የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w94 9/15 ገጽ 8-9
  • የይሖዋ ምሥክሮች በዓለም ዙሪያ ናይጄሪያ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የይሖዋ ምሥክሮች በዓለም ዙሪያ ናይጄሪያ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ወጣቶች አቅኚ እየሆኑ ነው
  • የቪድዮ ካሴቱና የመንግሥት አዳራሹ
  • የይሖዋ ምስክሮች—ከስሙ በስተጀርባ ያለው ድርጅት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • ያሳየችው ድፍረት ክሷታል
    ንቁ!—2002
  • ምሥክርነት ለመስጠት የሚረዱት የቪዲዮ ፊልሞች በሰዎች ላይ እያሳደሩ ያሉት በጎ ተጽዕኖ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2002
  • በአቅኚነት አገልግሎት ተጨማሪ ወንድሞች ያስፈልጋሉ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
w94 9/15 ገጽ 8-9

የይሖዋ ምሥክሮች በዓለም ዙሪያ ናይጄሪያ

ናይጄሪያ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ በሚገኘው የምዕራብ አፍሪካ ክፍል እንደ ሽብልቅ ተሰክታ የምትገኝ አገር ነች። በጊኒ ባሕረ ሰላጤ ላይ በስተሰሜን በኩል ከምድር ወገብ አጠገብ የምትገኝ ሲሆን ከ88 ሚልዮን በላይ ነዋሪዎች አሏት።a

ባለፉት ሁለት የአገልግሎት ዓመታት በናይጄሪያ የሚገኘው የመጠበቂያ ግንብ ቅርንጫፍ ቢሮ ለወጣቶች ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ነበር። በይሖዋ ምሥክሮች ጉባኤዎች ውስጥ የተደረገ አንድ ጥናት በናይጄሪያ ውስጥ በ1992 የምሥራቹን መስበክ ከጀመሩት መካከል 80 በመቶ የሚሆኑት ከ10 እስከ 20 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን ይጠቁማል። በዚሁ ዓመት ከተጠመቁት መካከል 63 በመቶ የሚሆኑት በዚሁ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው።

ወጣቶች አቅኚ እየሆኑ ነው

ብዙ ወጣቶች አቅኚዎች እየሆኑ በሙሉ ጊዜ የስብከት ሥራ እየተሰማሩ ናቸው። ሀና የተባለች አንዲት አቅኚ እንዲህ አለች፦ “ትምህርቴን ልጨርስ ትንሽ ሲቀረኝ የአቅኚነት አገልግሎት ትምህርት ቤት በመካፈል ላይ ያሉ ወንድሞችንና እህቶችን እየሄድኩ ጠየቅኋቸው። በዚህም አጋጣሚ ሁለት አረጋውያን እህቶችን አገኘሁ። ‘እነዚህ ሁለት እህቶች አቅኚ መሆን ከቻሉ እኔ መሆን የማልችልበት ምን ምክንያት አለ?’ በማለት ራሴን ጠየቅሁት።”

“ስለዚህ ትምህርቴን ከጨረስኩ በኋላ አቅኚ ሆንኩ። ከሦስት ወራት በኋላ በመተት ታምን የነበረችውን የ26 ዓመቷን ጆዜፊንን አገኘኋት። ‘እናንተ የይሖዋ ምሥክሮች መጥፎ ሰዎች ናችሁ። ገናን አታከብሩም ወይም ክታብ አታስሩም’ አለችኝ። አብረን መጽሐፍ ቅዱስን እንድናጠና ፈቃደኛ ከሆንሽ እነዚህን ነገሮች የማናደርገው ለምን እንደሆነ ማወቅ ትችያለሽ ብዬ መለስኩላት። ተመልሼ እንድመጣ ጋበዘችኝ። ብዙም ሳይቆይ በስብሰባዎች ላይ መገኘት ጀመረች። በሕይወቷም ላይ ብዙ ለውጦችን አደረገች። በታኅሣሥ ወር 1990 ተጠመቀች። ጆዜፊን ከነሐሴ 1991 ጀምሮ አቅኚ ሆና ታገለግላለች። ባለፈው ዓመት የአቅኚነት አገልግሎት ትምህርት ቤት ስትካፈል አብረዋት ኮርሱን ይካፈሉ ለነበሩት ጓደኞቿ መንፈሳዊ እናቴ ናት እያለች አስተዋውቃኛለች!”

የቪድዮ ካሴቱና የመንግሥት አዳራሹ

ማኅበሩ ካስቀረጻቸው የቪድዮ ካሴቶች መካከል አንዱ አንድ አነስተኛ ጉባኤ ለመንግሥት አዳራሽ መሥሪያ የሚሆን ቦታ እንዲያገኝ አስተዋጽኦ አድርጓል። መሬት ለመግዛት አራት ወንድሞች የአካባቢው ባሕላዊ ገዥ የሆነውን ኦኖጂ ቀርበው አነጋገሩት። 20,000 ናያራ (1,025 የአሜሪካ ዶላር) የሚከፈልበት መሬት እንዲወስዱ ነገራቸው። ፕሮጀክቱን በገንዘብ ለመደጎም የሚችሉት አስፋፊዎች 17 ብቻ ስለነበሩ ጉባኤው ያን ያህል ገንዘብ የመክፈል አቅም አልነበረውም። ኦኖጂው ሌላ ቦታ እንደሚፈልግላቸው ነገራቸው።

የተወሰኑ ወራት ካለፉ በኋላ ከጉባኤው ሽማግሌዎች አንዱ ኦኖጂውን ለመጠየቅ ወደ መኖሪያ ቤቱ ሄደ። ኦኖጂው የሥርዓተ ንግሥናው አከባበር የተቀረጸበትን የቪድዮ ካሴት እየተመለከተ ነበር። ሽማግሌው ወንድም “እርስዎ እንዲያዩት የምፈልገው አንድ የቪድዮ ካሴት አለኝ። ርዕሱ የይሖዋ ምሥክሮች —ከስሙ በስተጀርባ ያለው ድርጅት የሚል ነው” አለው።

ከጊዜ በኋላ ሽማግሌው ተመልሶ መጣና ኦኖጂው ስለ ቪድዮ ካሴቱ ምን እንደተሰማው ጠየቀው። ኦኖጂው “ፊልሙን አምስት ጊዜ ተመልክቼዋለሁ” አለው። ሽማግሌው ኦኖጂው በቪድዮ ካሴቱ ላይ ያያቸውን የመንግሥት አዳራሾች አስታወሰውና የእነርሱ ጉባኤም ተመሳሳይ የሆነ የመንግሥት አዳራሽ መሥራት እንደሚፈልግ ገለጸለት። ከዚያም ቀደም ሲል ገዝተውት ከነበረው አነስተኛ መሬት ጋር የሚዋሰን ቦታ መግዛት ይችሉ እንደሆነ ጠየቀው። ኦኖጂው “ትናንትና ማታ የቪድዮ ካሴቱን ከተመለከትኩ በኋላ እኔም ልክ እንደዚሁ አስቤ ነበር” ሲል መለሰለት። ከዚያም የጉባኤው ንብረት ከሆነው መሬት ቀጥሎ ያለ 6 ሜትር ስፋት ያለው መሬት ለካ። “ይህን ቦታ መውሰድ ትችላላችሁ፤ የቦታውን ርዝመት በተመለከተም የፈለጋችሁትን ያህል መውሰድ ትችላላችሁ። ሰነዶቹን አዘጋጁና እፈርምባቸዋለሁ” አለው።

[የግርጌ ማስታወሻ]

a ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የ1994ቱን የይሖዋ ምሥክሮች የቀን መቁጠሪያ ተመ ልከት።

[በገጽ 9 ላይ የሚገኝ ሣጥን]

የ1993 የአገልግሎት ዓመት

የአገሪቱ ሪፖርት መግለጫ

የምሥክሮቹ ከፍተኛ ቁጥር፦174,582

ከሕዝቡ ብዛት ጋር ሲነፃፀር፦1 ምሥክር ለ507 ሰዎች

የመታሰቢያው በዓል ተሰብሳቢዎች፦473,245

የአቅኚዎች ብዛት በአማካይ፦19,777

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች በአማካይ፦242,028

የተጠማቂዎች ብዛት፦8,888

የጉባኤዎች ብዛት፦3,289

ቅርንጫፍ ቢሮው የሚገኝበት ቦታ፦ ቤኒን ሲቲ፣ ኤዶ ስቴት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ