የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w94 9/15 ገጽ 25-26
  • አስተማማኝ የድፍረት ምንጭ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አስተማማኝ የድፍረት ምንጭ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ለክርስቲያኖች የሚሆን ትምህርት
  • ደፋሮች ሁኑ!
    መጠበቂያ ግንብ—1993
  • ድፍረት ስጠኝ
    ለይሖዋ ‘በደስታ ዘምሩ’
  • “ደፋርና ብርቱ ሁን”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • “ደፋር . . . ሁን፤ ሥራህንም ጀምር”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2017
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
w94 9/15 ገጽ 25-26

አስተማማኝ የድፍረት ምንጭ

“አንድ ድምፅ በድንገት እርምጃችንን አቋርጠን እንድቆም አደረገን። ከዚያም ከበስተግራችን ከጫካው ውስጥ ሁለት አሞራዎች ክንፋቸውን ዘርግተው ወደ እኛ ሲሮጡ አየን። ከፊት ለፊታችን በአንድ ትንሽ ጎድጓዳ ቦታ ላይ ሁለት እንቁላሎች ቁጭ ብለዋል። አሞራዎቹ ሳናይ ጎጆአቸውን እንዳንረግጥባቸው መከልከላቸው ነበር። ቡናማ ጠቃጠቆ ያላቸውን ውብ እንቁላሎች ጠጋ ብለን ፎቶግራፍ ለማንሣት በተደጋጋሚ ስንሞክር ወደ እንቁላላቸው እንዳንቀርብ ያስፈራሩን ነበር። ‘እንዴት ደፋሮች ናቸው’ ብለን አሰብን።”

ይህ ሁኔታ አራት ሰዎች ዲኮፕ ወደሚባሉት ዥንጉርጉር አሞራዎች ጎጆ ለመቅረብ ሲሞክሩ ያጋጠማቸው ነው። በጣም ትንሿ አሞራ ብላክስሚዝ ፕሎቨር የምትባለው ነች። ሲንክሌር እና ሜንዲልሰን የተባሉ ስለ አእዋፍ የሚያጠኑ ሰዎች ኤቭሪዋንስ ጋይድ ቱ ሳውዝ አፍሪካን በርድስ በተባለው መጽሐፋቸው ላይ እንደሚከተለው ሲሉ ገልጸዋል፦ “ጥንድ የሆኑት አሞራዎች ጎጆአቸውንና ጫጩቶቻቸውን ከጥቃት ለመከላከል ባላቸው ኃይል ሁሉ ይጠቀማሉ። ማንኛውም ነገር ወደዚያ ለመቅረብ ቢሞክር በጣም ይቆጣሉ። ደፍሮ ለመጠጋት የሚሞክረው ነገር ግዙፍ ቢሆን እንኳ ምንም አይፈሩም፤ ሰዎችን እንኳን ሳይቀር ለማስፈራራትና ለማባረር በኃይል እየጮኹ ወደ ሰማይ ከበረሩ በኋላ ከሰማይ ተወርውረው ይመጣሉ።”

አንዳንድ ትላልቅ ዝሆኖች በድንገት ብላክስሚዝ ፕሎቨር የተባለው አሞራ ባለበት ጎጆ አቅጣጫ ሲሄዱ አሞራዎቹ በጣም እንደሚቆጡ አንዳንድ ሰዎች ተመልክተዋል። ዝሆኖቹም አብዛኛውን ጊዜ በሌላ አቅጣጫ ዞረው ይሄዳሉ።

አሞራዎች ይህን ዓይነቱን ድፍረት ያገኙት ከየት ነው? ይህን ድፍረት ያገኙት ከፈጣሪያቸው ነው። ይሖዋ አምላክ ለእነዚህ አነስተኛ ፍጥረታት ትልልቅ የሆኑ እንሰሳት ጎጆአቸውን እንዳያፈርሱባቸው ወይም በጫጩቶቻቸው ላይ ጉዳት እንዳያደርሱባቸው የመከላከል የተፈጠሮ ችሎታ ሰጥቷቸዋል።

ለክርስቲያኖች የሚሆን ትምህርት

ምንም እንኳ ክርስቲያኖች እንዲያው በተፈጥሮ ከሚገኝ ድፍረት የበለጠ ድፍረት የሚያስፈልጋቸው ቢሆንም ከዚህ አንድ ትምህርት ማግኘት ይችላሉ። ክርስቲያኖች የአምላክን ትዕዛዞች ያለ ምንም ፍርሃት የተከተለውን ጌታቸውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲመስሉት ጥሪ ቀርቦላቸዋል። (ዕብራውያን 12:1–3) መጽሐፍ ቅዱስ አምላክን ከማገልገል ወደኋላ የሚሉ ፈሪዎችን ያወግዛል። (ዕብራውያን 10:39፤ ራእይ 21:8) ሆኖም ይሖዋ ፍጽምና የሌለን መሆናችንንና አንዳንድ ጊዜ ኃጢአት ልንሠራ ወይም የእሱን ፈቃድ ሙሉ በሙሉ ለመፈጸም የሚያስፈልገውን ድፍረት እንደምናጣ ይገባዋል። (መዝሙር 103:12–14) ፍርሃት አንድ ሰው ትክክል የሆነውን ነገር ከማድረግ ወደኋላ ቢመልሰው ምን ማድረግ ይችላል?

አንድ ክርስቲያን ፈተናዎችን ፊት ለፊት ለመጋፈጥ የሚያስችለውን ድፍረት ለማግኘትና መለኮታዊውን ፈቃድ ማድረጉን ለመቀጠል በጸሎት ወደ አምላክ ዞር ማለት አለበት። መጽሐፍ ቅዱስ ይሖዋ ስለሚሰጠው እርዳታ የሚገልጸውን የሚከተለውን አስተማማኝ ተስፋ ይዟል፦ “ለደካማ ኃይልን ይሰጣል፣ ጉልበት ለሌለውም ብርታትን ይጨምራል። ብላቴኖች ይደክማሉ ይታክቱማል፣ ጎበዛዝቱም ፈጽሞ ይወድቃሉ፤ እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፣ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፣ አይደክሙም።” (ኢሳይያስ 40:29–31) ፍጽምና የሌላቸው ብዙ ሰዎች የእነዚህን ቃላት እውነተኝነት ለመመልከት ችለዋል፤ ‘የደከሙትም ኃይል አግኝተዋል።’ (ዕብራውያን 11:34) ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው እንደሚከተለው ሲል የጻፈው ክርስቲያኑ ሐዋርያ ጳውሎስ ነው፦ “ዳሩ ግን የስብከቱ ሥራ በእኔ እንዲፈጸም አሕዛብም ሁሉ እንዲሰሙት፣ ጌታ በእኔ አጠገብ ቆሞ አበረታኝ።”—2 ጢሞቴዎስ 4:17

ሌላው ቀርቶ የክርስቶስ ተከታዮች ለመሆን ፍላጎት ያላቸው አዲስ ሰዎች እንኳ ይህን ዓይነቱን ብርታት የሚሰጥ እርዳታ ሊያገኙ ይችላሉ። በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ከፍተኛ ግምት ይሰጠው የነበረውና የቤተ ክርስቲያኑ ቄስ ጎረቤት የነበረውን ሄንሪ የተባለውን አንድ የደቡብ አፍሪካ ሰው ሁኔታ ተመልከት። ሄንሪ እውነትን ይፈልግ ነበር። ምንም እንኳን ከቤተ ክርስቲያኑ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ቢኖረውም አንድ ቀን ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር ነፃ የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዲደረግለት የቀረበለትን ግብዣ ተቀበለ። ውሎ አድሮም የይሖዋ ምሥክር ለመሆን ያለውን ምኞት ገለጸ፤ እንዲሁም ወደዚህ ግብ ለመድረስ ምን እርምጃዎችን መውሰድ እንዳለበት ጠየቀ። በመጀመሪያ ከቤተ ክርስቲያኑ መልቀቅ እንዳለበት ተነገረው። (ራእይ 18:4) የቤተ ክርስቲያኑ ቄስ ጎረቤቱ ስለሆኑና በጣም ስለሚቀርቡት ከቤተ ክርስቲያኑ መልቀቁን የሚገልጽ ደብዳቤ ከመጻፍ ይልቅ ጉዳዩን በግንባር ቀርቦ መግለጽ እንደሚያስፈልገው ተሰማው። ይህንንም በድፍረት አደረገ።

ቄሱ በጣም ደነገጡ፤ ከዚያም የሲኖዶሱ ሊቀ መንበርና ሌሎች የቤተ ክርስቲያኑ አባላት ሄንሪን እንዲያነጋግሩት ይዘዋቸው ሄዱ። እነሱም ሄንሪ ቤተ ክርስቲያናቸውን ለቅቆ እንደ እነሱ አባባል የአምላክ መንፈስ ቅዱስ የሌለው ሃይማኖት አባል የሚሆንበት ምክንያት ምን እንደሆነ ለማወቅ ፈለጉ። “በመጀመሪያ ለእነሱ መልስ ለመስጠት በጣም ፈርቼ ነበር፤ ምክንያቱም ሁልጊዜ የበላዮቼ ሆነው በቀላሉ ሐሳባቸውን እንድቀበል ያደርጉኝ ነበር። ይሁን እንጂ ይሖዋ እንዲረዳኝ ጸለይኩ፤ ‘ለመሆኑ በዓለም ዙሪያ ካሉት ሃይማኖቶች ሁሉ ይሖዋ በሚለው የአምላክ ስም የሚጠቀም ብቸኛው ሃይማኖት የቱ ነው? የይሖዋ ምሥክሮች አይደሉምን? አምላክ የእሱን መንፈስ ቅዱስ ሳይሰጣቸው ስሙን እንዲሸከሙ ይፈቅድላቸዋል ብላችሁ ታስባላችሁን?’” የሚል መልስ እንድሰጥ ይሖዋ ረዳኝ። የቤተ ክርስቲያኑ ባለ ሥልጣኖችም ይህ አባባል ሐሰት ነው በማለት ሊያስተባብሉ አልቻሉም። አምላክ ይህን እውቀትና ድፍረት ስለ ሰጠው ሄንሪ በአሁኑ ጊዜ ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር ከቤት ወደ ቤት በሚደረገው አገልግሎት በድፍረት እየተካፈለ ነው።

እውነት ነው፣ እውነተኛ ክርስቲያን መሆን ድፍረት ይጠይቃል። የዚህ ዓለም ፍጻሜ እየቀረበ በመጣ መጠን የእምነት ፈተናዎች ይጨምራሉ። ሰይጣን የአምላክ አገልጋዮች ለይሖዋ ያላቸውን ፍጹም አቋም ጠባቂነት ለማበላሸትና ግሩም የሆነውን የዘላለም ሕይወት ተስፋቸውን ለማጥፋት እየጣረ ነው። (ከራእይ 2:10 ጋር አወዳድር) ቢሆንም በፍጹም ተስፋ መቁረጥ የለብንም። ምንም እንኳ ከፍርሃት የተነሣ ጊዜያዊ መሰናክል ቢያጋጥመንም እንደገና እንድናንሰራራ ይሖዋ ሊረዳን ይችላል። ይሖዋ ፈቃዱን ማድረጋችሁን እንድትቀጥሉ የሚያስችላችሁን ብርታት እንዲሰጣችሁ ያለማቋረጥ ጠይቁት። ደፋር የሆኑ አሞራዎችን የፈጠረው አምላክ አስተማማኝ የድፍረት ምንጭ መሆኑን አትዘንጉ። በእርግጥም እውነተኛ ክርስቲያኖች “በድፍረት፦ ጌታ [ይሖዋ አዓት] ይረዳኛልና አልፈራም ሰው ምን ያደርገኛል?” ማለት ይኖርባቸዋል።—ዕብራውያን 13:6

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ