የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w98 12/1 ገጽ 3-4
  • ብዙዎች እምነት እንዳላቸው ይናገራሉ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ብዙዎች እምነት እንዳላቸው ይናገራሉ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የኢየሱስ ስም በዛሬው ጊዜ
  • ወደ እውነተኛ እምነት የሚመራ ስም
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
  • የይሖዋ ስም—ኢየሱስ የሰጠው ቦታ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2025
  • የአምላክን ስም ማወቅ የሚኖርብን ለምንድን ነው?
    ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም
  • የይሖዋን ታላቅ ስም አክብሩ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
w98 12/1 ገጽ 3-4

ብዙዎች እምነት እንዳላቸው ይናገራሉ

“ኢየሱስ ታላቅ ነው! እጅግ የሚደነቅ ነው!” ይህን የተናገረችው በብራዚል የምትኖር አንዲት ሃይማኖተኛ ሴት ናት። እርግጥ ነው የኢየሱስ ስም ኃይል እንዳለው አይካድም። በታሪክ ዘመናት በሙሉ ሰዎች ስለ ኢየሱስ መከራ ለመቀበል አልፎ ተርፎም ለመሞት ፈቃደኛ ሆነዋል።

ሐዋርያው ጴጥሮስና ሐዋርያው ዮሐንስ ኢየሩሳሌም ውስጥ ‘በኢየሱስ ስም’ ሰብከዋል። እንዲህ በማድረጋቸውም ተይዘው ተገርፈዋል። ሆኖም “ስለ ስሙ ይናቁ ዘንድ የተገባቸው ሆነው ስለ ተቈጠሩ ከሸንጎው ፊት ደስ እያላቸው ወጡ።”​—⁠ሥራ 5:​28, 41

የኢየሱስን ስም ከፍ አድርጎ የተመለከተው ሌላው የመጀመሪያው መቶ ዘመን ክርስቲያን አንቲጳስ ነበር። ኢየሱስ በመጨረሻው የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ በራእይ ላይ ስለ አንቲጳስ ሲናገር “ሰይጣንም በሚኖርበት፣ በእናንተ ዘንድ የተገደለው የታመነው ምስክሬ” ብሏል። (ራእይ 2:​13) በጴርጋሞን እንደነበሩ ሌሎች ክርስቲያኖች ሁሉ አንቲጳስም በክርስቶስ ላይ ያለውን እምነት ለመካድ ፈቃደኛ አልሆነም። አንቲጳስ ሕይወቱን መሥዋዕት ማድረግ ቢጠይቅበትም እንኳን የኢየሱስን ስም አጥብቆ ይዟል!

ከግማሽ ምዕተ ዓመት ገደማ በኋላ ማለትም በ155 እዘአ ክርስቲያን እንደሆነ የሚነገርለት ፖሊካርፕ ክርስቶስን እንዲሰድብ ሲታዘዝ ተመሳሳይ የሆነ ፈተና ተደቅኖበት ነበር። የሰጠው መልስ “ሰማንያ ስድስት ዓመታት ሙሉ አገልግዬዋለሁ፤ በዚህ ሁሉ ዓመት አንዳች ነገር አልበደለኝም። ያዳነኝን ንጉሤን እንዴት እሰድበዋለሁ?” የሚል ነበር። ፖሊካርፕ ክርስቶስን ለመካድ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ምክንያት በእንጨት ላይ ከተሰቀለ በኋላ በእሳት ተቃጥሏል።

ሐዋርያት፣ አንቲጳስና ሌሎችም በክርስቶስ ላይ ያላቸውን ጽኑ እምነት እስከ ሞት ድረስ ለማረጋገጥ ፈቃደኞች ነበሩ! በዛሬው ጊዜ ስለሚገኙ ሰዎችስ ምን ለማለት ይቻላል?

የኢየሱስ ስም በዛሬው ጊዜ

የኢየሱስ ስም ጠንካራ ግፊት ማሳደሩን ቀጥሏል። በላቲን አሜሪካ ውስጥ በኢየሱስ እንደሚያምኑ የሚናገሩ አብያተ ክርስቲያናት ቁጥር በቅርብ አሥርተ ዓመታት ውስጥ በከፍተኛ ፍጥነት ጨምሯል። በትንንሽ መንደሮች ውስጥ እንኳ ሳይቀር የጰንጠቆስጤ ቤተ ክርስቲያን ይገኛል። የዚያኑ ያህል ደግሞ እነዚህ አብያተ ክርስቲያናት የሚያሳድሩት ፖለቲካዊ ተጽእኖ እየጨመረ ሄዷል። ለምሳሌ ያህል በብራዚል በምክር ቤቱና በሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ ውስጥ 31 መቀመጫዎችን የያዙት የእነዚህ አብያተ ክርስቲያናት አባላት ናቸው።

በተጨማሪም ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በኢየሱስ ላይ ያተኮረ አንድ አዲስ ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴ ተጀምሯል። የሃይማኖቱ ተከታዮች ራሳቸውን ቃል ኪዳን ጠባቂዎች (Promise Keepers) ብለው ሰይመዋል። በ1997 ታይም መጽሔት ባወጣው ዘገባ መሠረት በ1991 በስብሰባዎቻቸው ላይ የሚገኙት ሰዎች ቁጥር ከ4,200 ተነስቶ በ1996 ወደ 1.1 ሚልዮን አድጓል። ከመዝሙሮቻቸው አንዱ “በዘላለማዊው አዳኜ በኢየሱስ ድል አደርጋለሁ” ይላል።

ይሁን እንጂ በኢየሱስ ስም የተመሠረቱት አመለካከቶች ሁሉ ትክክል ናቸው ማለት አይደለም። የኢየሱስን ስም እንደ አርማ በማንገብ ብዙ ጊዜ ጦርነቶች ይካሄዳሉ። አይሁዶች ተጨፍጭፈዋል፣ አረማውያን ታርደዋል፣ ክርስትናን ያልተቀበሉ ተደብድበዋል፣ አካላቸው ተቆርጧል እንዲሁም በእንጨት ላይ ተሰቅለው ተቃጥለዋል። ይህ ሁሉ የተፈጸመው በኢየሱስ ስም ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ወንጌላዊነት የትርፍ ማግኛ መንገድ እየሆነ መጥቷል። ይህ ሁሉ የኢየሱስን ስምና ስሙ የሚወክለውን ነገር የሚያጎድፍ የተሳሳተ ድርጊት ነው!

ከዚህም በላይ ይህ ነገር ከጉዳዩ ጋር ዝምድና ያላቸውን አንዳንድ ጥያቄዎች ያስነሳል:- በኢየሱስ ስም ማመን ምን ነገር ያጠቃልላል? የይሖዋ ምሥክሮች በዚህ ጉዳይ ላይ ያላቸው አመለካከት ምንድን ነው? የሚከተለው ርዕስ ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ