ልዩ የመስክ አገልግሎት ወር
ታኅሣሥ ልዩ የመስክ አገልግሎት ወር ሊሆንልህ ይችላልን? በየቀኑ በምታደርጋቸው ነገሮች ላይ አንዳንድ ማስተካከያዎች ማድረግ ያስፈልግህ ይሆናል፤ ሆኖም የምታገኘውን አርኪ ውጤት ስትመለከት ይህ ዓይነቱ ማስተካከያ ቢደረግለት የሚቆጭ ነውን?
የተጠመቁ አንዳንድ ወጣት አስፋፊዎች ተጨማሪ የትምህርት ቤት የእረፍት ቀናት ስለሚኖሯቸው በዚያ ወር ረዳት አቅኚዎች ለመሆን ለመመዝገብ ይፈልጉ ይሆናል። አንዳንድ ሽማግሌዎች፣ ዲያቆናትና ሌሎች አስፋፊዎች በመስክ አብረዋቸው ቢሠሩ እነዚህ ወጣት አቅኚዎች እንዴት ይበረታቱ ነበር! የግል ሁኔታዎችህ በዚያ ወር አቅኚ ሆነህ እንዳታገለግል ቢያግዱህም አቅኚ ከሚሆኑት ጋር በመስክ ጥቂት ተጨማሪ ሰዓታት ማገልገል አትችልም? እንዲህ ማድረግህ ሁለታችሁንም የሚያበረታታ ነው።
ሁሉም አስፋፊዎች ተጨማሪ ጥረት ቢያደርጉ ሽማግሌዎች በበዓል ቀናት የቡድን ምስክርነት ለመስጠት የሚያስችል ዝግጅት ሊያደርጉ ይችሉ ይሆናል። እንዲህ ማድረጋቸው አቅኚ ለመሆን የቻሉት ሁልጊዜ አብረዋቸው በመስክ አገልግሎት የሚሠሩ ሰዎች እንዲያገኙ ያስችላቸዋል።
ታኅሣሥ ለጉባኤያችሁ ልዩ የመስክ አገልግሎት ወር እንዲሆንላችሁ በግለሰብም ይሁን በቤተሰብ እንዲሁም በጉባኤ ደረጃ ዕቅድ ለማውጣት የምትችሉበት ጊዜው አሁን ነው።