ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች
ካሜሩን፦ በሰኔ ወር 18,810 የሚያክል አዲስ የአስፋፊዎች ቁጥር ላይ የደረሱ ሲሆን በዚያው ወር 84 ተጠምቀዋል።
ኮት ዲ ቩዋር፦ በሰኔ ሪፖርት ያደረጉ 4,330 አስፋፊዎች ነበሩ። ይህም በዚህ የአገልግሎት ዓመት ለስድስተኛ ጊዜ የተገኘ አዲስ የአስፋፊዎች ቁጥር ነው።
ኢጣልያ፦ በሰኔ ወር በመስክ አገልግሎት ተሰማርተው የነበሩ 198,179 አስፋፊዎች ስለነበሩ ሌላ አዲስ የአስፋፊዎች ከፍተኛ ቁጥር ሪፖርት አድርጋለች። በዚያው ወር ውስጥ ሃያ ሁለት አዳዲስ ጉባኤዎች ተቋቁመዋል።
ሳኦ ቶሜ እና ፕሪንሲፔ፦ ሰኔ 30 ማኅበሩ በሕግ የተቋቋሟል። ይህም ለከፍተኛ እንቅስቃሴ በር የሚከፍት ነው። በወሩ ውስጥ 100 አስፋፊዎች ሪፖርት ማድረጋቸው ካለፈው ዓመት አማካይ ቁጥር 43 በመቶ ጭማሪ እንዳለ አሳይቷል።
ኡራጓይ፦ በሰኔ ወር 9,093 የሚያክል ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር ላይ ደርሰዋል።