የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w96 8/15 ገጽ 21
  • ታስታውሳለህን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ታስታውሳለህን?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የአንባብያን ጥያቄዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
  • ‘እርስ በርስ በነፃ ይቅር መባባላችሁን ቀጥሉ’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
  • አምላክ ይቅር ይለኝ ይሆን?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ‘ለአሕዛብ ሁሉ የሚሆን የጸሎት ቤት’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
w96 8/15 ገጽ 21

ታስታውሳለህን?

በቅርቡ የወጡትን የመጠበቂያ ግንብ እትሞች በማንበብህ ተደስተሃልን? ከሆነ እስቲ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

◻ “ኃጢአታቸውን ይቅር ያላችኋቸው ሁሉ ይቀርላቸዋል” የሚሉት የኢየሱስ ቃላት ክርስቲያኖች ኃጢአትን ይቅር ማለት እንደሚችሉ ያሳያሉን? (ዮሐንስ 20:23)

ክርስቲያኖች በጠቅላላ፣ ሌላው ቀርቶ የተሾሙ የጉባኤ ሽማግሌዎች እንኳ ቢሆኑ ኃጢአትን ይቅር ለማለት መለኮታዊ ሥልጣን ተሰጥቷቸዋል የሚል መደምደሚያ ላይ ለመድረስ የሚያስችል ቅዱስ ጽሑፋዊ ማስረጃ የለም። ኢየሱስ የተናገራቸው ቃላት ሐዋርያት በአምላክ መንፈስ አማካኝነት ኃጢአትን ይቅር ለማለት ወይም ለመያዝ ልዩ መብት ተሰጥቷቸው እንደነበር ለማሳየት የገቡ ይመስላል። (ሥራ 5:1-11፤ 2 ቆሮንቶስ 12:12ን ተመልከት።)—4/15፣ ገጽ 28

◻ ለመጀመሪያ ጊዜ በ1864 የታተመው ጄ ጄ ስቲዋርት ፐሮን ያዘጋጀው የመዝሙር መጽሐፍ ትርጉም ምን ለየት ያለ ባሕርይ አለው?

ፐሮን በትርጉሙ ውስጥ ‘በፈሊጣዊ አነጋገሮቹም ሆነ በሐረጎቹ የሰዋስው አሰካክ የዕብራይስጡን የአጻጻፍ ስልት በጥብቅ ለመከተል’ ሞክሯል። እንዲህ በሚያደርግበት ጊዜ መለኮታዊውን ስም ወደ ቦታው ለመመለስ “ጅሆቫ” በሚለው አጠራር መጠቀምን መርጧል።—4/15፣ ገጽ 31

◻ ኢየሱስ ተከታዮቹ ከዓለም ባለ ሥልጣኖች ጋር ሊኖራቸው የሚገባውን ግንኙነት በተመለከተ ምን መመሪያ ሰጥቷል?

ኢየሱስ “እንኪያስ የቄሣርን ለቄሣር የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር አስረክቡ” ብሏል። (ማቴዎስ 22:21) ከዚህም በተጨማሪ ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ማንም ሰው [“አንድ በሥልጣን ያለ ሰው፣” አዓት] አንድ ምዕራፍ ትሄድ ዘንድ ቢያስገድድህ ሁለተኛውን ከእርሱ ጋር ሂድ።” (ማቴዎስ 5:41) እዚህ ላይ ኢየሱስ ከሰው ጋር ባለን ግንኙነትም ሆነ መንግሥት እንድናሟላቸው በሚፈልጋቸው ነገሮች ረገድ ከአምላክ ሕግ ጋር ለሚስማሙና አግባብነት ላላቸው ነገሮች ራስን በፈቃደኛነት የማስገዛትን አስፈላጊነት የሚገልጸውን መሠረታዊ ሥርዓት አብራርቷል። (ሉቃስ 6:27-31፤ ዮሐንስ 17:14, 15)—5/1፣ ገጽ 12

◻ ‘በእውነት መመላለስ’ ማለት ምን ማለት ነው? (መዝሙር 86:11)

ይህ አምላክ ከሚፈልግብን ብቃት ጋር ተስማምቶ መሄድን እንዲሁም የታመኑ ሆኖ መገኘትንና ከልብ ማገልገልን ይጨምራል። (መዝሙር 25:4, 5፤ ዮሐንስ 4:23, 24)—5/15፣ ገጽ 18

◻ ይሖዋ ዮናስን ወደ ነነዌ በመላኩ ምን ነገር ተከናውኗል?

የዮናስ የስብከት ሥራ የንስሐ መንፈስ ባላቸው የነነዌ ሰዎችና ምንም ዓይነት እምነትና ትሕትና በሌላቸው አንገተ ደንዳናዎቹ እስራኤላውያን መካከል ያለውን ልዩነት ለማሳየት አገልግሏል። (ከዘዳግም 9:6, 13 እና ዮናስ 3:4-10 ጋር አወዳድር።)—5/15፣ ገጽ 28

◻ በዘፍጥረት 3:15 ላይ የተጠቀሰው እባብ ማን ነው? “ሴቲቱስ”?

እዚህ ላይ የተጠቀሰው ዝቅተኛ ፍጥረት የሆነው ተራ እባብ ሳይሆን በእባቡ የተገለገለው ሰይጣን ዲያብሎስ ነው። (ራእይ 12:9) “ሴቲቱ” ደግሞ በምድር ላይ ያሉት በመንፈስ የተቀቡ የይሖዋ አገልጋዮች እናት የሆነችው የይሖዋ ሰማያዊ ድርጅት እንጂ ሔዋን አይደለችም። (ገላትያ 4:26)—6/1፣ ገጽ 9

◻ አንድ ሰው ከታላቂቱ ባቢሎን ሊወጣና ደህንነት ሊያገኝ የሚችለው እንዴት ነው? (ራእይ 18:4)

ራሱን ሙሉ በሙሉ ከሐሰት ሃይማኖታዊ ድርጅቶች እንዲሁም ከሚያራምዱት ባሕልና አስተሳሰብ መለየትና ወደ ይሖዋ ቲኦክራሲያዊ ድርጅት ሸሽቶ ማምለጥ ይኖርበታል። (ኤፌሶን 5:7-11)—6/1፣ ገጽ 18

◻ ንስር በቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ በተደጋጋሚ የተጠቀሰው ለምንድን ነው?

የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች ስለ ጥበብ፣ መለኮታዊ ጥበቃ እና ፍጥነት ለማስረዳት የንስርን ባሕርያት ጠቅሰዋል።—6/15፣ ገጽ 8

◻ በዛሬው ጊዜ የሚገኙ ምድራዊ ተስፋ ያላቸው የአምላክ አገልጋዮች በመንፈስ ከተቀቡት ክርስቲያኖች እኩል የአምላክ መንፈስ አላቸውን?

በመሠረቱ መልሱ አዎን የሚል ነው። ሁለቱም ቡድኖች የአምላክን መንፈስ እኩል ያገኛሉ፣ እኩል እውቀትና ማስተዋል ይቀርብላቸዋል።—6/15፣ ገጽ 31

◻ በኢየሩሳሌም በሚገኘው ቤተ መቅደስ ውስጥ አስራኤላውያን ካህናት ያከናውኑት የነበረውን ቅዱስ አገልግሎት መመርመራችን ዛሬ ለእኛ ምን ጥቅም አለው?

እንዲህ ማድረጋችን ዛሬ ያሉ ኃጢአተኛ ሰዎች ከአምላክ ጋር ስለሚታረቁበት የምሕረት ዝግጅት ይበልጥ በተሟላ መልኩ ለመረዳት ያስችለናል። (ዕብራውያን 10:1-7)—7/1፣ ገጽ 8

◻ በኢየሩሳሌም የተገነባው ሁለተኛው ቤተ መቅደስ በሰሎሞን ዘመን ከነበረው የበለጠ ክብር የተጎናጸፈው እንዴት ነው?

ሁለተኛው ቤተ መቅደስ ከሰሎሞን ቤተ መቅደስ ዕድሜ በ164 ዓመታት ይበልጥ ነበር። ከብዙ ተጨማሪ አገሮች የመጡ ብዙ አምላኪዎች ወደ አደባባዮቹ ጎርፈዋል። ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ የአምላክ ልጅ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ቤተ መቅደስ አደባባዮች ቆሞ በማስተማሩ ይህ ሁለተኛ ቤተ መቅደስ የላቀ ክብር አግኝቷል።—7/1፣ ገጽ 12, 13

◻ አምላክ መንፈሳዊ ቤተ መቅደሱን ወደ ሕልውና ያመጣው መቼ ነው?

ይህ የሆነው አምላክ ኢየሱስ ሲጠመቅ ያቀረበውን ጸሎት እንደተቀበለው ባሳየበት ዓመት በ29 እዘአ ነው። (ማቴዎስ 3:16, 17) አምላክ የኢየሱስ አካል መሥዋዕት ሆኖ እንዲቀርብ መስማማቱ በመንፈሳዊ አባባል በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ውስጥ ከነበረው የሚበልጠው መሠዊያ ሥራ እንደጀመረ ያሳያል።—7/1፣ ገጽ 14, 15

◻ ይቅር ባዮች መሆን ያለብን ለምንድን ነው?

ክርስቲያናዊ አንድነታችን እንዲጠበቅ ከተፈለገ ይቅርታ የጠየቀንን አንድ በደለኛ ይቅር ማለት በጣም አስፈላጊ ነው። ጥላቻና ቂም መያዝ የአእምሮ ሰላም ያሳጣናል። ይቅር ባዮች ካልሆንን ይሖዋ እኛ የሠራናቸውን ኃጢአቶች ይቅር ማለቱን ሊያቆም ይችላል። (ማቴዎስ 6:14, 15)—7/15፣ ገጽ 18

◻ እስራኤላውያን ቅዱስ መሆን የሚችሉት እንዴት ነበር?

ይህን ማድረግ የሚችሉት ቅዱስ ከሆነው አምላክ ከይሖዋ ጋር ባላቸው የቅርብ ዝምድናና ለእርሱ በሚያቀርቡት ንጹሕ አምልኮ አማካኝነት ብቻ ነበር። እርሱን በቅድስና እንዲሁም በአካላዊና መንፈሳዊ ንጽሕና ለማምለክ ስለ ‘ቅዱሱ’ ትክክለኛ እውቀት ማግኘት ያስፈልጋቸው ነበር። (ምሳሌ 2:1-6፤ 9:10)—8/1፣ ገጽ 11

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ