የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 12/93 ገጽ 2
  • የታኅሣሥ የአገልግሎት ስብሰባዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የታኅሣሥ የአገልግሎት ስብሰባዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ታኅሣሥ 6 የሚጀምር ሳምንት
  • ታኅሣሥ 13 የሚጀመር ሳምንት
  • ታኅሣሥ 20 የሚጀምር ሳምንት
  • ታኅሣሥ 27 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
km 12/93 ገጽ 2

የታኅሣሥ የአገልግሎት ስብሰባዎች

ታኅሣሥ 6 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 105

10 ደቂቃ፦ የጉባኤው ማስታወቂያዎችና ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂ ያዎች።

20 ደቂቃ፦ “ሌሎች ሰዎች ስለ አምላክ ልጅ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲማሩ እርዷቸው።” በጥያቄና መልስ የሚሸፈን። በአንቀጽ 2 ላይ (ልምድ ባለው አስፋፊ) እንዲሁም በአንቀጽ 4 ላይ (በወጣት አስፋፊ) የሚቀርቡ ትዕይንቶችን አዘጋጅ። ሁሉም ከቤት ወደ ቤት በሚያደርጉት አገልግሎትም ይሁን መደበኛ ባልሆነ መንገድ ሲመሰክሩ ታላቁ ሰው የተባለውን መጽሐፍ እንዲያበረክቱ አበረታታ።

15 ደቂቃ፦ “‘መለኮታዊ ትምህርት’ ብሔራት አቀፍ ስብሰባ በናይሮቢና በአዲስ አበባ” ከአድማጮች ጋር የሚደረግ ውይይት የታከለበት ንግግር። የወረዳ ስብሰባውን በተመለከተ ጉባኤው ያደረገውን የመጨረሻ ዝግጅት ጨምረህ አቅርብ።

መዝሙር 121 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ታኅሣሥ 13 የሚጀመር ሳምንት

መዝሙር 155

10 ደቂቃ፦ የጉባኤው ማስታወቂያዎች፣ የሒሳብ ሪፖርትና ማኅበሩ የጉባኤው መዋጮ የደረሰው መሆኑን የገለጸበት ማስታወቂያ። ለጉባኤው ወጭዎችና ለማኅበሩ ዓለም አቀፍ ሥራ ማካሄጃ ጉባኤው ስለሚያደርገው የገንዘብ ድጋፍ ምስጋና አቅርብ። በመጪው ቅዳሜና እሁድ ለመስክ አገልግሎት የሚያገለግሉ አንድ ወይም ሁለት የመግቢያ ሐሳቦችን አቅርብ።

20 ደቂቃ፦ “በታኅሣሥ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ማስጀመር።” ከአድማጮች ጋር የሚደረግ ውይይት። አንቀጽ 4⁠ን ስታብራራ በተመላልሶ መጠየቅ ጊዜ እንዴት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መጀመር እንደሚቻል የሚያሳይ ትዕይንት አቅርብ። ከተቻለ ሁሉም በእያንዳንዱ ወር የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዲመሩ አበረታታ።

15 ደቂቃ፦ “መጽሔት ለማበርከት ጊዜ መድብ።” ከአድማጮች ጋር የሚደረግ ውይይት የታከለበት ንግግር። አንቀጽ 3 ላይ ስትደርስ በቅርቡ በወጡት መጽሔቶች ላይ ያሉትን ልዩ ልዩ ትምህርቶች በመጠቀም በክልላችን ለምናገኛቸው የተለያዩ ሰዎች እንዴት ማቅረብ እንደምንችል በምሳሌ አቅርብ።

መዝሙር 215 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ታኅሣሥ 20 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 19

7 ደቂቃ፦ የጉባኤው ማስታወቂያዎች።

15 ደቂቃ፦ “የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪህን ልብ ለመንካት ጣር።” በጥያቄና መልስ እንዲሁም በትዕይንት የሚቀርብ። በጉባኤው ያሉት ሁሉ የማስተማር ችሎታቸውን ማዳበር እንዳለባቸው የሚገልጸውን ነጥብ አጉላ። አንቀጽ 3⁠ን ካብራራህ በኋላ አንድ አስፋፊ ለዘላለም መኖር ከተባለው መጽሐፍ በምዕራፍ 1 አንቀጽ 13 እና 14 ላይ ባሉት ጥያቄዎች በመጠቀም ከመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪው ጋር እየተወያየ ምክንያቱን ሲያስረዳ የሚያሳይ ትዕይንት አቅርብ።

8 ደቂቃ፦ “የአገልጋዮች ትምህርት ቤት የሚሰጠውን ጥቅም ማስፋት” በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት የበላይ ተመልካች የሚቀርብ ንግግር።

15 ደቂቃ፦ “የሚያበረታቱ ታሪኮችንና ተሞክሮዎችን የያዘው የዓመት መጽሐፍ” ምዕራፋቸውና ቁጥራቸው ብቻ የተጠቀሱትን ጥቅሶች በማብራራት በግለት የሚቀርብ ንግግር። በደንብ ተለማምደው የተዘጋጁ አስፋፊዎች በጥር 1, 1990 ገጽ 30፣ በጥር 1, 1987 እና በጥር 1, 1986 በወጡት የመጠበቂያ ግንብ እትሞች ላይ ያሉትን ተሞክሮዎችና ትምህርቶች በጋለ ስሜት እንዲያቀርቡ ዝግጅት አድርግ።

መዝሙር 34 እና የመደምደሚያ ጽሎት።

ታኅሣሥ 27 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 53

10 ደቂቃ፦ የጉባኤው ማስታወቂያዎች። ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች። በጥር ወር እንዲበረከት የታቀደውን ጽሑፍ እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ትዕይንት አቅርብ።

15 ደቂቃ፦ አደንዛዥ ዕጾችን መሞከር ምን ስህተት አለው? በአሥራዎቹ ዕድሜ የሚገኙ ሁለት አስፋፊዎች ከአንድ ሽማግሌ ጋር ሆነው በትምህርት ቤት አደንዛዥ ዕጾችን መውሰድ በስፋት የተለመደ ስለመሆኑ ይወያያሉ። አስፋፊዎቹ አንዳንድ ወጣቶች አልፎ አልፎ አደንዛዥ ዕጾችን ሲወስዱ ምንም እንዳልሆኑ ይጠቅሳሉ። ሽማግሌው እርሱ ተማሪ ከነበረበት ጊዜ ወዲህ ሁኔታዎች የተበላሹ መሆናቸውን ይገልጻል። እርሱም አደንዛዥ ዕጾች በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ተለይተው ያልተጠቀሱ መሆናቸውን ይናገራል፤ ይሁን እንጂ አደንዛዥ ዕጾችን በተመለከተ ምክንያቱን ማስረዳት በተባለው መጽሐፍ በገጽ 106–12 ላይ ጥሩ መመሪያዎች እንደሚገኙ ይናገራል። ወጣቶቹ ጥቅሶቹን ያነባሉ። ሽማግሌው ከእነርሱ ጋር ጥያቄዎችን እያቀረበ በመወያየት ትምህርቱን ይሸፍናል። ወጣቶቹ ከዕድሜ እኩዮቻቸው የሚደርስባቸውን ተጽዕኖ በግላቸው ለመቋቋም የሚረዷቸውን ልዩ ልዩ መንገዶች በተመለከተ ያላቸውን ሐሳብ ያቀርባሉ።

20 ደቂቃ፦ “ሥራው እየተስፋፋ ስለሄደ ተጨማሪ የመንግሥት አዳራሾች አስፈልገዋል።” አባሪ ሆኖ በቀረበው ጽሑፍ ላይ በጥያቄና መልስ የሚሸፈን። ሽማግሌዎች የመንግሥት አዳራሽ ለመሥራት ሲያስቡ በመጀመሪያ ከአካባቢው የሕንፃ ሥራ ኮሚቴ ጋር ለምን መገናኘት እንዳለባቸው ምክንያቶቹን አጉላ።

መዝሙር 10 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ