቸው መፍትሔ ለማቅረብ አለመቻላቸውን ነው።

ብቸኛ አማራጭ

ከ3,500 ዓመታት በፊት መጻፍ የጀመረው መጽሐፍ ቅዱስ በመቶዎች በሚቆጠሩ ዘመናት ሁሉ አልተለወጠም። መሠረታዊ ሥርዓቶቹ ሳይለዋወጡ ኖረዋል። ለምሳሌ ያህል “አቤቱ፣ የሰው መንገድ ከራሱ እንዳይደለ አውቃለሁ፣ አካሄዱንም ለማቅናት ከሚራመድ ሰው አይደለም“ የሚሉት የኤርምያስ 10:23 ቃላት ከምንጊዜውም የበለጠ ዛሬ እውነት መሆናቸው ተረጋግጧል። ሰዎች አካሄዳቸውን ለማቅናት ካልቻሉ ማን ሊያቀናላቸው ይችላል? መጽሐፍ ቅዱስ ብቸኛውን የአመራር ምንጭ እንደሚከተለው በማለት ይገልጸዋል፦ “እኔ የሚረባህን ነገር የማስተምርህ በምትሄድባትም መንገድ የምመራህ አምላክህ እግዚአብሔር [ይሖዋ አዓት] ነኝ።“​—(ኢሳይያስ 48: 17,18)

ይሖዋ አምላክ በመጽሐፍ ቅዱስ ገጾች አማካኝነት ራሳችንን እንድንረዳ ያስተምረናል። መጽሐፉ የምንሄድበትን መንገድ በሚያሳዩን ምክሮች የተሞላ ነው። ምክሩ በተጻፈበት ዘመን ጠቃሚ የነበረውን ያህል በአሁኑ ጊዜም ጠቃሚ ነው። የሚቀጥለው ርዕሰ ትምህርት መጽሐፍ ቅዱስ ለዘመናችን ያለውን ተግባራዊነት ይመረምራል። ሲረግጡት እንደሚከዳ አሸዋ በሆነው በዛሬው ዓለም ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስ ከጤንነትና ከሀብት ጀምሮ እስከ ቤተሰብ ሕይወትና የግል ጠባይ ድረስ ባሉ ልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ እንደ ዓለት የጸና መሆኑን ልትመለከቱ ትችላላችሁ።

[በገጽ 4 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

መጽሐፍ ቅዱስ ተነዋዋጭ በሆነው በዛሬው ዓለም ውስጥ አስተማማኝ መልሕቅ ነው

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ