የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 4/93 ገጽ 7
  • የጥያቄ ሣጥን

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የጥያቄ ሣጥን
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • 1,000 ረዳት አቅኚዎች ይፈለጋሉ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
  • ዘንድሮም ጥሪውን ትቀበላላችሁን?—ለረዳት አቅኚነት በድጋሚ የቀረበ ጥሪ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
  • ለአዲሱ የአገልግሎት ዓመት ልታወጣው የምትችለው ጠቃሚ ግብ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2007
  • የይሖዋን ግርማ በሰፊው አውጁ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2007
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
km 4/93 ገጽ 7

የጥያቄ ሣጥን

◼ ረዳት አቅኚ ሆኖ ማገልገል እንዴት ሊታይ ይገባል?

ረዳት አቅኚ ሆኖ ማገልገል እንደ መብትም እንደ ከባድ ኃላፊነትም ተደርጎ ሊታይ ይገባል። በየወሩ በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ አስፋፊዎች ረዳት አቅኚዎች ሆነው ለማገልገል ይሾማሉ። አንዳንዶችም ያለማቋረጥ በረዳት አቅኚነት ያገለግላሉ። በየወሩ በመስክ አገልግሎት እንዲያሳልፉ የሚፈለግባቸውን 60 ሰዓት ለማሟላት ሁኔታቸው የሚፈቅድላቸው በመሆኑ ረዳት አቅኚዎች ሆነው የሚያገለግሉትን እነዚህን ቀናተኛ አስፋፊዎች እናመሰግናቸዋለን። ረዳት አቅኚዎች ሆነው ለማገልገል ያመለከቱት እነዚህ አስፋፊዎች ሹመታቸውን አክብደው እንዲመለከቱትና ወደ ግዴለሽነት የሚያመራ ማንኛውንም ዝንባሌ እንዲያስወግዱ ሽማግሌዎችም ሆኑ ሌሎች ሊያበረታቷቸው ይገባል።

ለአንድ ወይም ከዚያ ለሚበልጡ ወራት ረዳት አቅኚዎች ለመሆን ፈቃደኞች የሆኑትም ልክ እንደ ዘወትር አቅኚዎች በመጀመሪያ ወጪውን ማስላት ይኖርባቸዋል። (ሉቃስ 14:28) ይህም ሌሎች ክርስቲያናዊ ኃላፊነቶችን ችላ ሳይሉ የሚፈለግባቸውን ሰዓት ያህል በመስክ አገልግሎቱ ለማሳለፍ መቻል አለመቻላቸውን ቀደም ብለው በምክንያታዊነት መወሰንን ይጨምራል። አንድ ሰው ረዳት አቅኚ ሆኖ ለመመዝገብ የሚወስነው ስለ ግል ሁኔታዎቹ በጸሎት ካሰበ በኋላ መሆን ይኖርበታል። ሌሎች አመልክተዋል በሚል ስሜት ተገፋፍቶ የሚደረግ መሆን አይገባውም። የሚፈለገውን ሰዓት ለማሟላት በጽሑፍ የሰፈረ ፕሮግራም አውጥቶ በምክንያታዊነት የሚደረግ ውሳኔ መሆን ይኖርበታል። ማመልከቻውን በጥንቃቄ ማንበብና ለሚጠየቀው ጥያቄ ከልብ አዎን የሚል እውነተኛ መልስ ለመስጠት መቻል ያስፈልጋል።

በእርግጥ ተጨማሪ ጥረት ማድረግ ይጠይቃል። በዓመት ውስጥ አንዳንድ ወራት የምሥራቹን በመስበኩ ሥራ ይበልጥ “ለመትጋት” የሚያመቹ ናቸው። (ሥራ 18:5) እነዚህም ወራት የመታሰቢያው በዓል የሚከበርባቸውን የመጋቢትንና የሚያዝያን ወራት እንዲሁም የክልል የበላይ ተመልካቹ ጉባኤውን የሚጎበኝባቸውን ወራት ይጨምራሉ። ብዙ አስፋፊዎች ልዩ እንቅስቃሴ በሚደረጉባቸው በእነዚህ ወራት በስብከቱ ሥራ ተጨማሪ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ጥብቅ የሆነ ፕሮግራም ለመከተል ይችሉ ዘንድ ራሳቸውን ለማሰልጠን ደስተኞች ናቸው። በውጤቱም ብዙውን ጊዜ በርከት ያሉ በረከቶች በማግኘታቸው ይደሰታሉ። (2 ቆሮ. 9:6) እረፍት በሚወስዱባቸው ወራትና በዓመቱ ውስጥ አምስት ቅዳሜና እሁዶች ባለው በማንኛውም ወር አቅኚዎች ለመሆን ብዙ አስፋፊዎች የተለየ ጥረት ያደርጋሉ። ይሁን እንጂ በሚመዘገቡበት ጊዜ ረዳት አቅኚ ሆነው በሚሠሩባቸው ወራት ሁሉ 60 ወይም ከዚያ በላይ ሰዓት ሪፖርት በማድረግ “ቃላችሁ አዎን አዎን . . . ይሁን” የሚለውን መሠረታዊ ሥርዓት አጥብቆ የመከተልን አስፈላጊነት መገንዘባቸውን ያሳያሉ። — ማቴ. 5:37

አቅኚዎች ለመሆን ያልቻሉ አስፋፊዎች ደግሞ ከረዳት አቅኚዎች ጋር ለመሥራት ዝግጁዎች በመሆንና ቋሚ ቀጠሮ በመውሰድ ለመርዳት ይችላሉ። የሚቻል ከሆነ ከአቅኚዎች ጋር ረጅም ሰዓት ማገልገል ጠቃሚ ነው። አቅኚዎች በተለይ በጠዋት፣ ከሰዓት በኋላ ቆየት ብሎ ወይም አመሻሹ ላይ አብረዋቸው የሚያገለግሉ የሌሎች አስፋፊዎችን ድጋፍ ቢያገኙ ይደሰታሉ። ረዳት አቅኚዎች ተመላልሶ መጠየቆችን በማድረግና የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን በማስጀመር ከሌሎች ጋር ለመሥራት ቢጋበዙ ደስ ይላቸዋል። በዚህ መንገድ ለረዳት አቅኚዎች ድጋፍ የሚሰጡ ሁሉ በመስጠት የሚገኘውን ብዙ ደስታ ያጭዳሉ። — ሥራ 20:35

ብዙ ረዳት አቅኚዎች የሚያሳዩት ትጋት በጥልቅ የሚደነቅ ነው። አብረዋቸው በአቅኚነት ለማገልገል የሚችሉም ብዙ በረከቶችን እንደሚያገኙ ሊጠባበቁ ይችላሉ። (ምሳሌ 10:4) ተጨማሪ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ከሚገኘው ደስታ ተካፋይ ለመሆን ረዳት አቅኚ የምትሆነው መቼ ነው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ