የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w94 12/15 ገጽ 30
  • ታስታውሳለህን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ታስታውሳለህን?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ከአንጀት የምትራሩ ሁኑ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • ስለ ይሖዋ ታማኝነት እና ይቅር ባይነት ያለንን ግንዛቤ ማሳደግ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • የአምላክ ወዳጅ መሆን የምትችለው እንዴት ነው?
    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?
  • ኢዮብ የይሖዋን ስም ከፍ ከፍ አድርጓል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
w94 12/15 ገጽ 30

ታስታውሳለህን?

በቅርብ ጊዜያት የወጡት የመጠበቂያ ግንብ እትሞች ተግባራዊ ጥቅም የሚሰጡህ ሆነው አግኝተሃቸዋልን? እንግዲያው ቀጥሎ ባሉት ጥያቄዎች አማካኝነት የማስታወስ ችሎታህን ፈትን፦

▫ የይሖዋ ምሥክሮች ሰዎችን ቤታቸው ድረስ በመሄድ ማነጋገራቸውን የማይተዉት ለምንድን ነው?

የይሖዋ ምሥክሮች ትመጣለች ተብሎ ቃል በተገባላት መንግሥት አማካኝነት የአምላክን በረከት ለማግኘት ስለሚፈልጉና ለሰው ሁሉ ባላቸው ፍቅር የተነሣ ሌሎች ሰዎችም የአምላክን በረከት እንዲያገኙ ስለሚፈልጉ ነው። ስለዚህ የኢየሱስን አርዓያ በመከተል ሰዎችን ቤታቸው ድረስ በመሄድ እንዲያነጋግሯቸው ራስ ወዳድነት የሌለበት ፍቅር ግድ ይላቸዋል። (ማቴዎስ 6:9, 10፤ 22:37–39)—8/15፣ ገጽ 8, 9

▫ በዝግመተ ለውጥ ማመን አሜን ብሎ መቀበልን ብቻ የሚጠይቅ ነገር የሆነው ለምንድን ነው?

ሳይንቲስቶች አዳዲስ ሕያዋን ነገሮችን ያስገኛል የሚባለው “ሚውቴሽን (በነባር አካል ላይ የሚከሰት ባሕሪያዊ ለውጥ)” ሲከሰት፣ ሌላው ቀርቶ “ቤኔፊሻል ሚውቴሽን (ጠቃሚ የሚባለው ለውጥ)” እንኳ ሲከናወን አልተመለከቱም። ያም ሆኖ ግን ያላንዳች ጥርጥር የተለያዩ ዝርያዎች ወደ መኖር የመጡት በዚህ መንገድ ነው ይላሉ። ሕይወት የመጣው ሕይወት ከሌለው ነገር ሲሆን አመጣጡም ቅጽበታዊ ነው ቢሉም ይህን በዓይናቸው አላዩም፤ ሆኖም ሕይወት ወደ መኖር የመጣው በዚህ መንገድ ነው በማለት ሽንጣቸውን ገትረው ይከራከራሉ።—9/1፣ ገጽ 5

▫ በሕይወታችን ውስጥ ባሉት ገደቦች የተነሣ የሚመጣ ተስፋ መቁረጥን እንዴት በተሳካ ሁኔታ ለመቋቋም እንች ላለን?

በምንም ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ብንገኝ ማድረግ ስለማንችለው ነገር ከመጨነቅ ይልቅ ማድረግ በምንችለው ነገር ላይ ብናተኩር ሕይወት አርኪ ይሆንልናል፤ በአምላክ አገልግሎትም እንደሰታለን። (መዝሙር 126:5, 6)—9/1፣ ገጽ 28

▫ ይቅር ባይነት ምን ጥቅሞች አሉት?

ሌሎችን ይቅር ማለት ከሰዎች ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዲኖር ያስችላል፤ (ኤፌሶን 4:32)፤ ከሰዎች ጋር ብቻ ሳይሆን በውስጣችንም ሰላምን ያመጣልናል፤ (ሮሜ 14:19፤ ቆላስይስ 3:13–15)፤ ሌሎችን ይቅር ማለታችን ኃጢአታችን ይቅር እንዲባልልን መንገድ ይከፍታል፤ (ማቴዎስ 6:14)፤ በተጨማሪም እኛ ራሳችን ይቅር መባል የሚያስፈልገን መሆናችንን እንድናስታውስ ይረዳናል። (ሮሜ 3:23)—9/15፣ ገጽ 7

▫ የነቢዩ አሞጽ ምሳሌ በስብከት ሥራችን ረገድ የሚረዳን እንዴት ነው?

እኛም እንደ አሞጽ የአምላክን መልእክት ለውጠን ወይም በርዘን አንናገርም። ከዚህ ይልቅ ሰሚዎቻችን ምንም ዓይነት ምላሽ ቢያሳዩ መልእክቱን በታዛዥነት እናውጃለን።—9/15፣ ገጽ 17

▫ የትኞቹን የአምላክን ባሕርያት ልንኮርጃቸው ይገባናል?

ዋና ዋናዎቹ ሁለት ባሕርያት የአደራጅነት ችሎታውና ደስተኛነቱ ናቸው። (1 ቆሮንቶስ 14:33፤ 1 ጢሞቴዎስ 1:11 አዓት) እነዚህ የአምላክ ባሕርያት ሚዛናቸውን የጠበቁ ናቸው፤ አንዱ ሌላውን በመጫን ልቆ አይታይም።—10/1፣ ገጽ 10

▫ ልጆቻቸው ይሖዋን የሚያገለግሉ እንዲሆኑ ለመርዳት ወላጆች ሊወስዷቸው የሚገቡ አንዳንድ ገንቢ እርምጃዎች ምንድን ናቸው?

አንዱ በጣም አስፈላጊ የሆነ ቁልፍ ከልጅነታቸው መጀመር ነው። ብዙውን ጊዜ ገና በለጋነታቸው የሚቀረጹባቸውና የሚማሯቸው ነገሮች በሕይወት ዘመናቸው በሙሉ የማይረሷቸው ይሆናሉ። (ምሳሌ 22:6) ለይሖዋና በሁሉም ስብሰባዎች ላይ ለሚካሄደው አምልኮቱ ታዛዥነትና አክብሮት እንዲኖራቸው ማስተማር አስፈላጊ ነው። በዚህ ረገድ የተሳካላቸው ወላጆች ልጆቻቸው በወረሱት አለፍጽምና ምክንያት ያሏቸውን መጥፎ ዝንባሌዎች ተገንዝበው ልጆቻቸው እነዚህን ነገሮች እንዲያርሙ መርዳትን ተምረዋል። (ምሳሌ 22:15) በመጨረሻም ከትንሽነታቸው ጀምራችሁ ሊደርሱባቸው የሚችሏቸውን ቲኦክራሲያዊ ግቦች በልጆቻችሁ ፊት አስቀምጡ።—10/1፣ ገጽ 27–8

▫ ተግባራዊ ለማድረግ መጣር ያለብን የትኛውን የይሖዋ አምላክን የተለየ ባሕርይ ነው?

ይሖዋ ይቅር ይላል፤ እንዲሁም በደሉን ይረሳዋል። (ኤርምያስ 31:34) ሰብዓዊ ፍጥረታት ይህን ማድረግ በጣም ይቸግራቸዋል። እንዲህ የማድረጉ አስፈላጊነት በማቴዎስ 6:14, 15 ላይ ተመዝግበው በሚገኙት የኢየሱስ ቃላት ጐላ ተደርጐ ተገልጿል።—10/15፣ ገጽ 25–6

▫ ርኅሩኆች እንዳንሆን እንቅፋት የሚሆኑብን ሦስት ነገሮች ምንድን ናቸው?

በኃጢአተኛው ሰብዓዊ ተፈጥሯችን የተነሣ የቅናት ስሜት በቀላሉ በልባችን ውስጥ ሥር ሊሰድ ይችላል። አንድን ሰው የምንቀናበት ከሆነ ከአንጀት በመነጨ ርኅራኄ እንዴት ልንይዘው እንችላለን? እንቅፋት የሚሆንብን ሌላው ነገር ራሳችንን አላግባብ ለዓመፅ ማጋለጣችን ነው። ይህ ሌሎች ሲሠቃዩ የማዘን ስሜት እንዳይኖረን ያደርገናል። በተጨማሪም ራስ ወዳድ የሆነ ሰው ርኅራኄ እንደማይኖረው የታወቀ ነው። (1 ዮሐንስ 3:17)—11/1፣ ገጽ 20

▫ ስለ ኢዮብ ከሚተርከው ቅዱስ ጽሑፋዊ ዘገባ ምን ነገሮችን ልንማር እንችላለን?

ስለ ኢዮብ የሚተርከው ዘገባ ሰይጣን የሚጠቀምባቸውን ዘዴዎች ይበልጥ እንድናውቅ ያደርገናል፤ እንዲሁም የይሖዋ ጽንፈ ዓለማዊ ሉዓላዊነት ሰው ለአምላክ የሚያሳየውን የጸና አቋም ሳያጎድፍ ከመቀጠሉ ጋር እንዴት እንደሚዛመድ መገንዘብ እንድንችል ይረዳናል። አምላክን የሚያፈቅሩ ሁሉ ልክ እንደ ኢዮብ ፈተና ይደርስባቸዋል። እኛም እንደ ኢዮብ መጽናት እንችላለን። ሰይጣን ሐሰተኛ መሆኑን ልናረጋግጥና የአምላክ መንግሥት የምታመጣቸውን በረከቶች አግኝተን ልንደሰት እንችላለን።—11/15፣ ገጽ 19, 20

▫ የሽማግሌዎች አካል ሊቀ መንበር ለእያንዳንዱ ሽማግሌ ተገቢውን ዕውቅና ሊያሳይ የሚችለው እንዴት ነው?

ሌሎቹ ሽማግሌዎች እያንዳንዱን ነጥብ በጥንቃቄና በጸሎት ያስቡበት ዘንድ በቂ ጊዜ እንዲኖራቸው የሚቻል በሚሆንበት ጊዜ ሁሉ ሊቀ መንበሩ የስብሰባቸውን አጀንዳ አስቀድሞ ሊሰጣቸው ይገባል። በሽማግሌዎች ስብሰባ ላይ የሽማግሌዎቹን ሐሳብ በፈለገው መንገድ ለመቅረጽ አይሞክርም፤ ከዚህ ይልቅ ውይይት በሚደረግባቸው ጉዳዮች ላይ ‘የመናገር ነፃነታቸውን’ እንዲጠቀሙበት ያበረታታቸዋል። (1 ጢሞቴዎስ 3:13 አዓት)—12/1፣ ገጽ 30

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ