የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w98 4/1 ገጽ 9
  • “ጠንካራና አሳማኝ”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “ጠንካራና አሳማኝ”
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ከአምላክ የተላከ ምሥራች!
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2013
  • በብሮሹሮች ተጠቅማችሁ የመንግሥቱን ምሥራች አውጁ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
  • ስታገለግሉ በተለያዩ ብሮሹሮች ተጠቀሙ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
  • ለሌሎች ልባዊ ኣሳቢነት በማሳየት ይሖዋን ምሰል
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
w98 4/1 ገጽ 9

“ጠንካራና አሳማኝ”

በፈረንሳይ የሚገኝ አንድ የይሖዋ ምሥክር “የቀረቡት የመከራከሪያ ነጥቦች እጅግ ጠንካራና አሳማኝ በመሆናቸው ከነገ ጀምሮ በስብከት ሥራዬ እጠቀምበታለሁ” ሲል ጽፏል። በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኝ ሌላ የይሖዋ ምሥክር ደግሞ እንዲህ ሲል ጽፏል:- “ያነበብኩት ወዲያው እንደደረሰኝ ነበር፤ ብዙ ግድ የለሽ የሆኑና በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እምነት የሌላቸው ሰዎች ስለሚያጋጥሙን በአገልግሎት ለመጠቀም ጊዜ አላጠፋሁም።” ይህን አስተያየት የሰጡት ምንን በሚመለከት ነው? በ1997/98 በተደረጉት “በአምላክ ቃል ማመን” የተባሉ የአውራጃ ስብሰባዎች ላይ የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ያወጣውን ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ የተባለ ባለ 32 ገጽ ብሮሹር በሚመለከት ነው።

ይህ ጽሑፍ የተዘጋጀው የተወሰኑ የኅብረተሰቡን ክፍሎች ማለትም የተማሩ ሆነው ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ግን በቂ እውቀት የሌላቸውን ሰዎች ለመርዳት ታስቦ ነው። እንዲህ ያሉት አብዛኛዎቹ ሰዎች ቢያንስ ቢያንስ መጽሐፍ ቅዱስን አንብበው የሚያውቁ ባይሆኑም እንኳ የራሳቸውን አስተያየቶች ይሰነዝራሉ። የዚህ ብሮሹር ዓላማ አንባቢዎቹ መጽሐፍ ቅዱስ ሊመረመር የሚገባው መጽሐፍ መሆኑን እንዲገነዘቡ ማስቻል ነው። ብሮሹሩ መጽሐፍ ቅዱስ በአምላክ መንፈስ አነሳሽነት የተጻፈ ስለመሆኑ አንባቢውን ሊያሳምን አይሞክርም። ከዚህ ይልቅ ሐቆቹ ስለራሳቸው እንዲናገሩ ያደርጋል። የብሮሹሩ ቃላት የተወሳሰቡ ሳይሆኑ ግልጽና ቀጥተኛ ናቸው።

ከላይ የተሰጡት አስተያየቶች እንደሚያሳዩት በስብሰባዎቹ ላይ ተገኝተው የነበሩት ሁሉ ይህን ብሮሹር በአገልግሎት ለመጠቀም ጓጉተው ነበር። ለምሳሌ ያህል ፈረንሳይ ውስጥ የዓለም ወጣቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ ከዓለም ዙሪያ የመጡ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ጎብኚዎች በፓሪስ በተሰበሰቡባቸው ቀናት ማለትም ነሐሴ 23 እና 24 ልዩ የምሥክርነት ዘመቻ ለማድረግ ዝግጅት ተደርጎ ነበር። ሁለት ሺህ አምስት መቶ የሚያክሉ የይሖዋ ምሥክሮች (አብዛኞቹ ዕድሜያቸው ከ16 እስከ 30 የሚሆን ነው) በእንግሊዝኛ፣ በፈረንሳይኛ፣ በጀርመንኛ፣ በጣልያንኛ፣ በፖላንድ ቋንቋ፣ እንዲሁም በስፓንኛ የተዘጋጁትን የዚህን ብሮሹር 18,000 ቅጂዎች አበርክተዋል።

ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ የተባለውን ይህን ብሮሹር በአገልግሎታችን እንጠቀምበት። ይህ ጽሑፍ ምክንያታዊ የሆኑ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን ራሳቸው ሊመረምሩት እንደሚገባ በማሳመን ረገድ ጠቃሚ መሣሪያ ሆኖ እንዲያገለግል ምኞታችን ነው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ